2011 (እ.አ.አ)
አጠቃላይ ጉባኤ—ልዩ የሆነ በረከት
ሴፕቴምበር 2011


የቀዳሚ አመራር መልእክት

አጠቃላይ ጉባኤ—ልዩ የሆነ በረከት

አንድ ጥሩ የቤተክርስቲያን አባል የእኛ እምነት አባል ካልሆነ ጎረቤት ጋር ይነጋገር ነበር። የንግግር ርዕሱ ወደ አጠቃላይ ጉባኤ ሲቀየር፣ ጎረቤቱ እንዲህ ጠየቀ፣ “ነቢያት እና ሐዋሪያት አሉን ትላለህ? በአመት ሁለት ጊዜም በአለም አቀፍ ጉባኤ የእግዚአብሔርን ቃል ይገልጻሉ?”

አባሉም በልበሙሉነት “ያለጥርጣሬ” ብሎ መለሰ።

ጎረቤቱም ስለዚህ ለትንሽ ጊዜ አሰበ። በቅንነት ለአወቅ የሚፈልግ ይመስል ነበር እና ከእዚያም፣ “ባለፈው የአጠቃላይ ጉባኤ ምን አሉ? ብሎ ጠየቀ።”

በዚህ ጊዜ ጥሩው የቤተክርስቲያኗ አባል ስሜታ ወንጌሉን ለመካፈው ከመደሰት ወደ እፍረት ስሜታ ተቀየረ። በምንም ቢሞክር፣ የአንድ ንግግርን ዝርዝር ለማስታወስ አልቻለም።

ጓደኛው ይህም እንዲረበሽ አደረገው እና እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር ለሰው ይናገራም እናም አንተ ምን እንዳለ አታስታውስል ትነኛለህ?”

ይህ ወንድምም በዚህ ንግግር ትህትና ተሰማው። በአጠቃላይ ጉባኤ በጌታ አገልጋዮች የሚናአገሩትን ቃላት ለማስትወስ ቃል ገባ።

እያንዳንዱን የአጠቃላይ ጉባኤ ለማስታወስ የሚያስሸግር እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፣ እናም ሁሉንም ለማስታወስ ስለማንችል ማፈር አያስፈገንም። ይህም ቢሆን፣ በእያንዳንዱ አጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ እንደ ስጦታ እና ከሰማይ ለግል የህይወት ጉዳያችን እንደ በረከት የሚሰጡ መልእክቶች አሉ።

ለአጠቃላይ ጉባኤ ለመዘጋጀት፣ በጌታ አገልጋይ የሚንነገሩንን ቃላት ለመቀበል፣ ለማስታወስ፣ እና ፤እመጠቀም የሚረዱን ሶስት መሰረታዊ መመሪያዎችን በሀሳብ ላቅርብ።

1. በአጠቃላይ ጉባኤ የሚነገሩትን ቃላይ ሲያዳምጡ እና ስይስጠኑ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ አባላት ለግል ራዕይ መብት አላቸው።

ለአጠቃላይ ጉባኤ ስትዘጋጁ፣ መልስ ለማግኘት የምትፈልጓቸውን እንድታሰላስሉ እጋብዛችኋለሁ። ለምሳሌ፣ ፈተና በሚያጋጥማችሁ ነገሮች ላይ የጌታን መመሪያ ለማግኘት ትፈልጉ ይሆናል።

ለጸሎታችሁ መልስ በቀጥታ ከአንድ ንግግር ወይም ከአንድ ሀረግ ሊመጣ ይችላል። በሌሎች ጊዜዎችም መልሶች የሚገናኙበት በማይታይ ቃል፣ ሀረግ፣ ወይም መዝሙር በኩል ሊመጣም ይችላል። በህይወት በረከቶች የተሞላ እና የምክር ቃላትን ለማዳመጥ እና ለከመተል ጥብቅ ፍላጎት ያለው ልብ ለግል ራዕይ መንገድን ያዘጋጃል።

2. መልእክቱ በፊት የምታውቁት ቢመስልም ችላ አትበሉት።

ነቢያት ሁልጊዜም የሚያስተምሩት በመደጋገም ነው፤ ይህም የመማር ህግ ነው። በአጠቃላይ ጉባኤ ውስጥ የሚደጋገሙ ጭብጥ መልእክቶች እና ትምህርቶችን ትሰማላችሁ። ማረጋገጫ ልስጣሁ፥ ይህ አዲስ ነገሮችን ለመፍጠር በአይነ ህሊና የማይት ችሎታ ስላጡ አይደለም። ወደ ሌሎች ነገሮች ከመሄዳችን በፊት መገባት እና መደረግ የሚያስፈልጋቸው ታላቅ ዘለአለማዊ ነገሮችን መሰረታዊ መመሪያ በአዕምሮአችን እና በልባችን ላይ ለማስተኮር እና ለማስተማር ጌታ በመፈለጉ ምክንያት ነው በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ መልእክቶችን ለማዳመጥ የምንቀጥለው። ጥበባዊ ገንቢ ግድግዳውን እና ጣራውን ከመስራቱ በፊት መጀመሪያ መሰረቱን ይመሰርታል።

3. በአጠዋላይ ጉባኤ የሚናገሩት ቃላት በሚቀጥሉት ወሮች መንገድን የሚያመለክቱን የአቅጣጫ መለያ መሳሪያችን ሊሆኑ ይገባቸውል።

የመንፈስ መነሳሻን ካዳመጥን እና ከተከተልን፣ ወደፊታችን ያሉትን ሸለቆዎች እና ተራራዎች በመቋቋም፣ በማይታወቀው ውስጥ መርተውን እንደምናልፍበት ሊያሆና ያገለግሉናል፣ (1 ኔፊ 16 ተመልከቱ)

አለም ከተፈጠረች ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር ለጊዜአቸ ሀዎች የሰማይን ፍላጎት የሚናገሩ ነቢያት ጠርቷል። ማዳመጥ እና ከእዚያም ጌታ የሰጠንን መልእክቶች የመጠቀም ሀላፊነት የእኛ ነው።

ምሀሪውና አፍቃሪው የሰማይ አባታችን ልጁቹን አልካደም እናም አይክዳቸውም። ዛሬ፣ እንደ ድሮም፣ ሐዋሪያትን እና ነቢያትን መድቧል። ቃላቱን ለእነርሱ መግለጥን ቀጥሏል።

በአጠቃላይ ጉባኤ ለእያንዳንዳችን ያለውን የእግዚአብሔር መልእክት ለመስማት የምንችልበት ምን አይነት አስደናቂ አድል ነው። በአገልጋዮቹ ለሚመጣው ለዚህ ታላቅ በረከት ለሆነው መለኮታዊ መመሪያ እራሳችንን እናዘጋጅ።

ይህም ልዩ የሆነ በረከት ነውና።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

  • አንቅጹን አብራችሁ አንብቡ። ቤተሰብ በአጠቃላይ ጉባኤ ሊያዳምጡ የሚፈልጉትን እንዲያስቡብዳቸው አበረታቷቸው።

  • በፕሬዘደንት ኡክዶርፍ የተሰጡትን ምክሮች ትንሽ ልጆች እንዲጠቀሙበት ለመርዳት፣ የአጠቃላይ ጉባኤ መዝገብን አሳዩአቸው (ይህም በጉባኤ በሚታተመው ሊያሆና ውስጥ ይገኛል) ቀዳሚ አመራር እን የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን በአጠቃላይ ጉባኤ እንደሚናገሩ አሳውቋቸው። ልጆች ጉባኤን እንዲያዳምጡ እና የተማሩትን እንዲያስታውሱ እንዲረዳቸው ስዕል እንዲስሉ አበረታቷቸው። ወላጆች ልጆች ለማድረግ ለሚችሏቸው ነገሮች conferencegames.lds.org ይጎበኙ።

ቀኝ፥ በለስ ኒልሰን የተነሳ ፎቶ

አትም