2012 (እ.አ.አ)
እንዲጸልዩ አበረታቷቸው
ፌብሩወሪ 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የየካቲት 2012 (እ.አ.አ)

እንዲጸልዩ አበረታቷቸው

ትንሽ ልጅ እያለሁ፣ ወላጆቼ በምሳሌ እንድጸልይ አስተማሩኝ። የሰማይ አባት ሩቅ እንደሆነ በአዕምሮዬ እያየሁ ነበር የጀመርኩት። ሳድግም፣ በጸሎት የነበረኝ አዳጣሚ ተቀየረ። በአዕምሮዬ የነበረው የሰማይ አባት አስተያየት ቅርብ የሆነ፣ ብርቅ በሆነ ብርሀን የተሸፈነ፣ እና በፍጹም የሚያውቀኝ አይነት እንደሆነ ተቀየረ።

በ1820 (እ.አ.አ) በማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ ውስጥ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳጋጠመው የተናገረው እውነት እንደሆነ እርግጠኛ የሆነ ምስክርነት ሳገኝ ነበር ያው ለውጥ የመጣው፥

“ከፀሀይ በላይ የደመቀ ሀየብርሀን አምድ ከራሴ በላይ አየሁ፣ በእኔ ላይ እስኪያርፍ ድረስ ይህም በቀስታ ወደእኔ ወረደ።

“ወዲያው እንደታየም ይዞኝ ከነበረው ጠላት ሀይል በመዳን ነጻ ሆንኩኝ። ብርሀኑም በእኔ ላይ ባበራም ጊዜ ብርሀናቸውና ክብራቸው የሚገለጽበት ሁሉ ብቁ ያልሆነ ሁለት ሰዎች በአየር ከእኔ በላይ ቆመው አየሁ። አንዱም ስሜን በመጥራት እና ወደሌላው በማስመልከት አናገረኝ—ይህ ውድ ልጄ ነው። አድምጠው!” (ጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥16–14)።

በእዚያ አስደናቂ የጸደይ ቀን የሰማይ አባት በጥሻ ውስጥ ነበር። ጆሴፍን በስም ጠራው። እናም ከሞት የተነሳውን የአለም አዳኝ እንደ “ውድ ልጄ” አስተዋወቀው። መቼም እና የትም ስትጸልዩ፣ የእዚያ አስደናቂ አጋጣሚ እውነተኛነት ምስክራችሁ ሊባርካችሁ ይችላል።

የምንጸልይለት አባት በውድ ልጁ በኩል አለሞችን የፈጠረው አስደናቂው እግዚአብሔር ነው። የጆሴፍን ጸሎት እንዳዳመጠው በፊቱ እንደሚቀርቡ አይነት ግልፅ እንደሆኑ አይነት የእኛንም ጸሎት ያዳምጣል። በጣም አፍቅሮን ልጁን እንደ አዳኛችን ሰጠን። በእዚያ ስጦታ አለሟችነትን እና ዘለአለማዊነትን እንድናገኝ እንድንችል አደረገልን። እናም በልጁ ስም በመጸለይ፣ በእዚህ ህይወት ከእርሱ ጋር በምንመርጥበት ሁኔታ የምንነጋገርበት እድል ይሰጠናል።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የክህነት ባለስልጣኖች “የእያንዳንዱን አባል ቤትን መጎብኘት፣ እናም በሚስጥር እና በድምፅ እንዲጸልዩ በጥብቅ ማበረታት” ቅዱስ ሀላፊነት አላቸው (D&C 20:47፤ ትኩረቱ የተጨመረበት ነው)።

አንድ ሰው እንዲጸልይ የምናበረታታበት ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር እንድንጸልይ እንዳዘዘን ለመመስከር እንችላለን፣ ወይም ከቅዱሳት መጻህፍት እና በምስጋና፣ በልመና፣ እና በጥያቄ በምንጸልይበት ከሚመጡት ከእራሳችን አጋጣሚዎች ምሳሌዎች ለመግለጽ እንችላለን። ለምሳሌ፣ የሰማይ አባት ለጸሎቶች መልስ እንደሚሰጥ እንደማውቅ ለመመስከር እችላለሁ። ወደ አዕምሮዬ የሚመጣ መመሪያ እና ከአለም መፅናኛ ተቀብያለሁ፣ እናም በመንፈስ ቃላቱ የእግዚአብሔር እንደሆኑ አውቃለሁ።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደ እዚህ አይነት አጋጣሚ ነበረው፣ እናም እናንተም ሊኖራችሁ ትችላላችሁ። ይህን መልስ ከልቡ በመጣ ጸሎት ክንያት ተቀብሏል፥

“ልጄ፣ በነፍስህ ሰላም ይኑርህ፤ ጭንቀትህ እና ስቃይህ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ነው፤

“ከእዚያም፣ በመልካም ይህን ከጸናህ፣ እግዚአብሔርም ወደ ላይ ከፍ ያደርግሀል” (D&C 121:7–8)።

ያም ከሚያፈቅር አባት ለታማኝ ልጁ በታላቅ ችግሩ ጊዜ የተሰጠ ራዕይ ነበር። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ይችላል። ለትሁት ጸሎት መልስ ጋር ከመጡት የፍቅር እና የብርሀን ስሜት በላይ እኔን የነካኝ ምንም እንድጸልይ የተበረታታሁበት ነገር የለም።

ያን ትእዛዝ በማክበር ለእግዚአብሔር ማንኛውም ትእዛዝ ምስክርነት ለማግኘት እንችላለን (ዮሀንስ 7፥17 ተመልከቱ)። ይህም በድምፅ እና በሚስጥር መጸለይ አለብን ለሚለው ትእዛዝም እውነት ነው። እንደ አስተአሪያችሁ እና ጓደኛችሁ፣ እግዚአብሔር ጸሎቶቻችሁን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እንደሚመልስ፣ መልሶቹም ከእርሱ እንደሆኑ ለእራሳችሁ ለማወቅ እንደምትችሉ ቃል እገባላችኋለሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

  • “ፎቶዎችና ስዕሎች የትምህርትን ዋና ነጥብ ለማጠናከር ዋጋ ያላቸው መሳሪያዎች ናቸው” (Teaching, No Greater Call [1999]፣ 176)። የጆሴፍ ስሚዝን ወይም የመጀመሪያ ራዕይን ስዕል አሳዩ። ጆሴፍ ስሚዝ ከጸሎት ጋር ስለነበረ አጋጣሚ ተወያዩበት። ፕሬዘደንት አይሪንግ እንዳደረጉት “የሰማይ አባት…ቅርብ እንደሆነ” በአዕምሮአችሁ ከተመለከታችሁ እንዴት ጸሎታችሁ ተጨማሪ ትርጉም ያለው ይሆናል?

  • ፕሬዘደንት አይሪንግሀሳብ እንዳቀረቡት፣ በጸሎት ምክንያት የተቀበላችኋቸውን በረከቶች በመግለጽ፣ ወይም ስለጸሎት የሚናገር ቅዱሳት መጻህፍትን በመካፈል ስለጸሎት ምስክርነታችሁን ለመካፈል አስቡበት።

አትም