2011 (እ.አ.አ)
የቅዱስ ሴቶች ማህበር
ኦገስት 2011


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት

የቅዱስ ሴቶች ማህበር

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ሁለተኛ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እላይዛ አር ስኖው እንዳስተማሩት፥ “ሐዋሪያው ጳውሎስ በጥንት ስለቅዱስ ሴቶች ተናገረ። ቅዱስ ሴት መሆን የእያንዳንዳችን ሀላፊነት ነው። ቅዱስ ሴቶች ከሆንን፣ ከፍ ያለ አላማ ሊንረን ይገባናል። አስፈላጊ ሀላፊነቶችን እንድናከናውን እንደተጠራን ይሰማናል። ማንም ከእነዚህ ግዴታ ነጻ የሆነ የለም። ከሁሉም የተለየች፣ እና ተፅዕኖዋ ጥብ ሆኖ የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለመመስረት ታላቅ ስራ ለመስራት የምትችል ማንም እህት የለችም።”1

እህቶች፣ የተለየን አይደለንም ወይም ተፅዕኖአችን የጠበበ አይደለም። በሴቶች መረዳጃ ማህበር የተሳታፊነትን ስጦታ በመቀበል፣ ነቢዩ ጆሴፍ “ከአለም ክፋቶች የተለየ፣ ምርጥ፣ ምግባረ ጥሩ፣ እና ቅዱስ” ማህበር ብሎ በገለጸው ውስጥ ክልፍ ሆነናል።2

ይህ ማህበር መመሪያ፣ አገልግሎት እና የማስተማር እድሎች በመስጠት እምነታችንን እንድናጠናክርና በመንፈስ እንድናድግ ይረዳናል። በአገልግሎታችን በህይወታችን ውስጥ አዲስ መጠን ይጨምራል። በመንፈስ ወደፊት እንሄዳለን፣ እና አባል የመሆን፣ የማንነት፣ እና የግል ብቁነት ስሜታችን ያድጋል። የወንጌሉ አላማ ችሎታችንን በሙሉ ለማሟላት እድል ለመስጠት እንደሆነ ይገባናል።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር የቤተመቅደስ በረከቶችን ለመቀበል፣ የገባነውን ቃል ኪዳን እንድናከብር፣ እና በፅዮን ስራ ተሳታፊ እንድንሆን ለመዘጋጀት ይረዳናል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እምነታችንን እና የግል ጻድቅነታችንን እንድናሳድግ፣ ቤተሰቦችን እንድናጠናክር፣ እና እርዳታ የሚፈልጉትን እንድንፈልግና እንድንረዳ እርዳታ ይሰጠናል።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስራ ቅዱስ ነው፣ እናም ቅዱስ ስራ መስራት በእኛ ቅድስናን ይፈጥራል።

ስልቪያ ኤች ኦልረድ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ።

ከቅዱስ መጻህፍት

ዘጸአት 19፥5ምሳሌ 24፥3–41 ተሰሎንቄ 4፥7ቲቶ 2፥3–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 38፥2446፥3382፥1487፥8ሙሴ 7፥18

ከታሪካችን

ከናቩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ጋር ሲነጋገር፣ ነቢዩ ጆሴፍ እህቶች ንጹህና ቅዱስ ሲሆኑ፣ በአለም ላይ ታላቅ ተፅዕኖ እንደሚኖራቸው በመግለፅ በቅድስና ላይ ትኩረት ጣለ። እንዲህም ገለጸ፥ “የዋህነት፣ ፍቅር፣ ንጹህነት—እነዚህ እናንተን ሊያጎሏችሁ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው። … ይህ ማህበር … በመካከላቸው ያሉትን ንግስቶች የማዘዝ ሀይል ይኖረዋል። … የምድር ንጉሶች እና ንግስቶች ወደ ፅዮን ይመጣሉ፣ እናም ሰላምታቸውን ያቀርባሉ።” ቃል ኪዳን በገቡበት የሚኖሩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች የልዑል ሰዎችን ክብር የሚያገኙ ብቻ ሳይሆን፣ ጆሴፍ ለእህቶች ቃል እንደገባው፣ “በእድላችሁ የምትኖሩ ከሆናችሁ፣ መላእክቶች ጓደኞቻችሁ ከመሆን ሊገደቡ አይችሉም።”3

እህቶች በአገልግሎት ስራ እና ሌሎችን በማዳን ሲሳተፉ፣ በግልም የተቀደሱ ይሆናሉ። የነቢዩ እናት ሉሲ ማክ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ለማከናወን የሚችሉትን ጥሩ ነገሮች እንዲህ ተካፍለው ነበር፥ “በሰማይ ሁላችንም አብረን እንድንቀመጥ ዘንድ፣ እርስ በራስ መፈቃቀር፣ እርስ በራስ መጠባበቅ፣ እርስ በራስ መፅናናትና ትምህርትን ማግኘት ይገባናል።”4

ማስታወሻዎች

  1. እላይዛ አር ስኖው፣ “An Address,” Woman’s Exponent መስከረም 15፣ 1873፣ 62።

  2. ጆሴፍ ስሚዝ፣ in History of the Church, 4፧570።

  3. ጆሴፍ ስሚዝ፣ in History of the Church, 4፧605፣ 606።

  4. ሉሲ ማክ ስሚዝ፣ in Relief Society, Minute Book Mar. 1842–መጋቢት 1844, entry for መጋቢት 24, 1842, Church History Library, 18–19

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. የምጠብቃቸውን እህቶች “ከፍ ያለ አላማዎች” እንዲኖራቸው እና እንዲያሟሉ ነዴት ልረዳቸው እችላለሁ?

  2. ህይወቴን “ምርጥ፣ ምግባረ ጥሩ፣ እና ቅዱስ” ለማድረግ ምን እያደረግሁ ነኝ?

አትም