2011 (እ.አ.አ)
በቤት ያለ ፍቅር—የነቢያችን ምክር
ኦገስት 2011


የቀዳሚ አመራር መልእክት

በቤት ያለ ፍቅር—የነቢያችን ምክር

የተባረከ የቤተሰብ ህይወት

“ብዙዎችን ከቀመስን፣ በብዙ ቦታዎች ከተንከራተትን እና አንዳንዴ የአለም ጥልቀት የሌለውን ከተመለከትን በኋላ፣ ልንቆጥርበት ከምንችልባቸው ከቤትና ከቤተሰብ እናም ከምንወዳቸው ታማኝነት ጋር ተካፋይ ለመሆን ላለን እድል ምስጋናችን ያድጋሉ። በሀላፊነት፣ በክብር፣ ተካፋይ በመሆን መተሳሰር ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅም እንችላለን። የተባረከ የቤተሰብ ህይወት ግንኙነትን ቦታ የሚወስድ ምንም ነገር ለመኖር እንድማይችልም ተምረናል።”1

ፍቅራችንን መካፈል

“ልጃችሁን ሞግሱ እና እቀፉ፤ በተጨማሪም ‘እወድሀለሁ’ በሉ፤ ሁልጊዜም ምስጋናችሁን ስጧቸው። መፍትሄ የሚገኝበት ችግርን ሰው ከመወደድ በላይ አስፈላጊ አታድርጉት። ጉደኞች ይሄዳሉ፣ ልጆች ያድጋሉ፣ የሚወደዱትን ይሞታሉ። ከህይወታችን ወጥተው እስከሚሄዱ እና ‘ይህን ባደርግስ’ እና ‘ይህን ባደርግ ኖሮ’ ከሚሉት ስሜታዎች ጋር እስከምንቀር ድረስ ሌሎችን ችላ ለማለት ቀላል ነው። …

“ህይወትን በምንኖርበት እንደሰትበት፣ በጉዞም ደስታን እናግኝ እናም ፍቅራችንን ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰቦቻችን ጋር እንካፈል። አንድ ቀን፣ እያንዳንዳችን ነገ አይኖረንም። ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ችላ አንበል።”2

ፍቅራችንን ማሳየት

“ወንድሞች፣ ባለቤቶቻችንን በታላቅ ስሜት እና በክብር እንንከባከብ። እነርሱ የዘለአለም ጉዳኞቻችን ናቸው። እህቶች፣ ባለቤቶቻችሁን አክብሩ። ጥሩ ቃል መስማት ያስፈልጋቸዋል። የጓዳኛ ፈገግታ ያስፈልጋቸዋል። ሙቅ የሆነ የእውነተኛ ፍቅር አስተያየትም ያስፈልጋቸዋል። …

“ወላጆች ለሆናችሁት፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ለልጆቻችሁ ፍቅር አሳዩ። እንደምትወዷቸው ታውቃላችሁ፣ ነገር ግን እነርሱ እንዲያውቁትም አድርጉ። እነርሱ ውድ ናቸው። እንዲያውቁትም አድርጉ። በየቀኑ እነርሱ የሚያስፈልጋቸውን በመስጠት ስትንከባከቡ እና ወላጅ ከመሆን ጋር ከሚመጡት ፈተናዎች ጋር ስትታገሉ ለእርዳታ የሰባይ አባታችንን ጥሩ። እነርሱን በማሳደግ ከእራሳችሁ ጥበብ በላይ ያስፈልጋችኋል።”3

የፍቅር መግለጫ

“ለወላጆት፣ ለልጆቻችሁ ፍቅራችሁን ግለጹ። የአለም ክፋትን ለመቋቋም ይችሉ ዘንድ ጸልዩላቸው። በእምነት እና በምስክር እንዲያድጉ ጸልዩላቸው። የጥሩነት እና ሌሎችን የሚያገለግሉበት ህይወት እንዲፈልጉ ጸልዩላቸው።

“ልጆች፣ ወላጆቻችሁ እንደምትወዷቸው እንዲያውቁ አድርጉ። ለእናንተ ላደረጉላችሁ እና በማድረግ ለሚቀጥሉት ምን ያህል እንደምታመሰግኗቸው እንዲያውቁ አድርጉ።”4

ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው

“ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆነው በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች ሁልጊዜም የሚያስገባ ነው። ብዙ ጊዜ ምን ያህል እንድምንወዳቸው ማወቅ አለባቸው ብለን እንገምታለን። ነገር ግን መገመት አይገባንም፣ እንዲያውቁ ማስደረግ ይገባናል። ዊልያም ሼክስፒር እንደጻፈው፣ ‘ፍቅራቸውን የማያሳዩትን አይወዱም።’ በተናገርናቸው የደግነት ቃላት ወይም ባሳየናቸው ፍቅር ቅርታ አይሰማንም። ይህም ሳይሆን፣ ቅርታ የሚሰማን ለእኛ ታላቅ ትርጉም ካላቸው ሰዎች ግንኙነቶች ጋር እንደ እነዚህ አይነት ነገሮች ሲቀሩ ነው።”5

ሰማይን ማቅረብ

“ቤተሰቦቻችን እና ቤታችን በፍቅር፣ እንዲሁ ለእርስ በራር በሚገኝ ፍቅር፣ በወንጌል ፍቅር፣ ለሰዎች በሚሰማን ፍቅር፣ እና ለአዳኝ ባለንፍቅር ይሞሉ። በዚህም ውጤት፣ ሰማይ ወደ ምድር በትንሽም ትቀርባለች።

“ቤቶቻችንን የቤተሰብ አባሎቻችን ለመመለስ እንደ ሚፈልጉበት መሸሸጊያ እናድርጋቸው።”6

ለቤተሰቦች ጸሎት

“ቤተሰብ በአለም ውስጥ እየተጠቃ እያለ፣ እና ለረጅም ጊዜ እንደ ቅዱስ ይመለከቱት የነበሩት ብዙ ነገሮች የሚሳለቁባቸው እየሆኑ እያሉ፣ አባታችን ሆይ፣ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ለመቋቋም እንድንችል፣ ለእውነት እና ለጻድቅነት በጥንካሬ ለመቆም እንድንችል እንድታደርግ እንጠይቅሀለን። ቤቶቻችን የሰላም፣ የፍቅር እና የመንፈሳዊነት መጠለያ ይሁኑ።”7

ማስታወሻዎች

  1. “A Sanctuary from the World,” Worldwide Leadership Training Meeting, ጥቅምት 9፣ 2008, 29

  2. “በጉዞው ደስታ” (Brigham Young University Women’s Conference፣ ግንቦት 2፣ 2008) http://ce.byu.edu/cw/womensconference/archive/transcripts.cfm

  3. “በምትረፍረፍ የተባረከ” Liahona, ግንቦት 2008፣ 112

  4. “እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ፣” Liahona, ግንቦት 2009, 113

  5. “በጉዞው ደስታን ማግኘት፣” Liahona, ህዳር 2008, 86

  6. “ከአለም መጠለያ” 30–31

  7. ለጊላ ቫሊ የአሪዞና ቤተመቅደስ የመቀደሻ ጸሎት፣ ግንቦት 23፣ 2010፤ “The Gila Valley Arizona Temple: ‘Wilt Thou Hallow This House,’” ውስጥ Church News, May 29, 2010, 5

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

“ስለሚሳተፉበት በማሰብ፣ አስተማሪው ጥያቄ ወይም ጉዳይ ያቀርባል እናም ለተማሪው መፍትሄ ወይም ሀሳብ እንዲያቀርብ አጭር ጊዜ ይሰጠዋል” (Teaching, No Greater Call [1999]፣ 160) ይህን አንቀጽ ከቤተሰብ ጋር አብራችሁ ስታነቡ፣ የሚያነሳሳቸውን ምክር ወይም ሀሳብ እንዲያዳምጡ ጠይቋቸው። የቤተሰብ አባላት ከእዚያም በኋላ በቤታቸው ፍቅር የሚያሳድጉበትን መንገዶች ሀሳብ ለማቅረብ ይችላሉ። እነዚህን ሀሳቦች በሚቀጥለው በቤተሰብ ምሽት እንዲገመግሟቸው ለመጋበዝ አስቡበት።

አትም