2012 (እ.አ.አ)
ለአገልግሎት የሚጠራው የአዳኝ ጥሪ
ኦገስት 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2012 (እ.አ.አ)

ለአገልግሎት የሚጠራው የአዳኝ ጥሪ

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን።

ሂሳብ ያጠኑት ሁሉ አካፋው ምን እንደሆነ ያውቃሉ። ለኋላኛው ቀን ቅዱሳን፣ አንድ ላይ የሚያስተሳስረን የጋራ አፋይ አለ። ያም የጋራ አካፋይም በምድር ላይ ባለችው የእግዚአብሔር መንግስት እያንዳንዳችን እንድናሟላ የተቀበልነው ጥሪ ነው።

ጥሪው ወደ እናንተ ሲመጣ በማጉረምረም ጥፋተኛ ናችሁ? ወይም የሰማይ አባስ የሚጠራቸውን እንደሚባርክ በማወቅ፣ ወንድሞቻችሁን እና እህቶቻችሁን ለማገልገል የሚሰጣችሁን እያንዳንዱን እድል በምስጋና ትቀበላላችሁ?

የማገልገል የውድ እድላችንን እውነተኛ አላማ እንዳይጠፋብን ተስፋ አለኝ። ያም አላማ፣ ዘለአለማዊው አላማ፣ ጌታ የተናገረው እና በየታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ የሚገኘው ነው፥ “እነሆ፣ የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ስራዬ እና ክብሬ ይህ ነው።”1

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነት እራስን የማመቻቸት ሽፋን ሳይሆን የሀላፊነት ካባ እንደሆነ ሁልጊዜም እናስታውስ። እራሳችንን ከማዳን በተጨማሪ፣ ሀላፊነታችን ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት ለመምራት ነው።

እግዚአብሔርን ማገልገያ መንገድ ላይ ለመራመድ ፈቃደኛ በመሆን፣ ሼክስፒር ስለጻፈበት ካርዲናል ዎዝሊ በምንም አንሆንም። ንጉሱን ለማገልገል ያለው ሀይል በሙሉ ተወስዶበት፣ እንዲህ በሀዘን አለቀሰ፥

ንጉሱን ባገለገልኩ አይነት አምላኬን በግማሽ ቅንአት ባገለግል

በእዚህ እድሜዬ

ለጠላቶቼ በእራቁቴ አይተወኝም ነበር።2

ሰማይ ምን አይነት አገልግሎች ትፈልጋለች? “ጌታ ልብን እና ፍላጎት ያለውን አዕምሮ ይፈልጋል፤ እናም ፍላጎት ያለው እና ታዛዡም በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የፅዮን ምድርን በረከት ይበላሉ።”3

የፕሬዘደንት ጆን ቴይለርን (1808–87) ቃላት ሳስብባቸው ነገሮችን እንዳሰላስል ያደርጉኛል፥ “ጥሪያችሁን ካላጎላችሁ፣ ሀላፊነታችሁን ብታከናውኑ ልታድኑ ለምትችሉት እግዚአብሔር ሀላፊ ያደርጋችኋል።”4

በሰዎች መካከል ሲያገለግል የነበረው የኢየሱስ ህይወት በሀይል እንደሚያበራ ብርሀን አይነት ነው። ኢየሱስ ሸባ ለሆኑት ሰዎች እጆችና እግሮች ጥንካሬ፣ ለአይነ ስውር ሰዎች አይኖች ብርሀን፣ ለደንቆሮዎች ጆሮ ድምጽ፣ እና ለሞተው ሰውነት ትንፋስ ሲያመጣ “እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል ነኝ”5 በማለት አውጇል።

በመልካሙ ሰማራዊ ምሳሌ፣ መምህር ጎረቤታችንን እንደ እራሳችን እንድንወድ አስተምሮናል።6 ለሀብታሙ ወጣት ገዢ በሰጠው መልስም፣ ራስ ወዳጅነታችንን እንድንጥል አስተምሯል።7 5 ሺሆችን በመመገብ፣ የሌሎች ፍላጎቶችን እንድናሟላ አስተምሮናል።8 እናም በተራራ ሰበካው፣ የእግዚአብሔር መንግስትን በመጀመሪያ እንድንፈልግ አስተምሮናል።9

በአዲሷ አለምም፣ ከሞት የተነሳው ጌታ “እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ የእኔ ወንጌል ነው፤ እናም በቤተክርስቲያኔም መስራት ያለባችሁንም ነገሮች ታውቃላችሁና፤ እኔ ስሰራው ያያችሁትን ስራ እናንተም ደግሞ ስሩ፤ ምክንያቱም ስሰራ ያያችሁትን ስራ እናንተም ስሩ።”10

እኛም “የናዝሬቱን ኢየሱስን … መልካም እያደረገ … [በዞረበት]” ጥላ ውስጥ ስናገለግል፣ ሌሎችን እንባርካለን።11 ልጆቹን በማገልገል የሰማይ አባታችንን ስናገለግል እግዚአብሔር ደስታን እንድናገኝ ይባርከናል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

“[ጌታ] ሀላፊነታችንን ካከናወንን እንድንወድቅ አይፈቅድም። ከመጋቢነታችን እና ከችሎታችን በላይ እንድንጎላ ያደርገናል። … ለሰው ዘር ከሚመቱት አስደሳች አጋጣሚዎች ይህ አንዱ ነው” (Ezra Taft Benson፣ in Teaching፣ No Greater Call [1999]፣ 20)። ጌታ የእናንተን ወይም የምታውቁትን ሰው ችሎታ ሲያጎላ የነበረውን አጋጣሚ ለመካፈል አስቡበት። ቤተሰቦች ለተቀበሉት “ለአገልግሎት የሚጠራ የጌታ ጥሪ” መልስ ሲሰጡ የነበራቸውን አጋጣሚዎች እንዲካፈሉ ጋብዟቸው።

አትም