ወጣቶች
የመንፈስ ግፊትን ማዳመጥ
አንድ ምሽት ትንሽዋ ያጎቴ ልጅ ከቤት ጠፋች፣ ስለዚህ እርሷን ለመፈለግ በቶሎ ሄድኩኝ። በመኪና ስነዳም፣ መንፈስ እንዲረዳኝ ጸለይኩኝ። እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠኝ እና እንደሚረዳኝ አውቅ ነበር፣ እናም የመንፈስ ግፊትን ለማዳመጥ ሞከርኩኝ። ምንም በማልሰማበት ጊዜ ግን፣ ተስፋ ቢስ መሆን ጀመርኩ እና መንፈስ እንደማያነሳሳኝ ተሰማኝ።
ምንም እንኳን ካለሁበት ወደ ራቀ ቦታ በመሄድ ለማሰብ ብፈልግም፣ የአጎቴ ልጅ ቤት አጠገብ እንድቆይ ስሜት ተሰማኝ። ስለዚህ በአካባቢው በመኪና እየነዳሁ ለመሄድ ወሰንኩ። በመሻገሪያው ላይ መኪናውን አቁሜ እያለሁ፣ የምትራመድ ወጣት ሴት ልጅን አየሁ። የአጎቴን ልጅ አግኘኋት!
ከመኪናው ወጥቼ ወደ እርሷ ስሮጥ፣ መንፈስ ባለሁበት አካባቢ እንድቆይ በማድረግ ይመራኝ እንደነበረም ገባኝ። ጸጥታ የሆነ ድምጽ አዳምጥ ስለነበረ፣ የመንፈስ ግፊትን ችላ ብዬ ነበር። ከዚያም በአብዛኛው ጊዜ ድምጽ እንደማንሰማ፣ ነገር ግን የሚሰማን ልባችንን የሚነካ ስሜታ እንደሆነ ተረዳሁ።
ከመንፈስ ለተሰጠኝ ምሪት በጣም ምስጋና ይሰማኛል። በእውነትም ሁልጊዜ እዚያ ይገኛል። ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚሉት፣ “መንፈስ ቅዱስም የዘወትር ባልንጀራህ ይሆናል” (ት. እናቃ. 121፥46)።
ለመንፈስ ቅዱስ አመራር ብቁ ከሆንን እና ትኩረት የምንሰጥ ከሆንን፣ በእግዚአብሔር እጅ ለብዙ ሰዎች መልካም ለማድረግ መሳሪያዎች ለመሆን እንችላለን። ከመንፈስ ጋር ሁልጊዜ ባልንጀራ በመሆን፣ በየትኛው መንገድ መሄድ እንደሚገባን እናውቃለን።