2012 (እ.አ.አ)
የቤት ጠባቂዎች
ፌብሩወሪ 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ የካቲት 2011 (እ.አ.አ)

የቤት ጠባቂዎች

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

በ1995 (እ.አ.አ) በአጠቃላይ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ላይ “ቤተሰብ፥ የአለም አማጅን” ሲያስተማውቁ ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ (1910–2008) “የቤት ጠባቂዎች ናችሁ” አሉ። “እናንተ የልጆች ወላጆች ናችሁ። የሚንከባከቧቸው እና በውስጣቸውም የህይወታቸውን ጸባዮች የምትመሰርቱት እናንተ ናችሁ። የእግዚአብሔርን ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ከመንከባከብ በላይ ወደ መለኮነት የሚቀርብ ምንም ሌላ ስራ የለም።”1

አሁን ለ17 አመት ይህ አዋጅ ከሁሉም ታላቅ የሆነውን ሀላፊነታችን—የአሁን ጉዳያችን ምንም ቢሆን —ቤተሰቦችን እና ቤቶችን በማጠናክር ላይ የሚያተኩር እንደሆነ አረጋግጦልናል። አሁን የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር ሁለተኛ አማካሪ የሆኑት ባርብራ ቶምሰን፣ ፕሬዘደንት ሒንክሊ ይህን አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያነቡበት ጊዜ በሶልት ሌክ ታበርናክል ውስጥ ነበሩ። “ያም ታላቅ ጉዳይ ነበር” ብለው ያስታውሳሉ። “የመልእክቱ ታላቅነትም ተሰማኝ። እንዲህም እያልኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ፣ ‘ለወላጆች ይህ ታላቅ መመሪያ ነው። ይህም ለወላጆች የተሰጠ ታላቅ ሀላፊነትም ነው።’ ያላገባሁ ስለሆንኩኝ እና ምንም ልጆች ስላልነበሩኝ ይህ ከእኔ ጋር ብዙ ግንኙነት ያለው አልመሰለኝም ነበር። ነገር ግን ወዲያውም እንዲህ አሰብኩኝ፣ ‘ይህ እኔንም የሚነካ ነው። እኔ የቤተሰብ አባል ነኝ። እኔ የሴት ልጅ፣ እህት፣ አክስት፣ የወንድም ወይም የእህት ልጅ፣ የዘመድ ልጅ፣ እና የልጅ ልጅ ነኝ። የቤተሰብ አጋል ስለሆንኩም ሀላፊነቶች—እናም በረከቶች—አሉኝ። ከቤተሰቤ ከሚኖሩት የመጨረሻው ብሆንም፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል ነኝ፣ እናም ሌሎች ቤተሰቦችን ለማጠናከር ለመርዳት ሀላፊነትም አለኝ።’”

ጥሩእድል ሆኖም፣ በጥረታችን በብቸኛነት አንተውም። “እህት ቶምሰን እንደሚሉት፣ “ቤተሰቦችን በማጠናከር የሚኖረን ታላቅ እርዳታ ቢኖር የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ማወቅ እና መከተል እና እርሱ እንዲረዳን በእርሱ መመካት ነው።”2

ከቅዱሳት መጻህፍት

ምሳሌዎች 22፥61 ኔፊ 1፥12 ኔፊ 25፥26አልማ 56፥46–48ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 93፥40

ከታሪካችን

“እህት በትሺባ ደብሊው ስሚዝ እንደ ሴትፕች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሲያገለግሉ [ከ1901 እስከ 1910 (እ.አ.አ)]፣ ቤተሰቦችን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለ ተመለከቱ፣ እናም ስለዚህ ለሴቶች መረእዳጃ ማህበር የእናቶች ማሰልጠኛ ትምህርትን መሰረቱ። ይህም ትምህርት በተጨማሪ ስለጋብቻ፣ ስለህጻናት እንክብካቤ፣ እና ልጆችን ስለማሳደግ ምክር የነረ ነበር። ይህም ትምህርት ሴቶችን በቤት ሀላፊነታቸው እርዳታ ለመስጠት የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስላለባት ሀላፊነት ፕሪስዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ የሚያስተምሩትን ይደግፍ ነበር።

“‘ቤተሰብን በሚመለከት ፣ ወይም መኖር ስለሚገባው ሀላፊነት እና በባልና ሚስት እናም በወላጆችንና ልጆች መካከል በህግ ስለሚኖሁት የቤተሰብ ሀላፊነቶች ደንቆሮነት፣ ወይም በትንሽ ቢሆንም አለመግባባት በሚኖርበት ጊዜ፣ በቅርብ የሚገኝ ድርጅት አለ፣ እናም የድርጅቱ በሆነው የፍጥረት መንፈሳዊ ስጦታ እና መነሳሻ ምክንያት እነዚህን አስፈላጊ ሀላፊነቶች የሚነኩ ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጁ ናቸው።’”3

ማስታወሻዎች

  1. ጎርደን ቢ. ሒንክሊ፣ “Stand Strong against the Wiles of the World,” Ensign ህዳር 1995፣ 99።

  2. ባርብራ ቶምሰን “I Will Strengthen Thee; I Will Help Thee,” Liahona and Ensign ህዳር 2007፣ 117።

  3. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011), 153.

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. የምጠብቃቸውን እህቶች ቤተሰቦችን እንዲያጠናክሩ ለመርዳት እንዴት እችላለሁ?

  2. በቤተሰቤ ጻድቅ ተፅዕኖ ለመሆን እንዴት እችላለሁ?

አትም