2011 (እ.አ.አ)
ለጊዜአችን ትምህርቶች
ሜይ 2011


ለጊዜአችን ትምህርቶች

የመልከጸዴቅ የክህነት ስልጣንና የሴቶች መረዳጃ ማህበር የአራተኛው እሁዶች ትምህርቶች “ለጊዜአችን ትምህርቶች” የተወከሉ ይሆናሉ። እያንዳንድ ትምህርትም በቅርብ ከነበረው የአጠቃላይ ጉባኤ አንድ ወይም ተጨማሪ ንግግሮች መምረጥ ይቻላል። የስቴክ እና የዲስትሪክት ፕሬዘደንቶች የትኛዎቹ ንግግሮች መጠቀም እንደሚገባቸው መምረጥ ይችላሉ፣ ወይም ይህን ሀላፊነት ለኤጲስ ቆጶስ እና ለቅርንጫፍ ፕሬዘደንቶች ለመስጠት ይችላሉ። የመልከጼደቅ የክህነት ስልጣን ወንድሞች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች አንድ አይነት ንግግሮችን በአንድ እሁድ ቀን ማጥናታቸው አስፈላጊነትን መሪዎች ደጋግመው ማሳሰብ ይገባቸዋል።

በአራተኛው ሰንበት ትምህርት ተሳታፊዎች የቅርቡን የአጠቃላይ ጉባኤ ጋዜጣን እንዲያጠኑ እና ወደ ክፍል እንዲያመጡ ይበረታቱ።

ከእነዚህ ንግግሮች ትምህርትን የማዘጋጃ ሀሳቦች

ንግግሮችን ስታጠኑ እና ስታስተምሩ መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ጋር እንዲሆን ጸልዩ። ሌሎች መፅሀፎችን በመጠቀም ትምህርትን ለማዘጋጀት ሀሳብ ይመጣላችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን የጉባኤ ንግግሮች የተፈቀደለት የትምህርት መረጃ ነው። የተመደባችሁትም በቤተክርስትያኗ የቅርብ አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ እንደሚገኙት ሌሎችን ወንጌሉን ለመኖር እና ለመማር እንድትረዱአቸው ነው።

የክፍል አባሎች ፍላጎትን የሚያሟሉ መሰረቶችን እና ትምህርቶችን በመፈለግ ንግግሮችን አጥኑ። ደግሞም ታሪኮችን፣ የቅዱስ መጻህፍት የተጠቀሱበትን፣ እና እነዚህን እውነቶች ለማስተማር የሚረዷችሁን ቃላቶች ፈልጉ።

መሰረቶችን እና ትምህርቶችን እንዴት እንደምታስተምሩም ዘርዝራችሁ ጻፉ። በዝርዝር በጻፋችሁት ውስጥም የክፍል አባሎቻችሁን የሚረዱ ጥያቄዎችን ጨምሩ፧

  • በንግግሮች ውስጥ መሰረቶችን እና ትምህርቶችን ፈልጉበት።

  • ስለትርጉማቸው የሚያስቡበት።

  • የተረዱትን፣ ሀሳባቸውን፣ አጋጣሚያቸውን፣ እና ምስክሮችን የሚካፈሉበት።

  • እነዚህን መሰረቶች እና ትምህርቶች በህይወታቸው የሚጠቀሙበት ጥያቄዎችን ጨምሩ።

ወሮች

ግንቦት 2010 (እ.አ.አ)---ጥቅምት 2010 (እ.አ.አ)

ግንቦት 2011–ጥቅምት 2011

በግንቦት 2010 (እ.አ.አ) Liahona *የታተሙ ንግግሮች

ህዳር 2010 (እ.አ.አ)---ሚያዝያ 2011 (እ.አ.አ)

በህዳር 2010 (እ.አ.አ) Liahona *የታተሙ ንግግሮች

  • እነዚህ ንግግሮች (በብዙ ቋንቋዎች) በconference.lds.orgውስጥ ይገኛሉ።

አትም