2011 (እ.አ.አ)
ቅዱስ ቤተመቅደስ -- ለአለም ምልክት
ሜይ 2011


ቅዱስ ቤተመቅደስ — ለአለም ምልክት

አስፈላጊ እና ታላቅ የሆኑ የቤተክርስቲያን አባልነት በረከቶች በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የምንቀበላቸው በረከቶች ናቸው።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ለእያንዳንዳችሁ ፍቅሬን እና ሰላምታዬን እሰጣለሁ እናም ሳነጋግራችሁ የሰማይ አባታችን ሀሳቤን እንዲመራና ቃላቴን እንዲያነሳሳ እጸልያለሁ።

ከእህት ኦልሬድ እና ኤጲስ ቆጶስ በርተን ስለቤተክርስቲያኗ በጎ ድርገት ስለሰማነው ጥሩ መልእክቶች አንዳንድ ነገሮች በማለት ንግግሬን እጀምራለሁ። እንደተመለከተው፣ ይህ ብዙ ህይወቶችን የባረከውን እና እየባረከ የሚቀጥለው የተነሳሳው ፕሮግራም 75ኛ አመት ነው ይህን ታላቅ ጥረት የጀመሩትን አንዳንድ ፈር ቀዳጅ ሰዎችን በግል ለማወቅ እድል ነበረኝ።

እህት ኦልሬድ እና ኤጲስ ቆጶስ በርተን እንዳሉት፣ የዎርድ ኤጲስ ቆጶስ በዎርዱ ግድብ ውስጥ የሚኖሩትን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የመንከባከብ ሀላፊነት አለው። አንድ ሺህ 80 አባላት እና ከመካከላቸውን 84 ባል የሞቱባቸው በነበሩበት በሶልት ሌክ ዎርድ ላይ እንደ ወጣት ኤጲስ ቆጶስ የማገልገል እድል ነበረኝ። እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ብዙ ነበሩ። ለቤተክርስቲያኗ የበጎ ድርገት ፕሮግራም እና ለሴቶች መረዳጃ ማህበርና ለክህነት ስልጣን ቡድኖች እንዴት ምስጋና ይሰማኝ አነበር።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የበጎ ድርገት ፕሮግራም በሁሉን ቻይ እግዚአብሔር የተነሳሳ እንደሆነ አውጃለሁ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ይህ አመት እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ከተደገፍኩበትን ሶስተኛ አመት ነው። ብዙ ስራ ያለበት፣ ብዙ ፈተና የተሞላበት፣ ግን ከመቆጠር በላይ ያሉ በረከቶች ያለብት ነበር። እነዚህ ስራ የበዛበት፣ በፈተናዎች የተሞሉ፣ ነገር ግን መቆጠር የማይቻሉ በረከቶች የነበሩባቸው አመቶች ነበሩ። ከእነዚህ በረከቶች መካከል ቤተመቅደሶችን ለመምረቅ የነበረኝ እድል አስደሳ እና ቅዱስ የነብሩ ናቸው። እናም ዛሬ ቤተመቅደስን በሚመለከት እናንተን ለማነጋገር እፈልጋለሁ።

ከ190 አመት በፊት በ1902 ዓ/ም የጥቅምት ጉባኤ፣ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ አንድ ቀን እኛ “ለህዝቡ ጥቅም በሚያስፈልጉበት በተለያዩ የአልም ክፍሎች ቤተመቅደሶችን ለመገንባት” እንድንችል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረው ነበር።1

ቤተክርስቲያኗ ከተመሰረተችበት በመጀመሪያው 150 አመት፣ ከ1830 እስከ 1980 ዓ/ም፣ ከከርትላንድ ኦሀዮ ና ከናቩ ኢለኖይ ቤተመቅደሶች በተጨማሪ ሀያ አንድ ቤተመቅደሶች ተገንብተው ነበር። ያን ከ1980 ዓ/ም እስካለፈው አመት መጨረሻ ከሚያደርሱን ካለፉት 30 አመታት ጋር ሲነጻጸር፣ 115 ቤተመቅደሶች ተገንብተውና ተቀድሰው ነበር። ትላንትና እንዲታወቁ ከተደረጉት ሶስት ቤተመቅደሶች በተጨማሪ፣ 26 ቤተመቅደሶች እየተገነቡ ወይም አላማ ላይ እያሉ ናቸው። ቁጥራቸውም እያደጉ ይቀጥላሉ።

በ1902 ዓ/ም ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ የነበራቸው አላማ ተማልተዋል። ፍላጎታችን ቤተመቅደስ ለአባላታችን በቀላል የሚገኝ እንዲሆን ነው።

አሁን እየተገነቡ ካሉት ቤተመቅደሶች መካከል አንዱ በማናስ ብራዚል ውስጥ የሚገኘው ነው። ከ6 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ባልይ በመራቅ ወደሚገኘው ወደ ሳኦ ፖሎ፣ ብራዚል እንደተጓዙ ሰማሁ። እነዚህ ታማኝ ቅዱሳን መንገድ ስላልነበረ በጀልባ ለአራት ቀንና ምሽት ተጉዘው ነበር። በውሀ የተጓዙበትን ከፈጸሙ በኋላ፣ ብዙ የሚበሉት ሳይኖራቸው እና ለመተኛት ሳይችሉ ለሶስት ቀን በአውቶባስ ተጓዙ። ለሰባት ቀን ከተጓዙ በኋላ የዘለአለም ስነስርዓቶች ወደተከናወኑበት ወደ ወደ ሳኦ ፖሎ፣ ብራዚል ቤተመቅደስ ደረሱ። የተመለሱበት ጉዞ አስቸጋሪ ነበር። ነገር ግን፣ የቤተመቅደስን ስነስርዓት እና በረከቶችን ተቀብለዋል፣ ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም፣ እነርሱም በቤተመቅደስ መንፈስና ለተቀበሉት በረከቶች ምስጋና ተሞልተው ነበር።2 አሁን፣ ከብዙ አመት በኋላ፣ በማናስ የሚገኙት አባላቶቻችን በሪዮ ኔግሮ ወንዝ ዳር የሚገነባውን ቤተመቅደስ እየተመለከቱ ይደሰታሉ። ቤተመቅደሶች በሚገነቡበት የትም ለሚገኙት ለታማኝ አባላታችን ደስታን ያመጣሉ።

በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ ብቻ የሚገኙትን በረከቶች ለመቀበል የሚደረጉትን መስዋዕቶች መስማት ልቤን ይነካል እናም ለቤተመቅደስ ያለኝን የምስጋና ስሜት ያሳድሳል።

የቲሂ እና ታራሬና ሙ ታምን እና የ10 ልጆቻቸውን ታሪክ ልንገራችሁ። ሚስዮኖች ከተሂቲ 240 ኪሎ ሜትር ወደ ደቡብ በሚገኘው ደሴት ላይ በመጡበት ጊዜ በ1960 ዓ/ም ቤተሰቡ በሙሉ ተጠመቁ። ወዲያውም በቤተመቅደስ ውስጥ እንደ ዘለአለም ቤተሰብ የመተሳሰር ፍላጎት ነበራቸው።

በእዚያ ጊዜ ለ Mou Tham ቤተሰብ ቅርብ የሆነው ቤተመቅደስ በአውሮፕላን ብቻ መደረስ የሚቻልበት ከነበሩበት 2500 ማይል (4 ሺህ ኪሎሜትር) የሚርቀው የሀሚልተን ኒው ዚላንድ ቤተመቅደስ ነበር። በትንሽ እርሻ ቦታ ላይ የሚኖሩት የሙ ታም ቤተሰብ ለአምሮፕላን ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም፣ ወይም በደሴቱ ላይ ለስራ ለመቀጠር ምንም እድል አልነበረም። ስለዚህ ወንድም ሙ ታም እና ልጃቸው ገራርድ ወደ ምዕራብ 4800 ኪሎ ሜትር በሚርቀው በኒው ካሊዶኒያ ማእደን ከሌላው ልጃቸው ጋር ለመስራት ወሰኑ። የቀጠራቸው ለሚሰሩለት ወደ ማእደኑ የሚጓዙበት ይሰጣቸው ነበር ነገር ግን ወደ ቤት የሚመለሱበትን አይሰጣቸውም።

ሶስቱ የ Mou Tham ወንዶች በማእደኑ በመቆፈር እና በመሸከም ለአራት አመት ሰሩ። ወንድም ሙ ታም ልጆቹን ትቶ ቤተሰብን ለመጎብኘት በአመት አንዴ ወደቤት ይመለስ ነበር።

ከአራት ከባድ ስራ በኋላ፣ ወንድም ሙ ታም እና ልጆቹ ቤተሰባቸውን ወደ ኒው ዚላንድ ለመውሰድ የሚበቃ ገንዘብ አጠራቀሙ። ከአንድ ሴት ልጅ በስተቀር ቤተሰብ በሙሉ አብረው ነበሩ። ለጊዜ እና ለዘለአለም ተሳሰሩ፣ ይህም አስደሳች እና አስደናቂ አጋጣሚ ነበር። ቀድመ አያቶቻቸውን ለማገልገልም ለሁለት ሳምነት በቤተመቅደስ ውስጥ ቆዩ። ከአንድ ሴት ልጅ በስተቀር ቤተሰብ በሙሉ አብረው ነበሩ። ለጊዜ እና ለዘለአለም ተሳሰሩ፣ ይህም አስደሳች እና አስደናቂ አጋጣሚ ነበር። ቀድመ አያቶቻቸውን ለማገልገልም ለሁለት ሳምነት በቤተመቅደስ ውስጥ ቆዩ።

ወንድም ሙ ታም ከቤተመቅደስ ወደ ማእደኑ ተመለሱ፣ በእዚያም ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ ላልቻለቸው ላገባችው ሴት ልጁ፣ ለልጇ እና ለባሏ መጓዣ ገንዘብ ለማጠራቀም ለሁለት አመት ሰራ።

በኋላም፣ ወንድም እና እህት ሙ ታም በቤተመቅደስ ለማገልገል ፈልገው ነበር። በእዚያ ጊዜ የፓፔተ ተሂቲ ቤተመቅደስ ተገንብቶና ተቀድሶ ነበር፣ እና ወንድም እና እህት ሙ ታም ሁለት ግዜ በሚስዮን አገለገሉ።3

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ቤተመቅደሶች ከድንጋይ እና ስሚንቶ በላይ ናቸው። እምነት ባላቸው እና በሚጾሙ የተሞሉ ናቸው። የተገነቡት በፈተና እና በምስክሮች ነው። በመስዋዕት እና በአገልግሎት የተቀደሱ ናቸው።

በእዚህ የዘመን ፍጻሜ በመጀመሪያ የተገነባው ቤተመቅደስ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ ነበር። በእዚያ ጊዜ ቅዱሳን ደሀ ነበሩ፣ ግን ጌታ ቤተመቅደስ እንዲገነቡ አዘዛቸው፣ ስለዚህ ይህን ገነቡ። ሽማግሌ ሒበር ሲ ኪምባል እንደጻፉት፣ “ይህን ለማከናወን የደረሰብንን ደሀንት፣ ፈተና፣ እና ጭንቀት ጌታ ብቻ ነው የሚያውቀው።”4 ከእዚያም፣ በጭንቀት ከተፈጸመ በኋላ፣ ቅዱሳን ከኦሀዩ እንዲወጡና ውድ ቤተመቅደሳቸውን እንዲተዉ ተገደዱ። በኋላም በምሥሥፒ ወንዝ ዳርቻ በኢለኖይ— ለጊዜም ቢሆን —መሸሸጊያ አገኙ። የሰፈሩባትን ናቩ ብለው ጠሯት እናም እንደገና ያላቸውን ሁሉ ለመስጠት እና በእምነት ሌላ ቤተመቅደስ ለአምላካቸው ገነቡ። መሰደድ እንደገና ተጀመረ፣ ነገር ግን የናቩ ቤተመቅደስ ገና በመጨረሱ ከቤታቸው እንደገና ተሳድደው ማንም ወዳልፈለገው በረሀ መሸሸጊያ ፈለጉ።

ዛሬ በመሰብሰቢያው አዳራሽ ውስጥ ካለነው ወደ ደቡብ የሚገኘው ቤተመቅደስን በአርባ አመት ለመገንባት የ40 አመት ትግል እና መስዋዕት እንደገና ተጀመረ።

በቤተመቅደስ መገንባትና በቤተመቅደስ መሳተፍ የመስዋዕት ደረጃን ይጠይቃል። በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኙትን በረከቶች ለእራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ለማግነት የሚሰሩና የሚታገሉ ቁጥራቸው ታላቅ ነው።

የቤተመቅደስን በረከቶች ለማግኘት ለምን ብዙዎች ያላቸውን ሁሉ ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው? ከቤተመቅደስ የሚመጡትን ዘለአለማዊ በረከቶች የሚያውቁት፣ እነዚያን በረከቶች ለመቀበል ምንም መስዋዕት ታላቅ እንዳልሆነ፣ ምንም ዋጋ ከባድ እንዳልሆነ፣ ምንም ትግል አስቸጋሪ እንዳልሆነ ያውቃሉ። መጓዝ የሚያስፈልግ ረጅም ጉዞም፣ መሸነፍ የማይችሉ መሰናከያዎች፣ ወይም መፅናናት የማይቻሉ ብዙ ስቃዮች የሉም። በቤተመቅደስ በምንገባቸው ቃል ኪዳኖች፣ እና ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥ በመሆን ብቻ በእዚህ እና በዘለአለም በእውነት ደስተኛ ለመሆን እንደምንችል ይገባቸዋል።

ዛሬ ብዙዎቻችን በቤተመቅደስ ለመሳተፍ ብዙ ችግር የለብንም። 80 ከመቶ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኗ አባላት ከቤተመቅደስ ከ320 ኪሎ ሜትር በማይርቅ ቦታ ነው የሚኖሩት፣ እናም ለብዙዎቻችን ይህ ረቀት በጣን ያነሰ ነው።

ለእራሳችሁ ወደ ቤተመቅደስ ከሄዳችሁ፣ እና በቤተመቅደስ ቀርባችሁ የምትኖሩ ከሆናችሁ፣ መስዋዕት የምታደርጉት ቢኖር ጊዜአችሁን መድባችሁ በየጊዜው በቤተመቅደስ ተሳታፊ መሆናችሁ ነው። በቤተመቅደሳችን ውስጥ ከመጋረጃው አልፈው ለሚጠብቁት ወኪል በመሆን መደረግ በመሆን የሚገባቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ለእነርሱ ስንሰራ፣ ለእራሳቸው ለማድረግ የማይችሉትን ለማከናወን እንደቻልን እናውቃለን። ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ እንዳሉት፣ “ለእነርሱ ጥቅም በምንጥርበት ከታሰሩበት ሰንሰለት ይወድቅላቸዋል፣ እናም ብርሀን እንዲበራባቸውና በእዚህ በልጆቻቸው የተሰራላቸው ስራ በመንፈስ አለም ይሰሙነ እነዚህን ሀላፊነቶች በማከናወናችሁ ይደሰቱ ዘንድ የከበባቸ ጭለማ የጠፋል።”5 ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ስራው የእኛ ነው።

በቤተሰቤ ውስጥ፣ ካጋጠሙን ቅዱስ እና የምናስታውሳቸው ጊዜዎች ቢኖሩ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አብረን ለሞቱን ቅድመ አያቶቻችን ያከናወንናቸው የመተሳሰር ስነስርዓቶች ናቸው።

ወደ ቤተመቅደስ ገና ካልገባቹ፣ ወይም ከነበራችሁ ግን ለመግቢያ ፈቃድ ቡቁ ካልሆናችሁ፣ ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ ብቁ ከመሆን በላይ የሆነ ምንም ታላቅ አላማ የለም። መስዋዕታችሁ ምናልባት ብቁ እንዳትሆኑ የሚያደርጋችሁን የድሮ ጸባያችሁን በመተው የመግቢያ ፈቃድ ለመቀበል የሚያስፈልጋችሁን ሁኔታ በህይወታችሁ ለመኖር እንድትችሉ ሊያደርጋችሁ ይችላል። እምነት መኖር እና አስራት ለመክፈል የሚያስፈልገው ውሳኔ ሊሆንም ይችላል። ምንም ቢሆን፣ ወደ እግዚአብሔር ቤተመቅደስ ለመግባት ብቁ ሁኑ። የቤተመቅደስ መጊያ ፈቃድን አግኙ እናም እንደ ውድ ንብረት ተመልከቱት፣ ይህም እንዲዚህ ነውና።

ወደ ጌታ ቤት እስከገባችሁ እና የሚጠብቃችሁን በረከቶች እስከምትቀበሉ ድረስ፣ ቤተክርስቲያኑ የምታቀርብላችሁን በሙሉ አልተቀበላችሁም። አስፈላጊ እና ታላቅ የሆኑ የቤተክርስቲያን አባልነት በረከቶች በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ የምንቀበላቸው በረከቶች ናቸው።

አሁን፣ ከሀያ አመት በታች የሆናችሁት ወጣት ጉዳኞቼ፣ ቤተመቅደስን ሁልጊዜ አላማችሁ አድርጉት። በበሩ ለመግባት እና በእዚያም ቅዱስና ዘለአለማዊ በረከቶችን ለመካቸል እንዳትችሉ የሚያደርገውን ምንም ነገር አታድርጉ። ከትምህርት በፊት በጠዋት በእዚህ ጥምቀት ለመሳተፍ በጠዋት የምትነሱትን ለሙታን ለመጠመቅ በየጊዜው ወደ ቤተመቅደስ የምትሄዱትን እሞግሳለሁ። ቀንን ለመጀመር ከዚህ የሚሻል ምንም ነገር ላስብበት አልችልም።

ለትንሽ ልጆች ወላጆች፣ የፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባልን ጥበባዊ ምክር ከእናንተ ጋር ልካፈል። እንዲህም አሉ፣ “ልጆቻቸው ከህጻንነታቸው ጀምሮ ፎቶውን ተመልክተው የህይወታቸው ክፍል እንዲሆን ዘንድ ወላጆች በቤታቸው እያንዳንዱ ክፍል የቤተመቅደስ ፎቶ ቢኖራቸው ጥሩ ነው። ወደ ቤተመቅደስ ስለመሄድ አስፈላጊ የሆነውን ውሳኔ የሚያደርጉበት እድሜአቸው ሲመጣ፣ ውሳኔ ወደፊት አድርገውበት ይሆናልና።”6

የመጀመሪያ ክፍል ልጆቻችን ይህን ይዘምራሉ፥

ቤተመቅደስን ማየት እወዳለሁ፣

በውስጡም አንድ ቀ እገባለሁ።

ከአባቴ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፣

ታዛዥ ለመሆን ቃል እገባለሁ።7

ስለቤተመቅደስ አስፈላጊነት ልጆቻችሁን እንድታስተምሩ እለምናችኋለሁ።

አለም ለህይወት የሚፈትን እና አስቸጋሪ ቦታ ሊሆን ይችላል። ሊያጠፋን በሚጥር ነገሮች በብዙ ጊዜ እንከበባለን። እናንተ እና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቅዱስ ቤት ስንሄድ፣ በውስጡ የምንሰራውን ቃል ኪዳን ስናስታውስ፣ እያንዳንዱን ፈተና ለመቋቋም እና እያንዳንዱን ፈተና ለማሸነፍ ተጨማሪ ችሎታ ይኖረናል። በእዚህ ቅዱስ መሸሸጊያ፣ ሰላም እናገኛለን፤ እንታደሳለን እናም እንጠናከራለን።

አሁን ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ከመጨረሴ በፊት አንድ ተጨማሪ ቤተመቅደስ ልጠቁም። አዲስ ቤተመቅደሶች በላም ውስጥ እየተገነቡ እያሉ፣ ከ2 ሺህ አምስት መቶ አመት በፊት በተገነባ ከተማ ውስጥ አንዱ ይሰራል። የምናገረውም በሮም ከተማ ውስጥ ስለሚገነባው ነው። የምናገረውም በሮም ከተማ ውስጥ ስለሚገነባው ነው።

ቤተመቅደስ በሙሉ አንድ አይነት ስራ ያለበትና አንድ አይነት በረከቶችና ስነስርዓቶች የሚገኙበት የእግዚአብሔር ቤት ነው። የሮም ቤተመቅደስ በአለም ውስጥ ብዙ ታሪክ ባለበት ቦታ፣ የጥንት ሐዋሪያት ጴጥሮስ እና ጳውሎስ የክርስቶስ ወንጌልን በሰበኩበትና በሰማእት በሞቱበት ነው የሚገነባው።

ባለፈው ጥቅምት፣ በሮም ሰሜን ምስራቅ በገጠር ቦታ እንደተሰበሰብን፣ መሪቷን የምትቀደስበት ጸሎትን የማቅረብ እድል ነበረኝ። የሮም ምክትል ከንቲባን ጉሴፒ ሲያርዲን እና የጣሊያን ሴነተር ሊቺዮ ማላንን አፈሩን ለመቆፈር የመጀመሪያ እንዲሆኑ እንድጠይቅ ስሜት ተሰማኝ። እያንዳንዱም በከተማቸው ቤተመቅደስ ለመገንባት እንድንችል ፈቃድ የመስጠት ውሳኔ ካደረጉት መካክል ነበሩ።

ቀኑ ዳመና ቢኖረውም የሚሞቅ ነበር፣ እናም የሚዘንብ ቢመስልም እስከዚህም አልዘነበም ነበር። አስደናቂ ዘማሪዎች “The Spirit of God” የሚለውን መዝሙር በጣሊያንኛ ሲዘምሩ፣ ሰማይ እና ምድር ለሁሉም ቻይ እግዚአብሔር በግርማዊ የማሞገስና ምስጋና መዝሙር የተገናኙ የሚመስል ነበር። እምባዎቼም ሊገደቡ አልተቻሉም።

በሚመጡት ቀናት፣ በእዚህ “ዘለአለማዊ ከተማ” የሚገኙት ታማኞች የዘለአለም ስነስርዓቶችን በእግዚአብሔር ቤት ይቀበላሉ።

በሮም ለሚገነባው ቤተመቅደስ እና የትም ቢሆኑ ለሚገንት ቤተመቅደሶቻችን ለሰማይ አባቴ ምስጋና አቀርባለሁ። ዘለአለማዊ ለሆኑ ጉዳዮች የተቀደሱት እያንዳንዱ ቅዱስ ቦታዎች እንዴት አስደናቂ ናቸው። እያንዳንዱ ለአለም እንደምልክት፣ የዘለአለም አብ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ፣ እኛን ለመባረክ እንደሚፈልግ፣ እናም በእርግጥም፣ በሁሉም ትውልዶች ወንድ እና ሴት ልጆቹን ለመባረክ እንደሚፈልግ እንደ ምስክር ቆመዋል። እያንዳንዱ ቤተመቅደሳችን ከመቃብር በኋላ ያለው ህይወት እውነት እንደሆነ እና በምድር ላይ እንዳለን አይነት ህይወት እርግጠኛ እንደሆነ ምስክራችንን የሚገልፅ ነው። ስለዚህም እመሰክራለሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ወደ ቤተመቅደስ ለመሄድ እና በልባችን እና በቤቶቻችን ቤተመቅደስ መንፈስ እንዲኖረን አስፈላጊ የሚሆኑትን መስዋዕቶች ሁሉ እናድርግ። የዘለአለም ህይወት እንዲኖረን እና በሰማይ አባታችን መንግስት ከፍ እንድንል የመጨረሻውን መስዋእት ባደረገልን በጌታችን እና በአዳኛችን እርምጃ በኩል ተከታዮች እንሁን። ይህም የልብ ጸሎቴ ነው፣ እናም ይህን የማቀርበው በአዳኛችን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ፣ በጉባኤ ሀተታ፣ ጥቅምት 1902፣ 3

  2. See Vilson Felipe Santiago and Linda Ritchie Archibald, “From Amazon Basin to Temple,” Church News, መጋቢት 13, 1993, 6።

  3. See ሲ ጄይ ላርሰን, “Temple Moments: Impossible Desire,” Church News, መጋቢት 16, 1996, 16።

  4. ሒበር ሲ ኪምባል, in ኦርሰን ኤፍ ውትኒ, Life of Heber C. Kimball (1945), 67

  5. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ [1998 (እ.አ.አ)]፣247።

  6. The Teachings of Spencer W. Kimball, ed. Edward L. Kimball (1982), 301

  7. Janice Kapp Perry, “I Love to See the Temple,” Children’s Songbook, 95.

አትም