2012 (እ.አ.አ)
ለሰንበት ትምህርት አስተማሪዬ ምስጋና ይሁን
ሰኔ 2012 (እ.አ.አ)


ወጣቶች

ለሰንበት ትምህርት አስተማሪዬ ምስጋና ይሁን

የሰንበት ትምህርት ክፍሌ ሁልጊዜም አምልኮን የሚያሳዩ አይደሉም። የየሳምንቱን ትምህርት ለማዳመጥ እወድ ነበር፣ ነገር ግን አንዳንዴ በክፍሌ ውስጥ ያሉት ሌሎች ይህን ለማድረግ የማይፈልጉ ይመስል ነበር። በብዙ ጊዜ አስተማሪያችን በምታስተምርበት ጊዜ እነርሱ እርስ በራስ ይነጋገራሉ ወይም በእጅ ስልኮች ይጫወታሉ። በሚያሳዝን ሁኔታም፣ እራሴ የችግሩ ክፍልም እሆናለሁ።

አንድ ሳምንት ከድሮ ይበልጥ መጥፎ ነበርን፣ እናም በማንም የምታስተምረውን ስላላዳመጡ በክፍሉ መጨረሻ ላይ አስተማሪያችን አለቀሰች። ከክፍል ስወጣ፣ በእርሷ ላይ ያደረግነው እንዲከፋኝ አደረገኝ።

በሚቀጥለው እሁድ በእዚያ ሳምንት ብዙ እንደጸለየች፣ መመሪያ እንደፈለገች፣ እና የቤተክርስቲያን ፊልም ለእኛ ማሳየት እንደሚያስፈልጋት እንደተሰማት ገለጸችልን። ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለሰራቸው ታዕምራት የነበረውን ፊልም ማሳየት ጀመረች።

በእዚያ ምሽት ስለፊልሙ ሳስብበት፣ ልዩ ስሜታ ተሰማኝ። ከእዚህ በፊት ከተሰማኝ በላይ፣ መንፈስ እየተሰማኝ እንደሆነም አወቅኩኝ። ወዲያውም እንደ አዳኝ ለመሆን ህይወቴን ለመቀየር እንደምፈልግ ወሰንኩኝ፣ እናም በእዚያ ቀን በሰንበት ትምህርት ውስጥ ያጋጠመኝ ምስክሬን እንዳጠናከረ አወቅኩኝ። ለሰንበት ትምህርት አስተማሪዬ እን አለክፍላችን በየሳምንቱ ለምታደርገው ታላቅ ምስጋና አለኝ።

አትም