2012 (እ.አ.አ)
እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ አንድ ነገር ለማድረግ መገኘት
ኦገስት 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ነሐሴ 2012 (እ.አ.አ)

እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ አንድ ነገር ለማድረግ መገኘት

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች፣ ከአላማዎቻችን አንዱ ቤተሰቦችን እና ቤቶችን ለማጠናከር ለመርዳት ነው። የምንጎበኛቸው እህቶች “ችግር ካለኝ፣ የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዬ ሳይጠየቁ ይረዱኛል” ለማለት መቻል ይገባታል። ለማገልገል፣ የምንጎበኛቸው ሴቶች ምን እንደሚፈልጉ የማወቅ ሀላፊነት አለን። መነሳሳትን ስንፈልግ፣ እንድንጎበኝ የተመደብናት የእያንዳንዷ እህት መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍላጎትን እንዴት ለማሟላት እንደምንችል እናውቃለን። ከእዚያም ጊዜአችንን፣ ችሎታችንን፣ የእምነት ጸሎታችንን፣ እና መንፈሳዊና ስሜታዊ ድገፋችንን በመጠቀም በህመም፣ በሞት፣ እና በሌሎች ልዩ ጉዳዮች ጊዜ የርህራሄ አገልግሎቶችን ለመስጠት ለመርዳት እንችላለን፡1

ከሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች ሀተታዎች በኩል፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር በህመም፣ በአደጋ፣ ልጅ በመውለድ፣ በሞት፣ በአካለ ስንኩልነት፣ ወይም በሌሎች ችግሮች ምክንያት ልዩ የእርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለማወቅ ይችላሉ። ከእዚያም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት የምታውቀውን ለኤጲስ ቆጶስ ትነግራለች። በእርሱም አበራር፣ እርዳታ የሚሰጠውን ታቀናጃለች።2

እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች “ለደስታችን እንዴት ታላቅ ምክንያት አለን” ምክንያቱም “ይህንን ታላቅ ስራም ለመፈፀም በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያ መሆናችን፣ ይህ በእኛ ላይ የወረደው በረከት ነውና” (አልማ 26፥1፣ 3)።

ከቅዱሳት መጻህፍት

ማቴዎስ 22፥37–40ሉቃስ 10፥29–37አልማ 26፥1–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥18–19

ከታሪካችን

በቤተክርስቲያኗ የመጀመሪያ አመታት፣ የአባላት ቁጥር ትንሽ እና በአንድ ቦታ የሚገኙ ነበሩ። አባላት አንድ ሰው እርዳታ ሲያስፈልገው ወደኢያው እንዳታ ለመስጠት ይችሉ ነበር። ዛሬ የአባላታችን ቁጥር ከ 14 ሚልዮን በላይ ነው እናም በአለም ውስጥ የተበተንን ነን። የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ጌታ ልጆቹን ለመርዳት ያለው አላማ ክፍል ውስጥ ነው።

በቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ የሆኑት ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ “በትልቋእና በተለያየ አለም ቦታ የምትገኝን ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ እና ለማፅናናት የሚቻልበት ዘዴ ቢኖር እርዳታ በሚያስፈልጋቸው አጠገብ በሚገኙ በግለሰብ አገልጋዮች በኩል ነው” ብለዋል።

ቀጥለውም፣ “… እያንዳንዱ ኤጲስ ቆጶስ እና እያንዳንዱ የቅርንጫፍ ፕሬዘደንት የሚደገፍበት የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት አለው” ብለዋል። “እርሷም የእያንዳንዷን እህት ፈተና እና ፍላጎት የሚያውቁ የሴት የቤት ለቤት አስተማሪዎች አሏት። በእነርሱም በኩል፣ የግለሰቦችን እና የቤተሰቦችን ሁኔታ ታውቃለች። እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት እና ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ለመንከባከብ ኤጲስ ቆጶስ ያለውን ጥሪ ለማሟላትም ትረዳለች።”3

ማስታወሻዎች

  1. Handbook 2: Administering the Church (2010)፣ 9.5.1፤ 9.6.2 ተመልከቱ።

  2. Handbook 2፣ 9.6.2 ተመልከቱ።

  3. ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣በ Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 110።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ስጦታዬን እና ችሎታዬን ሌሎችን ለመባረክ እጠቀምበታለሁን?

  2. የምጠብቃቸው እህቶች እርዳታ ሲያስፈልጋቸው እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ እንደሆንኩኝ ያውቃሉ?

አትም