2012 (እ.አ.አ)
‘ተነስቷል’— የነቢይ ምስክርነት
ኤፕረል 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሚያዝያ 2012 (እ.አ.አ)

“ተነስቷል”

የነቢይ ምስክርነት

“የክርስቲያን አለም የሚሰማ ጥሪ” ቢኖር የናዝሬት ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ ነው ብለው ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን አውጀዋል። “የትንሳኤ እውነትነት ለሁሉም መረዳት ከሚቻለው በላይ የሆነ ሰላም ይሰጣል” (Philippians 4:7 ተመልከቱ)።1

በሚቀጥሉት ምንባቦች ውስጥ፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን ለአዳኝ ትንሳኤ ያላቸውን ምስክርነትና ምስጋና ይካፈላሉ እናም ልጅ ሞትን ስላሸነፈ፣ ወደ ምድር የመጡ የአብ ልጆች በሙሉ እንደገና እንደሚኖሩ ያውጃሉ።

ከሟችነት በኋላ ያለ ህይወት

“ኢየሱስ በገትሰመኔ ያደረገልንን ሙሉ አስፈላጊነት በፍጹም ለመረዳት ማንኛችንም እንደማንችል አምናለሁ፣ ነገር ግን ለእኔ ባደረገው የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት በህይወቴ በሙሉ ምስጋና ይሰማኛል።

“በመጨረሻው ጊዜ፣ ዞር ብሎ ለመመለስ ይችል ነበር። ነገር ግን አልተመለሰም። ሁሉንም ነገሮች ያድን ዘንድ ከሁሉም ነገሮች በታች አልፎ ሄደ። ይህን በማድረጉ፣ ከሟችነት በኋላ የሚገኝ ህይወት ሰጠን። ከአዳም ውድቀት አድኖ እንደገና የእርሱ አደረገን።

“በነፍሴ በሙሉ፣ ለእርሱ ምስጋና ይሰማኛል። እንዴት እንደምንኖር አስተማረን። እንዴት መሞት እንዳለብን አስተማረን። ደህንነታችንን እንድናገኝ አደረገልን።”2

የሞትን ጭለማ መበተን

“በታላቅ ስቃይ ወይም ህመም አይነት አንዳንድ ጉዳዮች፣ ሞትም እንደ ምህረት መልአክ ይመጣል። ነገር ግን ለብዙ ጊዜ፣ እንደ ሰው ደስታ ጠላት ነው የምናስብበት።

“የሞት ጭለማ በተገለጸ እውነት ብርሀን ሊበተን ይቻላል። ‘ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፣’ ብሎ መምህር ተናግሯል። ‘የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም።’

“ይህ ከመቃብር በኋላ ህይወት እንዳለ የሚያሳይ መፅናኛ—አዎን እንዲሁም ቅዱስ ማረጋገጫ—አዳኝ ለደቀመዛሙርቱ ቃል የገባውን ሰላይ ለመስጠት ይችላል፥ ‘ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” በሚልበት ጊዜ ቃል በገባበት ቃል ኪዳን ለነፍሶቻችን ሰላም ያመጣል።’”3

እዚህ የለም

“አዳኛችን እንደገና ህያው ነው። በሰው ዘር ታሪክ ሁሉ ከሁሉም ድርገቶች በላይ ግርማዊ፣ የሚያፅናና፣ እና የሚያረጋግጥ የሆነው ደርሷል—ይህም ከሞት በላይ ያል ድል ነው። የገትሰመኔ እና የቀራንዮም ስቃይ ተጠርጓል። የሰው ዘር ደህንነት ተረጋግጧል። ከአዳም ውድቀት እንደገና ተመልሰናል።

“በመጀመሪያ የትንሳኤ ጠዋት የነበረው ባዶ መቃብር ለኢዮብ ጥያቄ መልስ ነበር፣ ‘ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?’ ድምጼን ለሚሰሙት በሙሉ፣ ይህን አውጃለሁ፣ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናል። ይህን እናውቃለን፣ የተገለጸ እውነት ብርሀን አለንና።…

“ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በጥልቅ ሀዘናችን ጊዜ ውስጥ፣ በእዚያ በመጀመሪያ ትንሳኤ ጠዋት መላኩ በተናገራቸው ቃላት ታላቅ ሰላም ለማግኘት እንችላለን፥ ‘ተነሥቶአልና በዚህ የለም።’”4

ሁሉም እንደገና ይኖራሉ

“እንስቃለን፣ እናለቅሳለን፣ እንሰራለን፣ እንጫወታለን፣ እናፈቅራለን፣ እንኖራለን። እና ከእዚያም እንሞታለን።…

“እናም በአንድ ሰው፣ እንዲሁም በናዝሬት ኢየሱስ፣ ባይሆን ኖሮ ሞተን እንቀር ነበር።…

“በልቤ እና በነፍሴ በሙሉ፣ እንደ ልዩ ምስክር የምስክርነቴን ድምፅ ከፍ አደርጋለሁ እናም እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ አውጃለሁ። ኢየሱስ ልጁ ነው፣ እርሱም የአብ በስጋ የተወለደ አንድያ ልጅ ነው። እርሱም ቤዛችን ነው፤ እርሱም ከአብ ጋር አማላጃችን ነው። እርሱም በመስቀል ላይ ለኃጢያቶቻችን ክፍያ የሞተ ነበር። እርሱም የትንሳኤ የመጀመሪያው ፍሬ ሆነ። ስለሞተም፣ ሁሉም እንደገና ይኖራሉ።”5

የግል ምስክር

“ሞት እንደተሸነፈ፣ በመቃብር ላይ ድል እንደነበረ የግል ምስክሬን አውጃለሁ። ባሟላቸው ቅዱስ የሆኑት ቃላት ለሁሉም እውነተኛ እውቀት ይሁኑ። አስታውሷቸው። አፍቅሯቸው። አክብሯቸው። ተነሥቷል6

ማስታወሻዎች

  1. “He Is Risen,” Liahona, ሚያዝያ፣ 2003፣ 7።

  2. “At Parting,” Liahona, ግንቦት 2011፣ 114።

  3. “Now Is the Time,” Liahona ጥር. 2002፣ 68፤ ደግሞም ዮሀንስ 11፥25–2614፥27

  4. “He Is Risen,” Liahona ግንቦት 2010፥ 89፥ 90፤ ደግሞም ኢዮብ 14፥14ማቴዎስ 28፥6

  5. “I Know That My Redeemer Lives!” Liahona ግንቦት 2007፣ 24፣ 25።

  6. Liahona ሚያዝያ 2003፣ 7።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

ከፕሬዘደንት ሞንሰን መልእክቶች የመጡትን እነዚህን ምንባቦች ከተካፈላችሁ በኋላ፣ ስለትንሳኤ እውነተኛ ትርጉም የሰጡትን ምስክርነት ጠቁሙ። የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች የቤተሰብ አባላትን ለመጠየቅ ትችላላችሁ፥ “ህያው የሆኑ ነቢይ ስለእነዚህ እውነቶች ዛሬ መመስከራቸው ለእናንተ ምን ትርጉም አለው? እነዚህን በህይወት እንዴት በጥቅም ለማዋል ትችላላችሁ?” ምስክራችሁን ለመጨመር አስቡበት።

አትም