2012 (እ.አ.አ)
እንደገና አየዋለሁ
ኤፕረል 2012


ወጣቶች

እንደገና አየዋለሁ

አባታችን እያንዳንዱ ልጆቹን ልዩ እንደሆንን እንዲሰማን አደረገ። ያፈቅረን እና ወዲያውም ይቅርታ ይሰጠን ነበር። እያንዳንዳችን ደስተኛ እንድንሆን ለማረጋገጥ የሚችለውን ያህል አደረገ፣ እናም እርሱ ለእኛ ከሁሉም በላይ የሚሻለውን እንደሚፈልግልን ግልፅ አደረገ። በጣም እወደው ነበር።

በስድስተኛ ክፍል እያለሁ፣ አባቴ በመኪና አደጋ ምክንያት ሞተ። ቤተሰቤ እና እኔ በጣም አዝነን ነበር። በቤተሰባችን ውስጥ ትልቅ ጉድጓድ እንዳለይመስል ነበር። አባቴ የምደገፍበት፣ ችግር ሲኖረኝ የምሄድበት ነበር። እርዳታ ከመፈለግ፣ ንዴቴ እና የተጎዳሁበት እንዲቆይ አደረግኩኝ። በመጨረሻም የእግዚአብሔር ጥፋት ነው ዬ ወሰንኩኝ። ቅዱሳት መጻህፍቴን ማንበብ እና መጸለይ አቆምኩኝ። ወደ ቤተክርስቲያን የሄድኩት እናቴ እንድሄድ ስለፈለገችኝ ብቻ ነበር። ከሰማይ አባት ለመራቅ እስከምችልበት ያህል እርቅ ነበር።

ከእዚያም ወደ ወጣት ሴቶች ካምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄድኩኝ። ከጓደኞቼ ጋር መገናኘትን እወድ ነበር፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻህፍቴን አላነብም ነበር። በመጨረሻው ምሽት፣ የምስክር ስብሰባ ነበረ። ለረጅም ጊዜ ያልተሰማኝ አንድ ነገር ተሰማኝ፥ ይህም መንፈስ ነበር። ተነስተው ምስክራቸውን የሰጡትን ሴት ልጆች ያስደንቁኝ ነበር፣ ነገር ግን እንዳልነበረኝ ስለማስብ አልተነሳሁም ነበር። በድንገት መነሳት እንዳለብኝ ተሰማኝ። ምን እንደምል እያሰብኩኝ፣ አፌን ከፈትኩኝ። ስለዚህ በወጣት ሴቶች ካምፕ ስለነበርኩኝ ደስተኛ ነኝ አልኩኝ። ከእዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ እንደሞተ አውቃለሁ እናም የሰማይ አባት እንደሚያፈቅረኛ ቤተክርስቲያኗ እውነት እንደሆነኝ እንደማውቅ መናገር ጀመርኩኝ።

በጣም አስደናቂ በሆነ ሰላይ ተሞላሁኝ። በእዚህ አጋጣሚ ምክንያት በአዳኝ የኃጢያት ክፍያ እና በትንሳኤ ምክንያት አባቴን እንደገና እንደማየው አውቃለሁ ለማለት እችላለሁ።

አትም