2012 (እ.አ.አ)
የእምነት ጸሎቴ
ፌብሩወሪ 2012


ወጣቶች

የእምነት ጸሎቴ

በ18 አመቴ፣ የቤት እቃ በሚሸጥበት እንደ አሻሻጭ እሰራ ነበር። የስራ መርሀ ግብሬ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ፣ ከጠዋት 2 ሰዓት እስከ ምሽት 4 ሰአት እሰራ ነበር። በኢንስትቲዩት ወይም በቤተክርስቲያን መሳተፊያዎች ለመካፈል ስለማልችል ይከፋኝ ነበር።

በኢንስትቲዩት ወይም በቤተክርስቲያን መሳተፊያ ተካፋል ለመሆን በቅዳሜ የማልሰራበት ስራ እንዳገኝ እርሱ እንዲረዳኝ ለሰማይ አባት በብዙ እምነት መጸለይ ጀመርኩኝ።

አንድ ቀን በስራ እያለሁ አንድ ሰውን እረዳ ነበር። መነጋገር ጀመርን እና እርሱም በትልቅ ባንክ ውስጥ እንደሚሰራ ነገረኝ። እርሱ በሚሰራበት ለሚገኘው ስራ ለማግኘት እንዴት እንደምችል ጠየቅኩት። ስሙን እና የስልክ ቁጥሩን ነገረኝ እናም ሰራተኛ የሚፈልገውን ሰው ለመጥራት እንደምችል እናም እርሱን እንደማውቀው እንድነግረው ነገረኝ። ወደ ባንኩ ሄድኩኝ እና አስፈላጊ የሆነውን ፈተና ወሰድኩኝ። አለፍኩኝ እና ከሰኞ እስከ አርብ በቀን ለስድስት ሰአት መስራት ጀመርኩኝ፣ በእዚህም በፊት ከማገኘው ደምዎች ከሶስት እጥፍ በላይ አገኝ ነበር።

ጌታ እርሱን በመጀመሪያ ለማድረግ ፍላጎት ሲኖረን እንደሚመራን አውቃለሁ። አሁንም ይመራኛል። የጸሎት መሰረታዊ መርሆ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ።

አትም