2012 (እ.አ.አ)
በመንግስቴ ውስጥ ያሉ ሴት ልጆች
ማርች 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት, የመጋቢት 2012 (እ.አ.አ)

በመንግስቴ ውስጥ ያሉ ሴት ልጆች

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት, ቤተሰብ. እርዳታ

እኛ የሰማይ አባታችን ሴት ልጆች ነን። እርሱም ያውቀናል፣ ያፈቅረናል፣ እናም ለእኛ እቅድ አለው። የእዚያ እቅድ ክፍልም መልካምን ከክፉ በላይ ለመምረጥ ለመማር ወደ ምድር መምጣትን ይጨምራል። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለማክበር ስንመርጥ፣ እርሱን እናከብራለን እና የእግዚአብሔር ሴት ልጆች እንደሆንን እንቀበላለን። የሴቶች መረዳጃ ማህበር መለኮታዊ ትውልዳችንን እንድናስታውስ ትረዳናለች።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና ታሪኳ እኛን ያጠናክራል እናም ይደግፈናል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ጁሊ ቢ ቤክእንዳሉት፥ “እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች፣ ለዘለአለማዊ ምድብ የተዘጋጃችሁ ናችሁ፣ እናም እያንዳንዳችሁ የሴት ማንነት፣ ፍጡር፣ እና ሀላፊነት አለባችሁ። የቤተሰብ፣ የህብረተሰብ፣ የዚህች ቤተክርስቲያን፣ እና የውዱ የደህንነት እቅድ ውጤታማነት የሚመካው በእኛ ታማኝነት ላይ ነው። … የሴቶች መረዳጃ ማህበር [የሰማይ አባታችን] ህዝቡን እንድትገነባ እና እነርሱን ለቤተመቅደስ በረከት እንዲያዘጋጅ ያቀደባት ነች። [የሴቶች መረዳጃ ማህበርን] የመሰረተው ሴት ልጆቹን በስራው ለማስተካከል እና መንግስቱን ለመገንባትና የፅዩን ቤቶችን ለማጠናከር የእነርሱን እርዳታ ለማግኘት ነው።”1

የሰማይ አባታችን መንግስቱን ለመገንባት እንድንረዳ ልዩ የሆነ ስራ ሰጥቶናል። እርሱም ደግሞ ይህን ልዩ ስራ ለማከናወን በሚያስፈልገን በመንፈሳዊ ስጦታዎች ባርኮናል። በሴቶች መረዳጃ ማህበር በኩል፣ ቤተሰቦችን ለማጠናከር፣ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት፣ እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዴት እንደምንኖር ለመማርልዩ ስጦታዎቻችንን ለመጠቀም እድል አለን።

ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ፣ የቀዳሚ አመራር ኁለተኛ አማካሪ፣ ስለደቀመዛሙርትነት እዳሉት፥ “በደቀመዛሙርትነት መንገድ በትእግስተኛነት በመራመድ፣ የእምነታችንን መጠን እና የእራሳችንን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለመቀበል ያለንን ፈቃደኛነት እናሳያለን።”2

የእግዚአብሔር ሴት ልጆች እንደሆንን እናስታውስ እናም እደ እርሱ ደቀመዛሙርቶች ለመኖርም እንጣር። ይህን ስናደርግ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለመገንባት እና ወደ ፊቱ ለመመለስ ብቁ ለመሆን እርዳታ እንሰጣለን።

ከቅዱሳት መጻህፍት

ዘካርያስ 2;10ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥1፣ 10፣ 16138፥38–39፣ 56፤ “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” (Liahona እና Ensign ህዳር 2010፣ 129)

ከታሪካችን

በሚያዝያ 28 ቀን 1842 (እ.አ.አ)፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለሴቶች መረዳጃ ማህበር እንዲህ አለ፥ “…እግዚአብሔር በሰጣችሁ ልቦና መሰረት በምትሰሩበት ሁኔታ ውስጥ ነው አሁን ያላችሁት። … ከእድላችሁ መሰረት ከኖራችሁ፣ መላእክት የእናንተ ጓደኞች ለመሆን አይከለከሉም።”3

ሌሎችን ለማገልገል እና ግለሰቦች ያላቸውን እምነት ለመጨመር ያላትን የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሀይል በማወቅ፣ ሶስተኛ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት ዚና ዲ. ኤች. ያንግ በ1893 (እ.አ.አ) ይህን ቃል ገቡ፣ “በልባችሁ ጥልቅ ከፈለጋችሁ ፣ በጌታ መንፈስ እርዳታ፣ የታላቅ ዋጋ እንቁን፣ የዚህን ስራ ምስክርነት፣ ታገኛላችሁ።”4

ማስታወሻዎች

  1. ጂሊ ቢ. ቤክ፣ “‘Daughters in My Kingdom’: The History and Work of Relief Society፣” Liahona ህዳር 2010፣ 112፣ 114።

  2. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “The Way of the Disciple፣” Liahona ግንቦት 2009፣ 76

  3. ጆሴፍ ስሚዝ፣ በ History of the Church 4፥605።

  4. ዚና ዲ. ኤች. ያንግ፣ “How I Gained My Testimony of the Truth፣” Young Woman’s Journal ሚያዝያ 1893፣ 319።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እህቶቼ እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች ያላቸውን ችሎታ እንዲያሟሉ እንዴት ለመርዳት እችላለሁ?

  2. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25 ውስጥ ለሴቶች የተሰጠውን ምክር እና ማስጠንቀቂያ እንዴት በህይወቴ በተግባር ለማዋል እችላለሁ?