2011 (እ.አ.አ)
ጥሩ ለማድረግ ያሉ እድሎች
ሜይ 2011


ጥሩ ለማድረግ ያሉ እድሎች

ጌታ ጊዜአዊ ፍላጎት ያላቸውን ለማሟላት በፍቅር ምክንያት እራሳቸውን እና ያላቸውን ለእግዚአብሔር እና ለስራው በመስዋዕት የሚሰጡ ሰዎች ያስፈልገዋል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የመልእክቴ አላማ ጌታ ደሆችንና በምድር ካሉት ልጆቹ መካከል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ያደረገውን እና የሚያደርገውን ለማክበር ነው። እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ልጆቹን እና እርዳታ የሚፈልጉትንም ያፈቅራል። እርዳታ የሚፈልጉትን እና እርዳታ የሚሰጡትን የሚባርክበት መንገዶች ፈጥሯል።

የሰማይ አባት በምድር ላይ ለሚበሉት ምግብ፣ ሰውነታቸውን ለሚሸፉበት ልብስ፣ እና እራሳቸው ለመርዳት ለመቻል ላለው የታላቅነት ስሜታ የሚለምኑትን የልጆቹን ጸሎቶች ያዳምጣል። ወንዶችና ሴቶችን በምድር ላይ ካስቀመጣቸው ጊዜ ጀምሮ እነዚህ ልመናዎች ይደርሱት ነበር።

በአለም አቀፍ በምትኖሩበት እነዚህ የእርዳታ ፍላጎቶችን ታውቃላችሁ። በዚህ ስሜታ ተካፋይ በመሆንም ልባችሁ ይነካል። ስራ ለማግኘት የሚታገል አንድ ሰው ሲያጋጥማችሁ፣ እርሱን ለመርዳት ስሜታ ይሰማችኋል። ባል ወደሞተባት ሴት ቤት ስትሄዱ እና ምግብ እንደሌላት ስትመለከቱም ይህ ይሰማችኋል። በእምድር መንቀጥቀጥ ወይም በእሳት ምክንያት በተደመሰሰው ቤታቸው አጠገብ ተቀምጠው የሚያለቅሱ ልጆች ፎቶዎችን ስትመለከቱ ይህ ይስማችኋል።

ጌታ ለቅሶአቸውን ስለሚሰማ እና ለእነርሱ ያላችሁን ዝልቅ ርህራሄ ስለሚሰማው፣ ከመጀመሪያ ጌዜ ጀምሮ ደቀ መዛሙርቱ እርዳታ የሚሰጡበት መንገድ ሰጥቷል። ልጆቹን ሌሎችን ከእርሱ ጋር ለመርዳት ጊዜአቸውን፣ ያላቸውን፣ እና እራሳቸውን በመስዋዕት እንዲሰጡ ይጋብዛል።

እርሱ እርስታ የሚሰጥበት መንገድ አንዳንዴ የቅድስና ህግ ተብሎ ይጠራ ነበር። በሌላም ጊዜ መንገዱ የትብብር ስርዓት ተብሎ ይጠራ ነበር። በጊዜአችን ይህም የቤተክርስቲያኗ የበጎ ድርገት ፕሮግራም ተብሎ ይጠራል።

ስሞቹ እና የሚሰራበት ሁኔታ በሰዎችን ፍላጎቶችና ጉዳዮች መሰረት ተቀይረዋል። ነገር ግን ጌታ ጊዜአዊ ፍላጎት ያላቸውን ለማሟላት በፍቅር ምክንያት እራሳቸውን እና ያላቸውን ለእግዚአብሔር እና ለስራው በመስዋዕት የሚሰጡ ሰዎች ያስፈልገዋል።

እኛንም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ከፍ ለማድረግ እንድንካፈል ጋብዞናል እናም አዝዞናል። ይህን ለማድረግም በጥምቀት ውሀዎች እና በእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች ውስጥ ቃል ኪዳኖች ገብተናል። ይህን ቃል ኪዳንንም በሰንበቶች ቅዱስ ቁርባንን ስንወስድ እናሳድሳለን።

የዛሬ አላማዬ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ለመርዳታ የሚሰጠንን እድል ለመግለጽ ነው። ባለን አጭር ጊዜ ስለሁሉም ለመናገር አልችልም። ተስፋዬ ለመርዳታ ያላችሁን ውሳኔ ለማሳደስ እና ለማጠናከር ነው።

ወደ እዚህ ስራ ጌታ ስለሚጋብዘን ከትንሽ ልጅነቴ ጀምሮ እዘምረው የነበረ መዝሙር አለ። በልጅነቴ ለሚያስደስተው ዜማ እንጂ ለሀይለኛዎቹ ቃላቶች ብዙ ትኩረት አልሰጥም ነበር። ዛሬ የመዝሙሩ ግጥም በልባችሁ እንዲሰማችሁ ጸሎቴ ነው። ቃላቶቹን እንደገና አድምጡ፥

በአለም ውስጥ ምን ጥሩ አድርጌአለሁ?

እርዳታ የሚያስፈልገውን ረጅቼአለሁ?

የከፋውን አፅናንቼአለሁ እና ሌላንስ ደስታ እንዲሰማው አድርጌአለሁ?

ይህን ካላደረኩ፣ በእርግጥም ወዳቂ ነኝ?

የሰው ችግር ቀለል ብሏል ዛሬ

ለመካፈል ፈቃደኛ ስለሆንኩኝ?

የታመሙት እና የደከሙት በመንገዳቸው ተረድተዋል?

እርዳታዬን ሲፈልጉ እዚያ ነበርኩኝ?

በላይ ከሚገኘው ቤት ከማለም በስተቀር

ተነሱ እና ተጨማሪ አድርጉ

ጥሩ ማድረግ አስደሳች ነው፣ መመዘን የማይቻል ደስታ፣

የሀላፊነት እና የፍቅርም ስራ።1

ጌታ በየጊዜ የሚያስነሳን ጥሪዎች ለሁላችንም ይሰጠናል። አንዳንዴም እርዳታ ለሚያስፈልገው የድንገት የሀዘን ስሜታ ይሆናል። አባት ልጅ ሲወድቅ እና ጉልበቱን ሲያቆስል ይህም ይሰማው ይሆናል። እናት በምሽት ላይ ልጇ በፍርሀት ሲያለቅስ ስትሰማ ስሜታው ይመጣባት ይሆናል። ወንድ ወይም ሴት ልጅ የከፋው ስለሚመስል አንድ ሰው ወይም በትምህርት ቤት ለሚፈራው ኡእሀዘን ስመኢታ ይሰማቸው ይሆናል።

ሁላችንም ለማናውቃቸው በሀዘን ስሜታ ተነክተን ይሆናል። ለምሳሌ፣ በጃፓን ውስጥ ከምድር መንቀጥቀጥ በኋላ የፓስፊክ ባህር ውሀ በጎርፍ እንደገባባቸው በሰማችሁ ጊዜ፣ ለተጎዱት ሀሳብ ነበራችሁ።

በክዊንስላንድ፣ አውስትሬልያ ውስጥ ስለነበርው ጎርፍ ባወቃችሁ ጊዜ ሀዘንም ተሰምቷችኋል። የዜና ሀተታው ስነት ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ግት ብቻ ነው የሚሰጠው። ነገር ግን ብዙዎቻችሁ የሰዎቹ ስቃይ ተሰምቷችኋል። ለመርዳት እና ለማፅናናት የመጣው የመነሳት ጥሪም ከ1 ሺህ 500 በላይ በሆኑት በአውስትሬሊያ የቤተክርስቲያን አባላት ተመልሶ ነበር።

የሀዘን ተካፋይነት ስሜታን በቃል ኪዳናቸው ወደ መስራት ቀይረውት ነበር። እርዳታ ለሚፈልጉት በተቀበሉት እርዳታ እና የመስጠትን እድል ለተጠቀሙበት የመጡትን በረከቶች እራሴም ልመለከተው ችያለሁ።

ጥበባዊ ወላጆችን በእያንዳንዱ በሌሎች ፍላጎቶች ወደ ወንድና ሴት ልጆቻቸው በረከቶችን የሚያመጡበትን መንገድ ያያሉ። ሶስት ልጆች የሚጣፍጥ ምግብ ያያዙ እቃዎችን ይዘው በበራችን መጡ። ወላጆቻቸው እርዳታ እንደሚያስፈልገን ያውቁ ነበር፣ እናም እኛን ለማገልገል ባላቸው እድል ልጆቻቸው ተሳታፊ እንዲሆኑ አደረጉ።

ወላጆቹም በደግ አገልግሎታቸው ቤተሰባችንን ባረኩ። በሚሰጡት ልጆቻቸው እንዲሳተፉ በመምረጥ፣ ለወደፊት የልጅ ልጆቻቸው በረከቶችን አቀረቡ። ልጆቹ ከቤታችን ሲሄዱ በፊታቸው ላይ የነበረው ፈገግታ ይህ እንደሚሆን እርግጠኛ እንድሆን አደረገኝ። ለጌታ አገልግሎት በመስጠት ደስታ እንደተሰማቸው ለልጆቻቸው ይነግራሉ። አባቴ ስለጠየቀኝ የጎሬቤታችንን ሜዳ ሳርም የተሰማኝን የእርካታ ስሜቴ አስታውሳለሁ። ሰጪ ለመሆን ስጋበዝ፣ “ስራው ጣፋጭ ነው፣ አምላኬ፣ ንጉሴ” የሚለውን የመዝሙር ግጥም አስታውሳለሁም አምናለሁም።2

እነዚህ የመዝሙር ግጥሞች የተጻፉት ጌታን በሰንበት በማምለክ ስለሚኖረው ደስታ ለመግለጽ እንደሆነ አውቃለሁ። ነገር ግን ምግብ ይዘው በበራችን ላይ የነበሩት ልጆች የጌታን ስራ የማከናወን ደስታን በሳምንት ቀን ውስጥ ይሰማቸው ነበር። ወላጆቻቸውም ጥሩ የማድረግ እድልን ተመለከቱ እናም ደስታን በትውልዶች ውስጥ አስተላለፉ።

እርዳታ ለሚፈልጉት እንክብካቤ ማድረግ ለወላጆች ልጆቻቸውን የሚባርኩበት ሌላ እድል ይሰጣል። ይህን በቤተክርስቲያን ውስጥ አንድ ጊዜ አየሁት። ትንሽ ልጅ የበጎ ድርገት ገንዘብን ለኤጲስ ቆጶሱ ወደ ቤተክስቲያ ሲገቡ በፖስታ ሲሰጥ አየሁ።

ቤተሰቡንና ልጁን አውቃቸው ነበር። ቤተሰቡ በዎርድ ውስጥ እድራታ ስለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰምተው ነበር። በፖስታ ውስጥ ብዙ የሆነ የጾም በኩራት ገንዘብ በሚጨምርበት ጊዜ አባትየው እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ዛሬ የምንጾመው እና የምንጸልየው እርዳታ ለሚፈልጉት ነው። ይህን ጆስታ ለኤጲስ ቆጶሱ ስጥልን። ከእኛ በላይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እንደሚሰጠው አውቃለኅ።”

በእዚያ ሰንበት ራብ ሳይሆን የሚሰማው፣ ያ ልጅ ይህን ወን በደስታ ያስታውሰዋል። በፈገግታው እና አባቱ በእምነት የሰጠውን የቤተሰብን በኩራት በጥብቅ በያዘበት ሁኔታ ይህን ለማወቅ እችላለሁ። ዲያቆን በሚሆንበት ጊዜ እና ምናልባትም ለዘለአለም ይህን ያስታውሳል።

እንደዚህ አይነት ደስታንም ከብዙ አመቶች በፊት ለጌታ በአይደሆ ይረዱ በነበሩት ሰዎች ፊት ላይ አይቼም ነበር። በሴኔ 5 ቀን፣ 1976 (እ.አ.አ) የቲቶን የውሀ ግድብ ፈረሰ። አስራ አንድ ሰዎች ተገደሉ። ብዙ ሺህ ሰዎችን በትንሽ ሰዓት ውስጥ ቤታቸውን ትተው መውጣት ነበረባቸው። አንዳንድ ቤቶች በጎርፍ ተደመሰሱ። የቤት ባለቤቶች ሊያደርጉት በማይችሉበት ሁኔታ ብቻ ነበር በአንዳንድ ቤቶች እንደገና ለመኖር ይቻል የነበረው።

ይህን አደጋ የሰሙትም ሀዘን ተሰማቸው፣ እናም አንዳንዶችም ጥሩ የማድረግ ጥሪም ተሰማቸው። ጎረቤቶች፣ ኤጲስ ቆጶሶች፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንቶች፣ የቡድን መሪዎች፣ የወንድ እና የሴት የቤት ለቤት አስተማሪዎች ቤታቸውንና ስራዎቻቸውን ትተው በጎርፍ የተበላሹትን ቤቶች ለማጽዳት ሄዱ።

አንድ ባልና ሚስት ከሽርሽር በኋላ ወደ ረክስበርግ ተመለሱ። የእራሳቸውን ቤት ለማየት አልሄዱም። በምትኩም፣ ኤጲስ ቆጶሳቸውን አግኝተው የት እርዳታ ለመስጠት እንደሚችሉ ጠየቁ። እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች መራቸው።

ከትንሽ ቀናት በኋላ ቤታቸውን ለማየት ሄዱ። በጎርፍ ተወስዶ ነበር። በቀጥታ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ተመለሱና፣ “አሁን ምን እንድናደርግ ይፈልጋሉ?” በማለት ጠየቁ።

የትም ብትኖሩም፣ የሀዘን ስሜታ ወደ ራስ ወዳጅ ወዳልሆነ ስራ የሚቀየርበትን ታዕምራት አይታችኋል። በታላቅ አደጋ ምክንያት ላይሆንም ይችላል። በክህነት ስልጣን ቡድን ውስጥ አንድ ወድንም እራሱን ወይም እራሷን እና ቤተሰቡን ወይም ቤተሰቧን ለመደገፍ ስለሚፈልግ ወይም ስለምትፈልግ ሰው ፍላጎት ሲገልጽ ይህንንም አይቻለሁ። በክፍሉ ውስጥ የነበረው የስሜታ መካፈል ተሰምቶኝ ነበር፣ ነገር ግን አንዳንዶች ስራ ለመስጠት የሚችሉትን ሰዎች ስም ሀሳብ አቀረቡ።

በክህነት ስልጣን ቡድን ውስጥ እና በአይደሆ ቤቶች ውስጥ የነበረው ጌታ እራሳቸውን ለመጃር ታላቅ ፍላጎት ያላቸውን የሚረዳበት መንገድ የሚገለጹባቸው ነው። ርህራሄ ይሰማናል፣ እናም በጌታ መንገድ ለመርዳት ምን እንደምናደርግ እናውቃለን።

በእዚህ አመት የቤተክርስቲያኗን የበጎ ድርገት ፕሮግራም 75ኛ አመትን እናከብራለን። ይህም የተጀመረው በታላቁ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሽቆልቆል ተብሎ በሚታወቀው ችግር ጊዜ ስራ፣ እርሻዎች፣ እና ቤቶች ያጡትን ለመርዳት ነበር።

የሰማይ አባት ልጆች የሚያስፈልጋቸው ታላቅ ጊዜአዊ ፍላጎት በዘመናችንም መጥተዋል እናም በሁሉም ዘመኖች ይመጣሉ። የቤተክርስቲያኗ የበጎ ድርገት ፕሮግራም መሰረታዊ መመሪያዎች ለአንድ ጊዜ ወይም ለአንድ ቦታ ብቻ አይደለም። እነዚህ ለሁሉም ጊዜዎች እና ቦታዎች ናቸው።

እነዚህ መሰረታዊ መመሪያዎች መንፈሳዊና ዘለአለማዊ ናቸው። በዚህም ምክንያት፣ እነዚህን መረዳት እና በልባችን ውስጥ ማስገባት ጌታ ሲጋብዘን በየት ይሁን መቼም የመርዳት እድልን ለማየትና ለመውሰድ እንድንችል ያደርጋሉ።

በጌታ መንገድ ለመርዳት ስፈልግ እና በሌሎች ስረዳ ይመሩኝ የነበሩት አንዳንድ መሰረታዊ መመሪያዎች እነዚህ ነበሩ።

መጀመሪያ፣ ሁሉም ሰዎች ደስተኛ የሚሆኑት እና እራሳቸውን የሚያከብሩት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ሲችሉ እና ሌሎችን ለመርዳት ሲጥሩ ነው። የሚያስፈልገኝን ለሚያሟሉት ምስጋና አለኝ። እራሴን ለመቻል ለረዱኝም ታላቅ ምስጋና ይሰማኛል። ከእዚያም በሚተርፈኝ እንዴት ሌሎችን ለመርዳት እንደምችል ላስተማሩኝም ከሁሉም በላይ ምስጋና ይሰማኛል።

ትርፍ የሚኖረኝ ከማገኘው በታች ሳጠፋ እንደሆነ ተምሬአለሁ። በዚህም ትርፍ መስጠት ከመቀበል በላይ እንደሆነ ለመማር ችዬአለሁ። ለዚህም ምክንያት፣ በጌታ መንገድ እርዳታ ስናቀርብ፣ እርሱም ስለሚባርከን ነው።

ፕሬዘደንት ሜሪያን ጂ ሯምኑ ስለበጎ ድርገት ስራ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በዚህ ስራ ድሀ እስክትሆኑ ድረስ ልትሰጡ አትችሉም።” ከእዚያም የሚስዮን ፕሬዘደንታቸውን ማልቭን ጄ ባለርድን እንዲህ ጠቀሱ፥ “ሰው ከጌታ ሙሉ ዳቦ ሳይቀበል ለጌታ ቁራሽ ለመስጠት አይችልም።”3

ይህን በህይወቴ እውነት እንደሆነ አግንቼዋለሁ። እርዳታ ለሚፈልጉት የሰማይ አባት ልጆች ደግ ስሆን፣ እርሱም ለእኔደግ ይሆናል።

በበጎ ድርገት ስራ ውስጥ የሚመራኝ ሁለተኛው የወንጌል መሰረታዊ መመሪያ የአንድነት ሀይል እና በረከት ነው። እርዳታ የሚፈልጉትን ሰዎች ለማገልገል ስንተባበር፣ ጌታ ልባችንን አንድ ያደርጋቸዋል። ፕሬዘደንት ጄ ሩብን ክላርክ፣ ዳግማዊ እንዲህ ብለዋል፥ “የተለያዩ ስልጣኔዎች ወይም ስራዎች የሚሰሩ ሰዎች አጠገብ በአጠገብ በበጎ ድርገት የአትክልት ስፍራ ሌላ ፕሮጀችት ሲሰሩ፣ ያም መስጠት የጋራ ወንድምነት ስሜትን ያመጣል።”4

የወንድምነት ስሜታ ተጨማሪነት ለሚቀበለውም ይሁን ለሚሰጠውም እውነት ነው። እስከዚህ ቀን ድረስ፣ አጠገብ በአጠገብ በጎርፍ በተሞላው ቤት ውስጥ ጭቃ አብሬው ስቆፍር ከነበርኩበት ሰው ጋር የግንኙነት ስሜታ አለ። ለእራሱና ለቤተሰቡ የሚችለውን ያህል ለማድረግ በመጣሩ ታላቅ የግል ክብር ይሰማዋል። ብቻችንን ብንሰራ ኖሮ፣ ሁለታችንም መንፈሳዊ በረከትን እናጣ ነበር።

ይህም ለእኔ ሶስተኛው የበጎ ድርገት ስራ መሰረታዊ መመሪያ ወደሆነው ይመራኛል፥ ሌሎችን ሲንከባከቡ እርስ በራስ ለመንከባከብ እንዲማሩ ዘንድ በስራውም ቤተሰባችሁን ከእናንተ ጋር አድርጉ። እርዳታ የሚፈልጉትን ለማገልገል ከእናንተ ጋር አብረው የሚሰሩት ወንድ እና ሴት ልጆች እርዳታ ሲያስፈልጋቸው እርስ በራስ ለመረዳዳት ይችላሉ።

ዋጋ ያለው አራተኛውን የቤተክርስቲያኗ በጎ ድርገት መሰረታዊ መመሪያ የተማርኩት ኤጲስ ቆጶስ ሆኜ ነበር። ይህም የመጣው ደሀውን ፈልጎ ለማግኘት ከቅዱሳት መጻህፍት ከመጣው ትእዛዝ ነው። እራሳቸው እና ቤተሰባቸው ለማድረግ የሚችሉትን ካደረጉ በኋላ እርዳታ የሚፈልጉትን መርዳት የኤጲስ ቆጶስ ሀላፊነት ነው። ጌታ እውነትን ለማግኘት እንደሚያደርጉው ደሀን ለመንከባከብ “ፈልጉ፣ እናም ታገኛላችሁ”5 የሚለው የሚቻል እንዲሆን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ ለማወቅ ችዬአለሁ። ነገር ግን በፍለጋው የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንትን ተሳታፊ ማድረግንም ተማርኩኝ። እርሷም ከእናንተ በፊት ራዕይል ልትቀበል ትችላለች።

አንዳንዶቻችሁ ይህን መነሳሻ ወደፊት በሚመጡት ወሮች ሊያስፈልጋችሁ ትችሉ ይሆናል። የቤተክርስቲያኗን የበጎ ድርገት ፕሮግራም 75ኛ አመትን ለማክበር፣ የአለም አቀፍ አባላት በአገልግሎት ቀን እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ። መሪዎች እና አባላት ፕሮእችቱ ምን አይነት እንደሆነ ንድፍ ሲያዘጋጁ ራዕይን ይፈልጉ።

የአገልግሎት ፕሮጀክት አላማን ስትሰሩ የምታስቡባቸው ሶስት ሀሳቦች ላቅርብ።

መጀመሪያ፣ እራሳችሁን እና በመንፈስ የምትመሩትን በመንፈስ አዘጋጁ። ልቦች በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ከተዘጋጀ ብቻ ነው የፕሮጀክቱን አላማ የሰማይ አባት ልጆች ህይወቶችን በመንፈሳዊ እና ጊዜአዊ በመባረክ እንደሆነ በግልጽ ለማየት የምንችለው።

ሁለተኛው ሀሳቤም ቢሆን በመንግስት ውስጥ ወይም በህብረተሰብ ውስጥ ለአገልግሎት የምትመርጧቸው ሰዎች የእርዳታ ፍላጎት አገልግሎት የሚሰጡት ሰዎችን ልብ የሚነካ ይሁን። የምታገለግሏቸው ሰዎች ፍቅራችሁ ይሰማችዋል። ያም መዝሙሩ ተስፋ እንደሚሰጠው የጊዜአዊ ፍላጎታቸውን ከማሟላት በላይ ደስተኛ እንዲያደርጋቸው ብዙ ያደርጋል።

በመጨረሻ የማቀርበው ሀሳቤም ከቤተሰቦች፣ ከቡድኖች፣ ከደጋፊ ድርጅቶች፣ እና በህብረተሰብ ውስጥ ከምታውቁት ሰዎች ሀይልን እንድትስቡ አላማ እንዲኖራችሁ ነው። የአንድነት ስሜታዎች በምትሰጡት አገልግሎት ላይ ጥሩ ውጤታዎችን ያባዛል። እናም በቤተሰቦች፣ በቤተክርስትያን፣ እና በህብረተሰብ ውስጥ የሚሰሙት እነዚህ የአንድነት ስሜታዎች ያድጋሉ እናም ስራው ካለቀ በኋላም ለረም ጊዜ የምታወሱ ይሆናሉ።

ይህም ምን ያህል እንደማመሰግናችሁ የምነግራችሁ እድል ነው። ለጌታ በምትሰጡት የፍቅር አገልግሎት፣ በአለም ውስጥ በምገናኛቸው ጊዜ እርዳታ ከሰጣችኋቸው ሰዎች ምስጋና ተቀብየም ነበር።

በጌታ መንገድ ስታገለግሏቸውን ከፍ የምታደርጓቸው መንገድን አገኛችሁ። እናንተ እና እንደ እናንተ አይነት ትሁት የጌታ አገልጋዮች ዳቦአችሁን በአገልግሎት ውሀ ላይ ጥላችኋል፣ እናም የረዳችኋቸው ሰዎችን በምላሽ የምስጋና ሙሉ ዳቦ ሊሰጡኝ ሞክረዋል።

እንደዚህም አይነት ምስጋና አብረዋችሁ ካገለገሉት ሰዎችም አግኝቼአለሁ። በፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን አጠገብ የነበርኩበትን አንድ ጊዜ አስታውሳለሁ። በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው የበጎ ድርገት አገልግሎት እየተነጋገርን ነበር። እጃቸውን ከፍ አድርገው፣ “ይህን ስራ እወደዋለሁ፣ እና ይህም ስራ ነው!” ሲሉ በወጣትነት አይነት መነሳሻቸው አስደንግጠውኝ ነበር።

ለመምህርም የሰማይ አባታችንን ልጆች ለምታገለግሉበት ስራ ምስጋናን አቀርባለሁ። ያውቃችኋል፣ እናም ጥረታችሁን፣ ትጋታችሁም እና መስዋዕታችሁን ያያል። በምትረዷቸው ሰዎችና ለጌታ አብራችሁ በምታገለግሉት ሰዎች ደስታ የስራችሁን ፍሬ ለማየት በረከትን እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ።

እግዚአብሔር አብ ህያው እንደሆነ እና ጸሎታችንን እንደሚሰማ አውቃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነም አውቃለሁ። እናንተ እና የምታገለግሏቸው እርሱን በማገልገል እና ትእዛዛቱን በማክበር ትቀደሳላችሁ እናም ትጠናከራላችሁ። በመንፈስ ቅዱስ ሀይልም፣ ጆሴፍ ስሚዝ የእውነተኛውን እና ህያውን ቤተክርስቲያን በዳግም የመለሰ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ እኔ እንደማውቀው እናንተም ታውቃላችሁ። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። ጌታ ጥሩ በማድረግ በሄደበት አይነት ጥሩ ምሳሌ ናቸው። “ደካማውን ደግፍ፣የላሉትን እጆች የሰለሉትን ጉልበቶች አቅና” የሚለውን እድል እንድንጠቀምበት እጸልያለሁ።6 በቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

አትም