ልጆች
መልሶችን በአጠቃላይ ጉባኤ ለማግኘት እችላለሁ
ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ እንዲህ አስተምረዋል፣ ከአጠቃላይ ጉባኤ በፊት አንዳንድ ጥያቄዎች ካሰባችሁ፣ ጌታ በአጠቃላይ ጉባኤ በነቢያቱ እና በሐዋሪያቱ በኩል ያነጋግራችኋል።
-
እንደ ቤተሰብ እና ክፍል፣ በግለሰብም ይሁን አብራችሁ ምን መማር የሚያስፈልጓችሁን ተወያዩበት። (ለምሳሌ፥ ምስክሬን እንዴት ለማጠናከር እችላለሁ? በትምህርት ቤት ባሉኝ ችግሮች እንዴት ለመቋቋም እችላለሁ?) በወረቀት ላይ ወይም በማስታወሻችሁ ላይ ጥያቄዎቻችሁን ጻፉ።
-
ከጉባኤው ከሳምንቶች በፊት ፣ ስለእነዚህ ጥያቄዎች ለማሰብና ለመጸለይ ትችላላችሁ።
-
በጉባኤም ጊዜ ቨጥንቃቄ አዳምጡ (ማስታወሻ መጻፍም ይረዳል)። ከእዚያም ጌታ—በቤተክርስቲያኗ መሪዎች በኩል—እንዴት ጥያቄዎቻችሁን እንደመለሰ ጻፉ።
-
በሌላ ወረቀት ላይ የተማራችሁትን ስታደርጉ የሚያሳይ ስዕለመሳል ትችላላችሁ።