የሴቶች የቤት ለቤት መልእክት፣ ታህሳስ 2011 (እ.አ.አ)
ተፅዕኖ ያለበት ታላቅ ቦታ
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
ጌታ፣ ቤተክርስቲያኑ፣ ቤተሰቦች፣ እና ህብረተሰቦች የጻድቅ ሴቶች ተፅዕኖ ያስፈልጋቸዋል። በእርግጥም፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ካህን ኤም ራስል ባለርድ እንዳስተማሩት፣ “በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን የገባች እያንዳንዷ እህት እያንዳንዱን መንፈስ ለመርዳት፣ የአለም ሴቶችን ለመምራት፣ የፅዮን ቤቶችን ለማጠናከር፣ እና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት መለኮታዊ ሀላፊነት አላት።”1
አንዳንድ እህቶች እንደዚህ አይነት ታላቅ አላማን ለማከናወን እንደሚችሉ ያስባሉ። ነገር ግን ሁለተኛዋ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እላይዛ አር ስኖው እንደገለጹት፣ “እህት በብቸኛነት ያለችበት እና ተፅዕኖ ያለባት ቦታ ታናሽ የሆነበር ቦታ ሳይኖር የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ለመመስረት ልታደርገው የምትችላቸው ታላቅ ነገሮች አሉ።”2 እህት ስኖው ደግመውም የሴቶች መረዳጃ ማህበር የተመሰረተችው “መልካም የሆኑትን እና ልዑል ስራዎችን ሁሉ ልማከናወን ነው።”3
በሴቶች መረዳጃ ማህበር መሳተፍ እያንዳንዷን እህት እምነቷን ለመገንባት፣ ቤተሰቦችንና ቤቶችን ለማጠናከር፣ እናም በቤት እና በአለም ሁሉ ለማገልገል እድል በመስጠት ተፅዕኖ ሊኖረን የምትችልበትን ቦታዎች ታስፋፋለች። ጥሩ አጋጣሚ ሆኖም፣ በግለሰብ እና እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር የምንጥርበት ታላቅ ወይም የሚያጥለቀልቅ መሆን አያስፈልገውም፣ ነገር ግን የታሰቢበትና የተደጋገሙ መሆን አለባቸው። እንደየቀኑ እና እንደ ቤተሰብ ጸሎት፣ እንደየቀኑ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ እና በየጊዜው የቤተክርስቲያን ጥሪን እንደማጉላት አይነት ጻድቅ ስራዎች እምነትን ለመጨመር እና የጌታን መንግስት ለመገንባት እርዳታ ይሰጣሉ።
እነዚህ ጸጥተኛ ተሳታፊነት ለውጥ እንደሚያመቱ ለሚያስቡት፣ ሽማግሌ ባለርድ እንዳረጋገጡት፣ “ለእውነት እና ለጻድቅነት የምትቆም እያንዳንዷ እህት የክፉን ተጽዕኖ ትቀንሳለች። ቤተሰቧን የምታጠናክር እያንዳንዷ እህት የእግዚአብሔርን ስራ እየሰራች ነች። እንደ እግዚአብሔር ሴት የምትኖር እያንዳንዷ ሴት ሌሎች የሚከተሏት ምልክት ትሆናለች እናም ለብዙ አመቶች የሚሰበሰቡ የጻድቅ ተፅዕኖ ዘርን ትተክላላች።”4
ከቅዱሳት መጻህፍት
ከታሪካችን
የሴቶች መረዳጃ ማህበር በናቩ በተደራጀበት ጊዜ እንደ ጸሀፊ ያገለገሉት እላይዛ አር ስኖው፣ በፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ (1801–77) በቤተክርስቲያኗ በሙሉ በመጓዝ በዎርዳቸው የሴቶች መረዳጃ ማህበርን ለማደራጀት ኤጲስ ቆጶሶችን እንዲረዱ ጠርተዋቸው ነበር።
እህት ስኖው እንዳስተማሩት፥ “ማንኛዎቹም የእስራኤል ሴት ልጆች እና እናቶች ተፅዕኑ ባላቸው የተገደቡ እንደሆኑ ቢሰማቸው፣ ለሀይሎች በሙሉ እና በደንብ በመንፈስ በረከት በተሰጣቸው መልካም ለማድረግ ብቁ ችሎታ ያገኛሉ። …ፕሬዘደንት ያንግ ለታላቅ እና የተዘረጋ የስራ እና የጠቃሚነት ተፅዕኖ ያለበት ታላቅ ቦታን ከፍተዋል።”5
© 2011 በIntellectual Reserve, Inc። መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/10 (እ.አ.አ)። Visiting Teaching Message, December 2011 (እ.አ.አ) Amharic። 09772 506