የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት
መስፈሳዊነትን በማሳደግ ቤተሰቦችን ማጠናከር
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ጁሊ ቢ ቤክ እንዳሉት፥ “በውስጤ ስለእግዚአብሔር ሴት ልጆች ዋጋ የሚያጥለቀልቅ ምስክር አድጓል። … ከዚህ በላይ ሆኖ የሚያስፈልግ የእምነት እና የግል ጻድቃዊነት ማሳደግ እንዳልነበረ ይሰማኛል። ከዚህ በላይ ሆኖ በጣም የሚያስፈልግ ጠንካራ ቤተሰቦች እና ቤቶች አልነበሩም።”
እህቶች የግል ራዕያቸውን ሲጠቀሙ ጠንካራ ቤት እና ቤተሰብ ለመስራት ለመርዳት ይችላሉ። እህት ቤክም እንዲህ ቀጠሉ፣ “ለግል ራዕይ ብቁ መሆን፣ ይህን መቀበል፣ እናም መጠቀም በእዚህ ህይወት ለማግኘት ከሚችሉት ችሎታዎች ሁሉ በላይ በጣም” አስፈላጊ የሆነው ነው። “ለጌታ መንፈስ ብቁ መሆን የሚጀምረው ለእዚያ መንፈስ ፍላጎት ሲኖር ነው እና ይህም የብቁነት ደረጃን ያመለክታል። ትእዛዛትን ማክበር፣ ንስሀ መግባት፣ እና በጥምቀት የተገቡትን ቃል ኪዳኖች ማሳደስ የጌታ መንፈስ ከእኛ ጋር ሁልጊዜ እንዲገኝ ወደሚያደርግ በረከት ይመራል። ወደ ቤተመቅደስ ቃል ኪዳን መግባት እና ማክበርም የመንፈስ ጥንካሬን እና ሀይልን ወደ ሴት ህይወት ይጨምራል። ለአስቸጋሪ ጥያቄዎች መልስ የሚገኙት ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ ነው ምክንያቱም ቅዱሳት መጻህፍት የራዕይ ረጂ ናቸውና። … በየቀን መጸለይም የጌታ መንፈስ ከእኛ ጋር እንዲሆን ለማድረግ አስፈላጊ ነው።”1
የቤተሰብ አባሎቻችን የሰማይ አባትን ዘለአለማዊ አላማ እንዲገባቸው በማድረግ በመንፈስ ለማጠናከር እንችላለን። “ልጆቻችንን ለዘለአለማዊ ሀላፊነቶች በመንፈሳዊነት ለማዘጋጀት ምን ማድረግ እንችላለን?” ብለው የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ኤም ራስል ባለርድ ጠየቁ። “ምናልባት ሁሉንም የሚሸፍን መልስ ቢኖር፥ በወንጌል መሰረታዊ መመሪያዎች እንዴት እንዲሚኖሩ ማስተማር ነው።” ይህም ትምህርት የሚመጣው በየቀኑ በመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ፣ እና አብሮ እንደ ቤተሰብ በመመገብ፣ በቤተሰብ የቤት ምሽትና በቤተክርስቲያን በመሳተፍ ነው። ሽማግሌ ባለርድ እንደገለጹት፥ “በእያንዳንዱ ቀን፣ አሁንም፣ ለዘለአለም ህይወት እንዘጋጃለን። ለዘለአለም ህይወት ካልተዘጋጀን፣ ከዚህ በታች ለሚሆን ነገር፣ ምናልባትም ከዚህ በጣም ለሚያንስ ነገር እንዘጋጃለኝ።”2
ከቅዱስ መጻህፍት
ምሳሌ 22:6; 1 ዮሀንስ 3:22; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 11:13–14; 19:38; 68:25
ከታሪካችን
በሚያዝያ 1842 (እ.አ.አ) የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ውስጥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እህቶችን የእራሳቸውን ደህንነት የመፈለግ ጥብቅ ሀላፊነት እንዳላቸው አስተማራቸው። እንዲህም አለ፣ “ከማስተምራችሁ በኋላ፣ ለእራሳችሁ ሀጢያት ሀላፊ ትሆናላችሁ፤ በሰማይ አባታችን ፊት እራሳችሁን ለማዳን እንዲህ መራመዳችሁ የሚያስፈልግ ክብር ነው፤ በጌታችን እራሳችንን ለማዳን እንዲያስችለን የሚሰጠንን ብርሀን እና ጥበብ ለምናሻሽልበት መንገድ ሁላችንም ሀላፊዎች ነን።”3 ጻድቅ ግለሰቦች እንዲሆኑ፣ ቅዱስ ህዝቦች እንድሆኑ፣ እና ለቤተሰብ ስነስርዓቶችና ቃል ኪዳኖች እንዲዘጋጁ አስተማራቸው።
© 2011 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, September 2011 ትርጉም Ahmaric 09769 506