2013 (እ.አ.አ)
የወንጌል ተልእኮ ስራ
ጃንዩወሪ 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክቶት፣ ጥር 2013 (እ.አ.አ)

የወንጌል ተልእኮ ስራ

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የወንጌል ሰባኪነት ስራ በተጨማሪ የሆነውን “በጌታ ወይን ስፍራ ለሰዎች የነፍስ ደህንነት እንዲያገለግሉ” ተልከዋል (ት. እና ቃ 138፥56)። ወንጌልን ለማካፈል መደበኛ የወንጌል ሰባኪነት ጥሪ አያስፈልገንም። ህይወታቸው በወንጌል ሊባረክ የሚችሉ ከበውን ይገኛሉ፣ እናም እራሳችንን ስናዘጋጅ፣ ጌታ ይጠቀምብናል። የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች መንፈሳዊ ሀላፊነቶቻቸውን ለማቀፍ እና “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ለማምጣት” ይችላሉ (ሙሴ 1፥39)።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበርን በ1842 (እ.አ.አ) ሲያደራጅ፣ ሴቶች ድሆችን መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ደግሞም ነፍሳትን ማዳን አለባቸው ብሏል።1 ይህ አሁንም አላማችን ነው።

የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ እንዳሉት “ጌታ…ከሌሎች ለሚያካፍሉት የእውነት ምስክርነትን በአደራ ይሰጣል። በተጨማሪም፣ ጌታ የቤተክርስቲያኑ አባላት ‘[ወንጌልን] በደስታ ድምጽ በማወጅ በሁሉም ጊዜ [አንደበታቸውን እንዲከፍቱ]’ ይጠብቅባቸዋል (ት. እና ቃ. 28፥16)። … አንዳንዴም አንድ የምስክርነት ሀረግ የሰውን ህይወት ለዘለአለም የሚቀይር ክስተትን ያስቀምጣል።”2

ከቅዱሳት መጻህፍት

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥20–2318፥15123፥12

ከታሪካችን

ድሮ ሼኮስሎቫኪያ ተብሎ ከምትጠራው አገር የኖረችው የኦልጋ ኮቫሮቫ ታሪክ ከሴቶች መረዳጃ ማህበር ታሪኮች ውስጥ፡የአባላት ወንጌል ሰባኪነት ስራ ምሳሌ ነው። በ1970 (እ.አ.አ) ውስጥ፣ ኦልጋ ለዶክትሬት የምታጠና እና ጥልቅ ለሆነ መንፈሳዊ ህይወት የተራበች ተማሪ ነበረች። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን አባል የሆኑትን የ75 አመት ኦታካር ቮየኩቭካ ተመለከተች። “ለእኔ በእድሜአቸው 75 ቢመስሉም ልባቸው ግን ወደ አስራ ስምንት የቀረበና በደስታ የሞላ ነበር” አለች። “የተጠራጣሪነት ጊዜ በነበረነት በሼኮስሎቫኪያ ውስጥ ይህ በጣም ልዩ ነበር።”

ኦልጋ ኦታካርን እናቤተሰቡን እንዴት ደስታን እንዳገኙ ጠየቀቻቸው። ከሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት ጋር አስተዋወቋት እናም መፅሐፈ ሞርሞንን ሰጧት። በጉጉት አነበበችው እናም ወዲያውም ተጠመቀች እናም ተረገጋገጠች። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ኦልጋ በፖለቲካ ጭቆና እና የሀይማኖት ስደት ባለበት አለም ውስጥ ለመልካም ተፅዕኖ ነበረች። በትንሿ ቅርንጫፏ ውስጥ እንደ ሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት አገለገለች እናም ሌሎችን ወደ ክርስቶስ በማምጣት ነፍሳቸውን ለማዳን እርዳታ ሰጠች።3

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ከምጎበኛቸው ሴቶች ጋር ምስክሬን ሳካፍል የመንፈስ ቅዱስ ግፊትን እከተላለሁ?

  2. የምጠብቃቸው ሴቶችን ወንጌሉን እንዲማሩ እንዴት እየረዳሁ ነኝ?

ማስታወሻዎች

  1. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ስሚዝ (2007)፣ 453 ተመልከቱ።

  2. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Waiting on the Road to Damascus፣” Liahona፣ ግንቦት 2011፣ 76–77።

  3. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 92–95 ተመልከቱ።

አትም