2012 (እ.አ.አ)
በነቢይ የተመራ
ማርች 2012


ወጣቶች

በነቢይ የተመራ

በ16 አመቴ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አጠቃላይ ጉባኤ ለመሳተፍ እድል አገኘሁ። ቤተሰቤ ከምስራቅ ኦረገን፣ ዩኤስኤ የሚኖሩ ነበሩ፣ እናም ወደ ዩታ በጉባኤው ለመሳተፍና ታላቅ ወንድሜን ወደ ሚስዮን ማሰልጠኛ ቦታ ለማድረስ መኪና በመንዳት ተጓዘን።

ወደ ጉባኤው በመንፈስ ቅዱስ ለመማር ፍላጎት እየኖረኝ ሄድኩኝ። በእዚህም ምክንያት፣ እራሴን ባላዘጋጅ ኖሮ ልቀበለው በማልችለው ሁኔታ ከመንፈስ መግለጫን ተቀበልኩኝ።

በአንዱ የጉባኤ ስብሰባ፣ የተሰበሰቡት ሰዎች ተነስተው “Guide Us, O Thou Great Jehovah” የሚለውን መዝሙር ዘመሩ። ስንዘምር፣ በጉባኤው አዳራሽ ያሉትን ዞር ብዬ እንድመለከት ተነሳሳሁኝ። ይህን አደረግኩኝ እናም ሁላችንም ድምጻችንን እግዚአብሔርን ለመወደስ ከፍ ስናደርግ በእዚያ በነበሩት ብዙ ሺህ ሰዎች አንድነት ሀይል ተደነቅኩኝ።

ከእዚያም ኔፊ የህይወት ዛፍን በተመለከተበት ጊዜ ይሰማይ እንደነበር በሚሰማኝ አይነት ስሜታ አጋጠመኝ፣ ምክንያቱም መንፈስ “ተመልከት” ብሎኝ ነበርና (Nephi 11–14 ተመልከቱ)። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ቶምሰንን ተመለከትኩኝ እናም የቤተክርስቲያኗ አንድነት የሚገኘው ህያው በሆነ ነቢይ ስለምንመራ እንደሆነ ተሰማኝ። በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን የቀናችን እውነተኛ ነቢይ እንደሆኑ አወቅኩኝ፣ እናም ኢየሱስ ክርስቲስ ይህችን ቤተክርስቲያን በእርሳቸው በኩል እንደሚመራ አወቅኩኝ።

አትም