2012 (እ.አ.አ)
ነቢያት ለምን ያስፈልጉናል?
ማርች 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መጋቢት 2011 (እ.አ.አ)

ነቢያት ለምን ያስፈልጉናል?

የሰማይ አባት ልጆቹን ስለሚወድ፣ በእዚህ ሟች ህወይት ያለመመሪያ በብቻቸው እንዲራመዱ አይተዋቸውም። የሰማይ አባታችን ትምህርቶች ተራ፣ ሊገመት የሚቻሉ፣ መፅሐፍ በሚሸጥበት በቀላል የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ልጆቹን ከሚያፈቅር ከሁሉም በላይ ሀይል ካለው፣ ሁሉን ከሚያውቀው የሰለስቲያል ፍጡር የሚመጡ ጥበቦች ናቸው። በቃላቱ የሚከበቡም የዘመናት ምስጢር ናቸው—እነዚህም ለእዚህ ህይወት እና ለሚመጣው አለም ደስታ ቁልፍ የሆኑ ናቸው።

የሰማይ አባት ይህን ጥበብ ለልጆቹ በምድር ላይ የሚገልጸው በአገልጋዮቹ በነቢያት በኩል ነው (አሞፅ 3፥7 ተመልከቱ)። ከአዳም ቀናት ጀምሮ፣ እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚናገረው ፍቃዱን እና ለሌሎች ያለውን ምክር የሚገልጸው በመደባቸው ጠቢብ ሰዎች በኩል ነው። ነቢያት የተነሳሱ አስተማሪዎች ናቸው እናም ሁልጊዜም የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክሮች ናቸው (D&C 107:23 ተመልከቱ)። ነቢያት ለጊዜአቸው ለሚገኙ ሰዎች ብቻ አይደለም የሚናገሩት፣ ነገር ግን በዘመናት በሙሉ ለሚኖሩ ሰዎችም ይናገራሉ። ደምጻቸውም እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለውን ፈቃድ በመመስከር በመቶ አመቶች ውስጥ ደጋግመው ይሰማሉ።

ዛሬ ከጥንት ዘመናት የተለየ አይደለም። ጌታ የእዚህ ቀናችን ሰዎችን ከጥንት ጊዜዎች ህዝቦች አስቀንሶ አያፈቅርም። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግም መመለስ አንዱ አስደናቂ መልእክት ቢኖር እግዚአብሔር ልጆቹን ለማነጋገር እንደቀጠለ ነው። በሰማያት የተደበቀ አይደለም ነገር ግን በጥንት ቀናት እንዳደረገው ዛሬም ይናገራል።

ጌታ ለነቢያቱ የሚገልጻቸው አብዛኛዎቹ እንደ ግለሰብ እና እንደ ህብረተሰብ እኛን ከሀዘን ለማዳን እቅድ ያለው ነው። እግዚአብሔር ሲናገር፣ ይህን የሚያደርገው ልጆቹን ለማስተማር፣ ለማነሳሳት፣ ለማንጠር፣ እና ለማስጠንቀቅ ነው። ግለሰቦች እና ህብረተሰቦች የሰማይ አባታቸውን መመሪያዎች ችላ ሲሉ፣ ይህን የሚያደርጉት በፈተና፣ በስቃይ፣ እና በከባድ ስራ ላይ እራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት ነው።

እግዚአብሔር ልጆቹን በሙሉ ያፈቅራል። ለእዚህም ነው በነቢያቱ በኩል በቅንነት የሚለምነን። ለምናፈቅራቸው ከሁሉም በላይ የሆኑትን እንዲያገኙ እንደምንፈልግ፣ የሰማይ አባትም ለእኛ ከሁሉም በላይ የሆነን እንድናገኝ ይፈልጋል። ለእዚህም ነው መመሪያዎቹ በጣም አስፈላጊ እና አንዳንዴም አስቸኳይ የሚሆኑት። ለእዚህም ነው ዛሬ እኛን በብቻችን ያልተወን ነገር ግን ለእኛ ፍላጎቱን በነቢያቱ በኩል ለመግለጽ ይቀጥላል። እጣችን እና የአለም እጣ የሚመሰረተው ለልጆቹ እግዚአብሔር የገለጸውን ቃል በመስማት እና በማድመጥ ነው።

ዋጋቸው ታላቅ የሆነው ለሰው ዘር የሰጣቸው የእግዚአብሔር መመሪያዎች በመፅሐፍ ቅዱስ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች እናም በታላቅ ዋጋ እንቁ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በተጨማሪም፣ በቅርብ በሚመጣው ጉባኤ እንደሚያደርገው፣ ጌታ ለእኛ በአገልጋዮቹ በኩል ይናገራል።

እንደእዚህ አይነት ነገር ለመሆን እንደሚችል ለሚያስቡት— “ዛሬ እግዚአብሔር ለእኛ መናገሩ እውነት ነው፣ ብለው ለሚጠይቁት?” —በሙሉ “እንድትመጡ እና እንድታዩ” (ዮሀንስ 1፥46). በቅዱሳት መጻህፍት የሚገኙትን የእግዚአብሔር ቃላት አንብቡ። በኋለኛ ቀል ነቢያት በኩል የሚሰጠውን የእግዚአብሔር ድምፅ ለመስማት ፈቃደኛ ከሆነ ጆሮ ጋር አጠጋላይ ጉባኤን አዳምጡ። ኑ፣ ስሙ፣ እናም በልባችሁ ተመልከቱ! “ሐበቅን ልባችሁ፤ ከእውነተኛ ፍላጎት፣ በክርስቶስ አምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል [እግዚአብሔር] እውነቱን ይገልፅላችኋል” (ሞሮኒ 10፥4)። በእዚህ ሀይል በኩል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው እንደሆነ እና ቤተክርስቲያኑን በህያው ነቢይ፣ እንዲሁም በፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንደሚመራ አውቃለሁ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ እግዚአብሔር ዛሬ እንደሚያናግረን አውቃለሁ። እናም ልጆቹ በሙሉ ድምጹን እንዲሰሙ እና እንዲያዳምጡ ይፈልጋል። ይህን ስናደርግ፣ በእዚህም ህይወት እና በሚመጣው አለሞች በኩል ጌታ ይባርከናል እናም በጣም ይደግፈናል።

አትም