2012 (እ.አ.አ)
የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ቅዱስ ምድብ
ሰኔ 2012 (እ.አ.አ)


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሰኔ 2012 (እ.ዓ.ዓ)

የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት—ቅዱስ ምድብ

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች፣ ማሟላት ያለብን አስፈላጊ የመንፈስ ሚስዮን አለን። “ዎርዱን ለማስተዳደር የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ሁሉንም የጌታ በጎች በአንድ ጊዜ ለመጠበቅ አይችልም። በሚነሳሱ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች እርዳታላይ ይመካል።”1 እያንዳንዷን እህት ለመጠበቅ ማን መመደብ እንዳለባት ለማወቅ ራዕይን መፈለግ እና መቀበል አስፈላጊ ነው።

መነሳሳት የሚጀምረው የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር በጸሎት የግለሰቦችን እና የቤተሰቦችን ፍላጎት በሚወያዩበት ነው። ከእዚያም፣ በኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ፣ እህቶች የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስፈላጊ መንፈሳዊ ሀላፊነት እንደሆነ እንዲረዱ በሚያስችላቸው መንገድ የሚመደቡበትን የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ይሰጣሉ።2

የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች እያንዳንዷን እህት ለማወቅ እና ለማፍቀር፣ እምነቷን እንድታጠናክር ለመርዳት፣ እና በሚያስፈልበት ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት ይችላሉ። ለሚጎበኟት እያንዳንዷ እህት መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍላጎቶች እንዴት መልስ ለመስጠት እንደሚችሉ ለማወቅ የግል መነሳሻን ይፈልጋሉ።3

“ትኩረታችን በቁጥር ላይ ሳይሆን በሰዎች ላይ ሲሆን፣ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት የጌታ ስራ ይሆናል። በእርግጥም፣ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት በምንም የሚፈጸም አይደለም። የስራ ሀላፊነት ሳይሆን በህይወት የሚኖርበት ነው።”4

ከቅዱሳት መጻህፍት

ማቴዎስ 22፥36–40ዮሀንስ 13፥34–35አልማ 37፥6–7

ከታሪካችን

እላይዛ አር ስኖው፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት፣ እንዳስተማሩት፣ “የአስተማሪ ሀላፊነትን እንደ ታላቅ እና ቅዱስ ሀላፊነት እመለከተዋለሁ። የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች ቤትን ከመጎብኘታቸው በፊት፣ መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍላጎቶችን ለማወቅ እና ለማሟላት እርግጠኛ እንዲሆኑ “በእግዚአብሔር መንፈስ፣ ጥበብ፣ ትሁትነት፣ ፍቅር እንዲሞሉ” መክረዋል። እንዲህም አሉ፣ “የሰላም እና የመፅናኛ ቃላትን እንድትናገሩ ይሰማችሁ ይሆናል፣ እናም የበረደች እህትን ካገኛችሁም፣ ልጅን በእቅፋችሁ እንደምታስገቡ እርሷንም ወደ ልባችሁ ውሰዱ እና ሙቀትን ስጧት።”5

የድሮ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች እንዳደረጉት በእምነት ወደ ፊት ስንገፋ፣ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ይገኛል እናም የምንጎበኛትን እያንዳንዷን እህት እንዴት ለመርዳት እንደምንችል ለማወቅ እንነሳሳለን። እህት ስኖው እንዳሉት፣ “ሀይን ሳይሆን ጥበብን [እንፈልግ]፣ እናም [እኛም] በጥበል ለመጠቀም የምንችልበትን ሀይል በሙሉ ይኖረናል።”6

ማስታወሻዎች

  1. ጁሊ ቢ ቤክ፣ “Relief Society: A Sacred Work፣” Liahona ህዳር 2009፣ 114።

  2. See Handbook 2: Administering the Church (2010)፣ 9.5፤ 9.5.2።

  3. ተመልከቱ።፣ 9.5.1 ተመልከቱ።

  4. ጁሊ ቢ ቤክ፣ Liahona, ህዳር 2009፣ 114

  5. እላይዛ አር. ስኖው በDaughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 108።

  6. እላይዛ አር. ስኖው፣ Daughters in My Kingdom ውስጥ፣ 45–46።