2011 (እ.አ.አ)
የሁሉም ነገሮች በዳግም መመለስ
ፌብሩወሪ 2011


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ የካቲት 2011 (እ.አ.አ)

የሁሉም ነገሮች በዳግም መመለስ

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ምስል

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን እንደ ቤተክርስቲያኗ አስፈላጊ ክፍል አደራጀ። እንደ አመራር፣ እኛም የሴቶች መረዳጃ ማህበር በህይወታችሁ አስፈላጊ እንደሆነ እንዲገባችሁ ለመርዳት ተስፋ አለን።

የአዲስ ኪዳን ሴቶች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን እንዳሳዩና በስራውም እንደተሳተፉ እናውቃለን። ሉቃስ10፧39 “ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ”ስለተቀመጠችው ማሪያም ይናገራል። በዮሀንስ 11፧27 ስለክርስቶስ ማርታ እንዲህ መሰከረች፧ “እርስዋም፣ አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው።” ስራ 9፧36፣ 39 “ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፣ … እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ነበረች። … መበለቶችም ሁሉ …ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ” ይላል። በ ሮሜ 16፧1–2 ውስጥ ፌቤን “የቤተክርስቲያን አገልጋይ” እና “ለብዙዎችደጋፊ ነበረች።”

እነዚህ የእምነት፣ የምስክር፣ እና የአገልግሎት ንድፎች በኋለኛው ቀን ቤተክርስቲያንም ይቀጥላሉ እና በሴቶች መረዳጃ ማህበር መደራጀትም ህጋዊ ሆነዋል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት ጁሊ ቢ ቤክ እንዳስተማሩት፣ “አዳኝ ማሪያምን እና ማርታን በአዲስ ኪዳን ዘመን ውስጥ በስራው እንዲሳተፉ እንደጋበዛቸው፣ ሴቶች በዚህ ዘመን በጌታ ስራ ተሳታፊ እንዲሆኑ ህጋዊ ሀላፊነት አላቸው። የሴቶች መረዳጃ ማህበር በ1842 (እ.አ.አ) መደራጀቱ የሴቶች አጠቃላይ ሀይልን እና የጌታን መንግስት ለመገንባት የተሰጣቸው ልዩ ሀላፊነትን አነሳስቷል።”1

እምነትን እና የግል ጻድቅነትን ለማሳደግ፣ ቤተሰቦችንና ቤቶችን ለማጠናከር፣ እና እርዳታ የሚያስፈልጓቸውን ለመፈለግና ለመርዳት በሆኑት በእነዚህን የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማዎች ላይ ስናተኩር ስራችንን እናከናውናለን።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር በደህንነት ስራ ለመርዳት በመለኮት የተደራጀ እንደሆነ እመሰክራለሁ። እያንዳንዷ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህት ይህን ቅዱስ ስራ ለማከናወን አስፈላጊ ሀላፊነት አላት።

ስልቪያ ኤች ኦልረድ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ።

ከቅዱስ መጻህፍት

ኢዩኤል 2፧28–29ሉቃስ 10፧38–42ኤፌሶን 1፧10

ከታሪካችን

እህት ጁሉ ቤክ እንዳስተማሩት፣ “የሴቶች መረዳጃ ማህበርን በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተደረገ የዳግም መመለስ ህጋዊ ክፍል እንደሆነ እናውቃለን።”2 ዳግም መመለስ የተጀመረው በ1820 (እ.አ.አ.) በነበረው በመጀምሪያው ራዕይ ነበር እናም “ሥርዓት በሥርዓት፣ ትእዛዝ በትእዛዝ” ቀጠለ ትምህርት እና ቃልኪዳን 98:12። በመጋቢት 17 ቀን 1842 (እ.አ.አ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሲደራጅ፣ ነቢዩ ሴቶችን በዳግም በተመለሰው ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላላቸው አስፈላጊ ቦታ አስተማራቸው። እንዲህም አለ፣ “ቤተክርስቲያኗ ሴቶች እንደዚህ እስከሚደራጁ ድረስ በፍጹም አልተደራጀችም ነበር።”3

ማስታወሻዎች

  1. ጁሊ ቢ ቤክ፣ “Fulfilling the Purpose of Relief Society,” Liahona, ህዳር 2008፣ 108።

  2. ጁሊ ቢ ቤክ፣ “የሴቶች መረዳጃ ማህበር አላማን ማሟላት፣” 108።

  3. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ስሚዝ [2007 (እ.አ.አ)]፣ 451።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. በኢየሱስ ክርስቶስ የሴት ደቀ መዛሙርቶች ስላላቸው እምነት ምሳሌ ለማሳየት የሚረዳ በዚህ ወር ምን ለእህቶቼ ለማቅረብ እችላለሁ?

  2. በዚህ ወር በዳግም ከተመለሰው ወንጌል ትምህርት ውስጥ ምስክሬን ለማጠናከር ምን ላጥና?

አትም