2011 (እ.አ.አ)
ጥሩ፣ የሚሻል፣ ምርጥ
ሴፕቴምበር 2011


ወጣቶች

ጥሩ፣ የተሻለ፣ ምርጥ

በጥቅምት 2007 (እ.አ.አ) የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግራቸው፣ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ካህን ዳለን ኤች ኦክስ “ጥሩ፣ የተሻለ፣ እና ምርጥ” ስለሆኑ ተሳታፊ ስለሚደረጉበት ነገሮች ተናገሩ። “ልጆችን ከሚችሉት በላይ ቀጠሮ ስለማድረግ” በሚናገሩበት ጊዜ፣ በተቀመጥኩበት በጥፋተኛነት ስሜታ መስመስመስ ጀመርኩኝ።

ብዛ እያደርግሁኝ እንደሆንኩኝ አውቀው ነበር። በትምህርት ቤት ድራማ ተስታፊ፣ የሚያስቸግሩ ክፍሎችን በትምህርት ቤት የምወስድ፣ እና በተለያዩ ሌሎች ስራዎች ተሳታፊ ነበርኩኝ። የወጣት ሴቶች ስብሰባን በየጊዜው እሳተፍበት ነበር፣ እናም እሁዶቼም የመጨረሻ የትምህርት ስራዎቼን ለመጨረስ የታገልበት ጊዜ ነበር። ሙዚቃን መለማመድ እና የትምህርት ቤትን ጋዜጣ ማረም የሚያስደስቱ ሳይሆን ስራዎች ሆነው ነበር።

የካህን ኦክስ ንግግር ቀጠሮዬን በትኩረት እንድመለከት አደረገኝ። የምሳተፍባቸው ጥሩ ነበር፣ ነገር ግን በጣም ብዙ ነበሩ። ከሁሉም ምርጥ የሚሆነውን መምረጥ ነበረብኝ። ከምሳተፍበት መካከል የትኛውን እንደምተው ለመወሰን ሳስብ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለማንም ሰው ከሁሉም ይበልጥ ጠቃሚ እንደሆነ ገባኝ። ጸሎትን እና ቅዱስ መጻህፍትን ማንበብ ከዘረዘርኳቸው ነገሮች በላይ አደረግኳቸው፣ እናም ከእዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ ህይወቴ ያለችግር ይሄድ ነበር።

ካህን ኦክስ ጌታ እንድናደርግ የሚፈልገንን መጀመሪያ በመጀመሪያ ስናደርግ፣ ሁሉም ነገሮች በቦታቸው በቀጥታ እንደሚገቡ አስተማሩኝ። ከመጫወቴ በፊት ወይም የቤት ስራን ከመስራቴ በፊት ቅዱሳት መጻህፍቴን ካጠናሁ፣ አስፈላጊ የሆነው ነገር በሙሉ ይከናወናል። እርሱን በሃላ በማሰብ ወደ ህይወቴ ከመጨመር ይልቅ ህይወቴን በጌታ ላይ ስመሰርት፣ ህይወቴ ተጨማሪ ሰላም እና ውጤታማነት አለው።

አሁን በአጠቃላይ ጉባኤ የሚሰጠውን ምክር በጥብቅ አዳምጣለሁ።

ስዕሉ የተሳለው በፖል ማን ነው።