2012 (እ.አ.አ)
በቤተመቅደስ ማገልገል
ኦገስት 2012


ወጣቶች

በቤተመቅደስ ማገልገል

በአስራ ሰባት አመቴ፣ ስለወደፊት ህይወቴ ማስብ ጀመርኩኝ፣ እናም ወደ ሚስዮን ለመሄድ እና ለመልከ ጼዴቅ ክህነት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንደምችል ለማወቅ ወደ ሰማይ አባት ጸለይኩኝ። የጌታ ቤት ስለሆነና ከሰማይ አባቴ ጋር የምቀርብበት ስሜት እንዲሰማኝ የምችልበት ቦታ ስለሆነ ወደ ቤተመቅደስ በተደጋጋሚ መሄድ እንደሚገባኝ ተሰማኝ።

ስለዚህ 1 ሺህ ጥምቀቶች ለማከናወን አላማ ሰራሁ። ይህን አላማ ለመስራት እንደሚያስፈልገኝ ተሰምቶኝ ነበር፤ ይህን ማድረግ እንደሚያስፈልገኝ ለማወቅ ጾምኩኝ። የሰማይ አባታችን መልስ ሰጠኝ፣ እናም ወደ ተምፒኮ ሜክሲኮ ቤተመቅደስ በየሳምንቱ በቅዳሜ መሄድ ጀመርኩኝ።

500 ጥምቀቶች ከፈጸምኩኝ በኋላ፣ የቅድመ አያቶቼን ታሪክ ለመፈለግ አላማ አደረኩኝ፣ እናም ታሪኩን መፈለግ በጣም አስደስቶኝ ስሞችን በመፈለግ ለመተኛት አልቻልኩም ነበር። 50 ስሞች እና የቤተሰቤን ስምንት ትውልድ ታሪኮችን አገኘሁ፤ ለሁሉም የቤተመቅደስ ስራቸውን ፈጸምኩላቸው።

1 ሺህ 300 ጥምቀቶችን አከናወንኩኝ፣ እናም ከሰምነሪ ተመረቅኩኝ፣ የመልከ ጼደቅ ክህነትን ተቀበልኩኝ፣ እናም አሁን በህይወቴ ታላቅ አላማዬ አንድ የነበረውን በሙሉ ጊዜ በሚስዮን እያገለገልኩኝ ነው ያለሁት።

አትም