2011 (እ.አ.አ)
ምስጋና እንዲሰማን የምንመርጥበት
ዲሴምበር 2011


የቀዳሚ አመራ መልእክት፣ ታህሳስ 2011 (እ.ዓ.ዓ)

ምስጋና እንዲሰማን የምንመርጥበት

ምስል
በፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ

የሰማይ አባታችን በሁሉም ነገሮች ምስጋና እንድናቀርብ አዝዞናል (1 ተሰሎንቄ 5፥18 ተመልከቱ)፣ እናም ለምንቀበለው በረከቶች ምስጋና እንድናቀርብም ይጠብቅብናል (ት. እና ቃ. 46፥32 ተመልከቱ)። ትእዛዛቱ በሙሉ እኛን ደስተኛ ለማድረግ እንደተሰጡ እናውቃለን፣ ደግሞም ትእዛዛትን መስበር ወደ ስቃይ እንደሚመራ እናውቃለን።

ስለዚህ ደስተኛ ለመሆን እና ስቃይን ለማስወገድ፣ ምስጋና ያለው ልብ ያስፈልገናል። በህይወታችን ውስጥ በምስጋና እና በደስታ መካከል ያለውን ግንኙነት ተመልክተናል። ሁላችንም ምስጋና እንዲሰማን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን በህይወት ፈተናዎች ውስጥ፡በሁሉም ነገሮች ሁልጊዜም ምስጋና እንዲኖረን ለማድረግ ቀላል አይደለም። በሽታ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ እናም የምናፈቅራቸውን ሰዎች ማጣት ወደ ህወታችን የሚመጡበት ጊዜዎች አሉ። ሀዘናችን በረከታችንን ለመመልከትና ወደፊት እግዚአብሔር ያከማቸልንን በረከቶች በምስጋና ለመመልከት አስቸጋሪ ያደርገዋል።

መልካም ነገሮችን በችለኛነት የመመልከት ልምድ ስላለን በረከቶቻችንን ለመቁጠር አስቸጋሪም ነው። ቤታችንን፣ የምንመገበውን ምግብ፣ ወይም የጓደኞችንና የቤተሰብን ቅርብነት ስናጣ፣ ሲኖሩን እንዴት ምስጋና ማቅረብ እንደነበረብን ይገባናል።

ከሁሉም በላይ፣ አንዳንዴ ከሁሉም በላይ ታላቅ ለሆነው ስጦታ፣ እንዲሁም ለኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ለኃጢያት ክፍያው፣ ለትንሳኤ የተስፋ ቃል፣ የዘለአለም ህይወትን ከቤተሰቦቻችን ጋለ ለምንደሰትበት እድል፣ ከክህነት ስልጣንና ቁልፎችይ ጋር ለወንጌል ዳግም መመለስ በብቁ ምስጋና ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው። እነዚያ በረከቶች ለእኛና ለምናፈቅራቸው ምን ትርጉም እንዳላቸው ሊሰማን የምንጀምረው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብቻ ነው። በዚህም ጊዜ ብቻ ነው በሁሉም ነገሮች ምስጋና እንዲኖረን እና የምስጋና አምላክን ማስቀየምን የማስወገድ ተስፋ የሚኖረን።

እግዚአብሔር፣ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል፣ በፈተናዎቻችን መካከል በረከቶቻችንን በግልፅ እንዳይ እንዲረዳን በጸሎት መጠየቅ ይገባናል። በመንፈስ ሀይል ችላ የምንላቸውን በረከቶች እንድናውቅና ምስጋና እንዲሰማን ይረዳናል። ከሁሉም በላይ የረዳኝ ቢኖር እግዚአብሔርን በጸሎት “ለአንተ ወደምረዳው አንድ ሰው ልትመራኝ ትችላለህ?” ብሎ መጠየቅ ነው። የእራሴን በረከቶች በግልፅ ለመመልከት የቻልኩት ሌሎችን እግዚአብሔር እንዲባርካቸው በመርዳት ነው።

አንድ ጊዜ ጸሎቴ የተመለሰው የማላውቃቸው ባልና ሚስት ወደ ሆስፒታል አብሬአቸው እንድሄድ ሲጋብዙኝ ነው። በእዚያም በጣም ትንሽ ሆና እጄን የምታክል ህጻን አገኘሁ። በትንሽ የህይወት ሳምንቷ፣ ብዙ ቀዶ ጥገና ነበረባት። ዶክተሮችም ይህችን ትንሽ የእግዚአብሔር ልጅ ህይወት ለማዳን ከሁሉም በላይ አስቸጋሪ የሆነው ቀዶ ጥገና ለልቧና ለሳምባዋ እንደሆነ ለወላጆቿ ነግረው ነበር።

ወላጆቿ ጠይቀውኝ፣ ለህጻኗ የክህነት በረከት ሰጠኋት። በረከቱም የረዘመ ህይወት እንደሚኖራት በተጨማሪ የተናገረ ነበረ። በረከት ከመስጠት በላይ፣ ምስጋና ያለው ልብ በረከትም ለእራሴ የቀበልኩኝ።

በአባታችነርዳታ፣ ሁላችንም ተጨማሪ ምስጋና ሊሰማን እንችላለን። ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ በረከቶቻችንን በግልፅ ለመመልከት እንድንችል እንዲረዳል ልንጠይቀው እንችላለን። በእዚያ ቀን ለእኔ ለልቤና ለሳንባዬ ከእዚህ በፊት ያልነበረኝ ምስጋና ተሰማኝ። ወደቤት ስሄፍም በግልፅ ለሚታየኝ ከእግዚአብሔርና በአካባቢያቸው ከሚገኙት ለነበሩት የደግነት ታዕምራት ለሆኑት የልጆቼ በረከቶች ምስጋናም አቀረብኩኝ።

ከሁሉም በላይ፣ በሚጨነቁት ወላጆችና በእኔ ህይወት ላይ ይሰራ ስለነበረው የኃጢያት ክፍያ ምስጋና ተሰማኝ። በጣም አስቸጋሪ በሆነው ፈተናቸው መካከልም፣ ተስፋና የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር በፊታቸው ሲበራ አይቻለሁ። የኃጢያት ክፍያው ተስፋና ፍቅር ለመሰማት እንደሚፈቅድላችሁ እግዚአብሔር እንዲገልጽላችሁ ከጠየቃችሁ እንደሚሰማችሁ ማረጋገጫም ተሰማኝ።

ሁላችንም በጸሎት ምስጋና የመስጠትና፣ በልዩም የአዳኝ ልደትን በምናከብርበት ዘመን፣ ለእርሱ ሌሎችን ለማገልገል እግዚአብሔርን መመሪያ ለመጠየቅ መምረጥ እንችላለን። እግዚአብሔር አብ ልጁን ሰጠ፣ እናም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁሉም ስጦታዎች እና ከሚሰጡት ሁሉ ታላቅ የሆነውን ስጦታ ሰጠ (ት እና ቃ 14:7 ተመልከቱ)።

በጸሎት ምስጋና ማቅረብ የእነዚህ በረከቶች እናም ሌሎቹ በረከቶቻችን ሁሉ ታላቅነትን ለመመልከት እንድንችል እና በታላቅ አመስጋኝ ልብ ስጦታን እንድንቀበል ይረዳናል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

አጋጣሚዎቻችንን እና በረከቶቻችንን መጻፍ እንድናስታውሳቸው እና በኋላም በትዝታ የምንመለከታቸው ነፈሮች ይሰጡናል። የተቀበሉትን በረከቶች እንዲያስታውሱ፣ የአሁኑን በረከቶች እንዲያውቁ፣ እና የወደፊት በረከቶችን በጉጉት እንዲጠብቁ እነርሱን እንዲረዳቸው፣ የምታስተምሯቸውን ምስጋና ስለሚሰማቸው ነገሮች እንዲጽፉ ጠይቁ።

የምታስተምሯቸውንም የሰማይ አባትን ለመርዳት እና ለማገልገል ለሚችሉት ሰው እንዲመራቸው የመጠየቅን የፕሬዘደንት አይሪንግን ምሳሌ እንዲከተሉ አበረታቷቸው።

አትም