የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የየካቲት 2011 (እ.አ.አ)
ደስታችሁ እንዴት ታላቅ ይሆናል
ሌሎች በዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በልባቸው ለመውሰድ እንደረዳችሁ በማወቅ በላይ የሚበልጥ አስደሳችና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ብዙ ደስታዎች የሉም። ይህን አይነት ደስታ ለማግኘት እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ አባላት እድል አላቸው። ስንጠመቅ፣ “በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን ]እንቆም] ዘንድ፣ እናም በጌታ [እንድን] ዘንድ እስከሞትም ድረስ እንኳን በሁሉም ቦታ [እንኖር] ዘንድ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትም [ይኖረን] ዘንድ እናም የፊተኛውን ትንሳኤ ከሚያገኙት ጋርም [እንቆጠር] ዘንድ” ቃል ኪዳን ገብተናል (ሞዛያ 18፧9)።
አባላት በሙሉ ፣ የትም ቢሆኑ እና ለስንት ጊዜም ህይወት ቢኖራቸው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ወደ አለም ለመውሰድ ለቤተክርስቲያኗ የተሰጠውን ሀላፊነት ክፍል ተቀብለዋል። ጌታ በግልፅ እንዲህ ብሏል፧ “እነሆ፣ የላኳችሁ እንድትመሰክሩ እና ሰዎችን እንድታስጠነቅቁ ነው፣ እናም የተጠነቀቀ ሰው ጎረቤቱን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው” (ትምህርቶች እና ቃል ኪዳን88:81)። የሙሉ ጊዜ ሚስዮኖች የቤተክርስቲያኗ አባል ያልሆኑትን ለማስተማር ሀይል አላቸው። የቤተክርስቲያኗ አባላት ጌታ ሚስዮኖች እንዲያስተምሯቸው ያዘጋጃቸውን ለማግኘት ሀይል ይኖራቸዋል።
ጌታ በአካባቢያችን ሰዎችን ለማስተማር እንዳዘጋጀ እምነት ሊኖረን ያስፈልገናል። ማን እንደሆኑና መቼ እንደሚዘጋጁ ያውቃል፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ወደ እነርሱ ሊመራንና እንዲማሩ የምንጋብዝበትን ቃላት ሊሰጠን ይችላል። በ1832 (እ.አ.አ) ለሚስዮን ጌታ የሰጠው ቃል ኪዳን እኛ የተዘጋጁ ሰዎችን በሚስዮን እንዲማሩ ለማግኘት በተሰጠን ሀላፊነትም ደግሞ የሚሰጠን ቃል ኪዳን ነው፧ “እውነትን እና የሚሄድበትን መንገድ የሚያስተምረውን አፅናኝንም እልክለታለሁ፤ እናም ታማኝ ከሆንውም፣ እንደገናም በነዶም አነግሰዋለሁ” (ትምህርቶች እና ቃል ኪዳን 79:2-3)።
ለታማኝ ሚስዮን ቃል የተገባው ታላቅ ደስታም ለእኛም ልባችንን ወደ ሚስዮን ስራ ለምንሰጠው ታማኝ አባሎች ተሰጥቷል።
“እናም አሁን፣ ወደ አባቴ ቤት ባመጣችሁት አንድ ነብስ ደስታችሁ ታላቅ ከሆነ፣ ወደ እኔ ብዙ ነብሶችን ብታመጡ ደስታችሁ ምን ያህል ይሆናል!
“እነሆ፣ ወንጌሌ እና አለቴ እናም ደህንነቴ በፊታችሁ ነው።
“እንደምትቀበሉ በማመን በእምነት አባቴን በስሜ ጠይቁ እናም ለሰው ልጆች አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ የሚገልጠውን መንፈስ ቅዱስ ይኖራችኋል”(ትምህርቶች እና ቃል ኪዳን 18:16-18)።
ለመማር የተዘጋጁትን ለማወቅና ለመጋበዝ ከሚረዳን ከመንፈስ ቅዱስ በተጨማሪ፣ ጌታ እንዲመሩን መሪዎችን ጠርቷልም አሰላጥኗልም። በየካቲት 28 ቀን 2002 (እ.አ.አ) በተጻፈው ደብዳቤ፣ ቀዳሚ አመራር የሚስዮን ስራን ከፍተኛ ሀላፊነት በኤጲስ ቆጶሶችና በዎርዶች ላይ አሳርፈዋል።1 በዎርድ ወይም በግርንጫፍ ሸንጎ እርዳታ፣ የክህነት ስልጣን አመራር ኮሚቴ የሚስዮን እቅድ ያዘጋጃሉ። በእዚያም እቅድ ውስጥ አባላት እንዴት ለመማር የተዘጋጁትን ለማግኘት እንደሚችሉ ሀሳቦችን አሉ። እንደ ዎርድ ወይም ቅርንጫፍ የሚስዮን መሪ የተጠራም ሰው አለ። ያም የሚስዮን መሪ ከሙሉ ጊዜ ሚስዮኖችና ከተመራማሪዎች ጋር ቅርብ ግንኙነት አለው።
ሰዎችን ሚስዮኖች እንዲያስተምሯቸው የማግኘት ሀላፊነታችሁን ለማሟላት የሚረዷችሁ ብዙ መንገዶች አሉ። ቀላሉም መንገድ ከሁሉም የሚበልጥ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት ጸልዩ። ከአካባቢያችሁ መሪዎችና ሚስዮኖች ጋር ተነጋገሩ፣ የእነርሱን ሀሳቦች ጠይቁ እናም እንደምትረዷቸውም ቃል ግቡላቸው። በዚህ ስራ ላይ ከእናንተ ጋር ያሉትንም አበረታቱ። በምትሉት እና ምታደርጉት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እና እግዚአብሔር ጸሎቶችን እንደሚመልስ በሁሉም ጊዜ ምስክር ሁኑ።
ለመመሪያ በምትጾሙና በምትሰሩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እውነትን ለሚፈልጉት መንፈስ ቅዱስ እንደሚመራችሁ እመሰክራልሁ። በእራሴ አጋጣሚም ደስታቹ ወንጌልን ወደ ልባቸው ለመውሰድ እና በእምነት ለመፅናት ከመረጡት ጋር ዘለአለማዊ እንደሚሆን አውቃለሁ።
© 2011 በ Intellectual Reserve, Inc። መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/10. (እ.አ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/10. (እ.አ.አ)። First Presidency Message, February 2010 ትርጉም። Amharic. 09762 506