2011 (እ.አ.አ)
እማዬ አዳነችን
ኦገስት 2011


ወጣቶች

እማዬ አዳነችን

በስድስት አመቴ፣ ታናሽ እህቴና እኔ የታላቅ እህቴን የቅርጫት ኳስ ጨዋታ እየተመለከትን ነበር። አባቴ ከእዚያ ሄደ፣ እናም እና ከእዚያምበኋላ ከእርሱ ጋር ወደቤት ለመሄድ ፈለግን፣ ስለዚህ በዝናብ እርሱን ለማግኘት መሮጥ ጀመርን። እርሱን ለማግኘት በማንችልበት ጊዜ፣ ከእናታችን ጋር ወደቤት ለመሄድ ወደ ስፖርት አዳራሹ ተመለስ፣ ነገር ግን ወደ ስፖርት አዳራሹ በገባንበት ጌዜ፣ ሁሉም ሰዎች ሄደው ነበር።

እኔን እና ታናሽ እህቴን ከዝናብ ለመሸፈን፣ አንድ ሰው ይመጣልን ዘንድ እየጸለይን፣ ከህንጻው አጠገብ እጅብ ብለን ቆመን እንደነበርን አስታውሳለሁ። ከእዚያም የቀይ መኪናችን በር ሲዘጋ እንደሰማን፣ እና ወደ ድምጹ እንደሮጥንም አስታውሳለሁ። “ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ እንደምትሰበስብ” እናታችን እንዴት እንዳቀፈችን በደንብ የማስታውሰው ግልጽ ትዝታ ነበረኝ (Nephi 10:4)። እማዬ አዳነችን፣ እናም በእዚያ ጊዜ እንደተሰማኝ አይነት በደህንነቴ እንደተጠበቅኩኝ አይሰማኝም ነበር።

በእኔ ላይ ስለነበራት ተጽእኖ ሳስብበት፣ የእናቴ ህይወት ወደ አዳኝ እንደሚጠቁመኝ እናም “የላሉትን እጆች የሰለሉትን ጉልበቶች አቅና” (D&C 81:5) የሚለው ምን ትርጉም እንዳለው እንዳሳየችኝ ተመልክቼአለሁ። “ከእራሷ በላይ” (Hymns, no. 220) የሆነውን ጥንካሬ በሰጣት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ተመክታለች።