2012 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር የተጠራ እና በህዝብ የተደገፈ
ሰኔ 2012 (እ.አ.አ)


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሰኔ 2012 (እ.ዓ.ዓ)

በእግዚአብሔር የተጠራ እና በህዝብ የተደገፈ

ምስል
በፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ

እንደ ቤተክርስቲያኗ አባላት፣ ለማገልገል በሚጠሩበት ሰዎችን እንድንደግፍ እንጋበዛለን። ከብዙ አመት በፊት የጌታን አገልጋይ መደገፍ ምን ማለት እንደሆነ የ18 አመት ተማሪ አሳይቶኛል። በእርሱ ትሁት ምሳሌ አሁንም እባረካለሁ።

የዩንቨርስቲ ትምህርቱን የመጀመሪያ አመት ገና ጀምሮ ነበር። በትልቅ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ትምህርቱን ለመጀመር ከቤት ከመውጣቱ አንድ አመት በፊት ተጠምቆ ነበር። በእዚያም እንደ ኤጴስ ቆጶስ አገለግል ነበር።

የትምህርቱ አመት በተጀመረበት ጊዜ፣ በኤጲስ ቆጶስ ቢሮ ውስጥ ከእርሱ ጋር ለአጭር ጊዜ የቃል ንግግር አደረግኩኝ። በአዲስ ቦታ ስላለው ፈተና ስለተናገረው በስተቀር ስለተነጋገርንባቸው ብዙ አላስታውስም ነበር፣ ነገር ግን ሁለተኛው ንግግራችንን በምንም አልረሳም።

በቢሮዬ ከእኔ ጋር ለመገናኘት ፈለገ። “አብረን ለመጸለይ እንችላለን፣ እናም እኔ ጸሎቱን ብል ግድ ይሎታል?” በማለት አስደንግጦኝ ነበር። ጸልያለሁ እናም እርሱ እንደጸለየም እርግጠኛ ነኝ ልለው አስቤ ነበር። ነገር ግን እንዲህ እንዲያደርግ ተስማማሁ።

ጸሎቱን ኤጲስ ቆጶስ በእግዚአብሔር የተጠራ እንደሆነ እንደሚያውቅ በመመስከር ጸሎቱን ጀመረ። በታላቅ መንፈሳዊ ውጤት ባለው ነገር ላይ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልገው እግዚአብሔር እንዲነግረኝም ጠየቀ። ኤጲስ ቆጶሱ የሚያስፈልገውን እንደሚያውቅ እና ለመስማት የሚያስፈልገውን ምክር እንደሚሰጠው እርግጠኛ እንደሆነ ወጣት ሰውየው ለእግዚአብሔር ነገረው።

ሲናገርም፣ የሚያጋጥመው አደጋ ምን እንደሆነ ወደ አዕምሮዬ መጣ። ምክሬ ያልተወሳሰበ ነገር ግን በግልጽ የተሰጠ ነበር፥ ሁልጊዜ ጸልይ፣ ትእዛዛትን አክብር፣ እና ምንም አትፍራ።

ያም ወጣት ልጅ፣ በቤተክርስቲያኗ የአንድ አመት አባል ቢሆንም፣ መሪ እንዲመራቸው በተጠራው ሰዎች እምነት እና ጸሎት ሲደገፍ እግዚአብሔር በእርሱ ምን ማድረግ እንደሚችል በምሳሌ አስተማረ። ያም ወጣት ሰው ለእኔ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለው የጋራ ስምምነት ህግ ሀይል አሳየኝ (ት. እና ቃ. 26:2 ተመልከቱ)። ምንም እንኳን ጌታ አገልጋዮቹን በራዕይ ቢጠራም፣ እነርሱ መስራት የሚችሉት እንዲያገለግሏቸው በተጠሩት ሰዎች ሲደገፉ ብቻ ነው።

በሚደገፉበት ምርጫ፣ የክብር ቃል ኪዳን እንገባለን። ጌታ እንዲመራቸው እና እንዲያጠናክራቸው ዘንድ፣ ለአገልጋዮቹ ለመጸለይ ቃል እንገባለን (ት. እና ቃ. 93:51 ተመልከቱ)። በምክራቸው እና በጥሪያቸው በሚሰሩበት በማንኛውም ጊዜ ከእግዚአብሐርን የሚመጣውን መነሳሻ ለመፈለግ እና እንዲሰማን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን (ት. እና ቃ. 1:38 ተመልከቱ)።

ያም ቃል ኪዳን በልባችን በተደጋጋሚ መታደስ ያስፈልገዋል። የሰንበት ትምህርት አስተማሪያችሁ በመንፈስ ለማስተማር ይጥራል፣ ነገር ግን እናንተ እንደምታደርጉትም፣ አስተማሪያችሁ በፊታችሁ ስህተት ማድረግ ይችል ይሆናል። እናንተ ግን መነሳሻ ሲመጣ የሚሰማችሁን ጊዜ ለማወቅ ለመስማት እና ለመመልከት ለመወሰንትችላላችሁ። ከጊዜም በኋላ የምትመለከቱት ስህተቶች ይቀንሳሉ እናም እግዚአብሔር ያን አስተማሪ እንደሚደግፍ የሚያሳየው መረጃ በተደጋጋሚ ትመለከታላችሁ።

ሰውን ለመደገፍ አጃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ያ ሰው የጌታን ማንኛውን ስራ እንዲያከናውን የተጠራበትን ለማከናወን ለመርዳት እንወስናለን። ልጆቻችን ትትንሽ በነበሩበት ጊዜ፣ ባለቤቴ የዎርዳችንን ትትንሽ ልጆች እንድታስተምር ተጠርታ ነበር። እርሷን ለመደገፍ እጄን ከማንሳት በስተቀር፣ ለእርሷ ጸለይኩኝ እና ከእዚያም እርሷን ለመርዳት ፈቃድ ጠየቅኩኝ። ሴቶች ስለሚያደርጉት እና ጌታ ለልጆች ስላለው ፍቅር ለመማር ስለተቀበልኩት ትምህርቶች ቤተሰቤን እና ህይወቴን ባርከዋል።

ከብዙ አመት በፊት ኤጲስ ቆጶሱን ከደገፈው ወጣት ሰው በቅርብ ተነጋግሬ ነበር። በወንጌል መልእክተኛነቱ፣ በካስማ ፕሬዘደንትነቱ፣ እና በአባትነቱ ጌታ እና ህዝቦች እንደደገፉት አወቅኩኝ። በንግግራችን መጨረሻ ላይ፣ “በየቀኑ ለእርስዎ እጸልይሎታለሁ” አለ።

በእግዚአብሔር እንዲያገለግለን ለተጠራ ሰው በየቀኑ ለመጸለይ መወሰን እንችላለን። በእርሱ ወይም በእርሷ አገልግሎት የባረከን ወይም የባረከችንን ለማመስገን እንችላለን። የደገፍናቸው ለእርዳታ ሲጠይቁም ወደፊት ለመሄድ ለመወሰንም እንችላለን።1

የጌታ አገልጋዮችን በመንግስቱ ውስጥ የሚደግፉም አቻ በሌለው ሀይሉ ይደገፋሉ። ሁላችንም ያ በረከት ያስፈልገናል።

ማስታወሻ

  1. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፥ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ [1998 (እ.አ.አ)]፣ 211–12።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

መልእክቱን ከተካፈላችሁ በኋላ፣ የሚቀጥለውን ጥቅሰት ለማንበብ አስቡበት፥ “ትሁት፣ ታማኝ፣ እና ትጉ ከሆናችሁ ጌታ በእጁ መሳሪያ ያደርጋችኋል። … በተሰብሳቢዎች ስትደገፉ እና ስትለያዩም ተጨማሪ ጥንካሬ ትቀበላላችሁ” (Teaching, No Greater Call [1999 (እ.አ.አ)]፣ 20)። ቤተሰቦች በከባድ እቃ አጠገብ እንዲቆሙ አድርጉ እናም አንድ ሰው ይህን እንዲያነሳ ጠይቁ። አንድ ሰው በተራ በመጨመር፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ይህን እቃ እንዲያነሱ ጠይቁ። ሁሉም ሲረዱ ምን እንደደረሰ ተወያዩበት። ሌሎችን በጥሪአቸው የምንደግፍበትን መንገዶች ስለመለማመድ ፕሬዘደንት አይሪንግ ስለመከሩት ትኩረት ለመስጠት አስቡበት።

አትም