2012 (እ.አ.አ)
አፍቅሩ፣ ጠብቁ፣ እናም አጠናክሩ
ኤፕረል 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2012 (እ.አ.አ)

አፍቅሩ፣ ጠብቁ፣ እናም አጠናክሩ

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

እንደ አዳኝ፣ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪ አንድ በአንድ ታገለግላለች (3 ኔፊ 11፥15 ተመልከቱ)። እህቶቻችን እንዲህ ሲሉ እንደ የቤት ለቤት አስተማሪ ያገለገልንበት ውጤታማ እንደሆንን እናውቃለን፥ (1) የሴቶች የቤት ለቤትአስተማሪዬ በመንፈስ እንዳድግ ትረዳኛለች፤ (2) የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዬ ለእኔ እና ለቤተሰቤ በጥብቅ ታስባለች፤ እና (3) ችግር ካለኝ፣ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዬ ለመጠየቅ ሳትጠብቅ ስራን ለማከናወን እንደምትሄድ አውቃለሁ።1

እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች እንዴት እህትን ለማፍቀር፣ ለመጠበቅ፣ እናም ለማጠናከር እችላለሁ? የሚከተሉት በDaughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ የሚገኙ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች እህቶቻቸውን እንዲያገለግሉ እንዲረዷቸው በምዕራፍ 7 ውስጥ የሚገኙት ዘጠኝ ሀሳቦች ናቸው፥

  • በየቀኑ ለእርሷ እና ለቤተሰቧ ጸልዩ።

  • እርሷን እና ቤተሰቧን ለማወቅ መነሳሻን ፈልጉ።

  • እርሷ እንዴት እንደሆነች ለማወቅ እና እርሷን ለማፅናናት እና ለማጠናከር በየጊዜው እርሷን ጎበኙ።

  • በጉብኝት፣ በስልክ በመደዋወል፣ በደብዳቤ፣ በኢሜል፣ በእጅ ስልክ መልእክት፣ እና በመልካም የደግ ስራ ከእርሷ ጋር በየግዜው ተገናኙ።

  • በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች እርሱን ሰላም በሏት።

  • አደጋ፣ በሽታ፣ ወይም ሌላ ቶሎ የሚያስፈልጋት ሲኖር እርሷን እርዳታ ስጧት።

  • ወንጌልን ከቅዱሳት መጻህፍት እና ከሴቶች የቤት ለቤት መልእክቶች አስተምሯት።

  • ጥሩ ምሳሌ በመሆን አነሳሷት።

  • ስለአገልግሎታችሁ እና ስለእህት መንፈሳዊ እና ጊዜአዊ ደህንነት ለሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች ሀተታ ስጡ።

ከቅዱስ መጻህፍት

ሉቃስ 10፥38–393 ኔፊ 11፥23–2627፥21

ከታሪካችን

“የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት የአለም አቀፍ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች ለማፍቀር፣ ለመንከባከብ፣ እና ለማገልገል፣ እንዲሁም ጆሴፍ ስሚዝ እንዳስተማረው ‘እግዚአብሔር በልባችሁ በተከለው ለሌሎች ሀዘን በሚሰማችሁ ሁኔታ መሰረት ለመስራት’ የሚጠቀሙበት መሳሪያ ሆኗል።2

በቅርብ ባሏ የሚተባት ሴት ስለሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች እንዳለችው፥ “ያዳምጣሉ። እኔንም አፅናኑኝ። ከእኔም ጋር አለቀሱ። አቀፉኝም። … [እነርሱም] በእነዚያ የመጀመሪያ ትንሽ ወሮች ውስጥ ከነበሩኝ ብቸኛነት ከመጡት ከጥልቅ ተስፋ መቁረጥ እና መከፋት እንድወጣ እርዳታ ሰጡኝ።3

በስጋዊ ስራዎች መርዳትም የማገልገል አይነት ነው። በጥቅምት 1856 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ላይ፣ በእጅ ጋሪ የሚጓዘ ፈር ቀዳጆች ጥልቅ በሆነ በረዶ ውስጥ 270–370 ማይል (435–595 ኪሎሜትር) ያህል በሚርቅ ቦታ ላይ ያለረዳት እንደቀሩ ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ አስታወቁ። በሶልት ሌክ ከተማ ውስጥ ያሉት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እነርሱን እንዲያድኑ እና “ስጋዊ ብለን የምንጠራቸውን ነገሮች በጥብቅ እንዲያከናውኑ” ጠሩ።4

ሴቶች ከበታች የሚለብሱትን የሚሞቅ ልብስ እና የእግር ሹራብን እዚያው እያሏውጥተው በብርድ ላይ ወደ አሉት ፈር ቀዳጆች በሚሄደ ጋሪ ላይ እንደቆለሉት ሉሲ መሰርቭ ስሚዝ ጻፈች። ከእዚያም መኝታዎችን እና ልብሶችን ጥቂት እቃ ይዘም ለሚመጡት ሰዎች አዘጋጁላቸው። የእጅ ጋሪ ቡድኖች ሲደርሱም፣ በከተማው ውስጥ የነበረው ህንጻ “ለእነርሱ በሚጠቅሙ ነገሮች ተሞልተው” ነበር።5

ማስታወሻዎች

  1. ጁሊ ቢ. ቤክ፣ “What I Hope My Granddaughters (and Grandsons) Will Understand about Relief Society፣” Liahona ህዳር 2011፣ 113።

  2. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 112።

  3. Daughters in My Kingdom 119–20።

  4. ብሪገም ያንግ፣ “Remarks፣” Deseret News ጥቅምት 15፣ 1856፣ 252።

  5. Daughters in My Kingdom 36–37 ተመልከቱ።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እህቶቾእ ምን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ለማወቅ እችላለሁ?

  2. እህቶቼ በጥልቅ እንደማስብላቸው እንዴት አውቃለሁ?

አትም