2013 (እ.አ.አ)
ሀዘኔን ለመተው ችዬ ነበር
ሴፕቴምበር 2013


ወጣቶች

ሀዘኔን ለመተው ችዬ ነበር

ደራሲው ከታይዋን ነው።

የጉዋደኛዬ ወንድም ቼን እና ሚስቱ በዋርዳችን በሚጠመቁ ወቅት፣ እጅግ ተደስቼ ነበር። ከጥምቀታቸው ወር በኋላ፣ በቤተመቅደስ ታተሙ፣ እና በቤተክርስቲያኗ አባል ከመሆናቸው በፊት የሞተው ልጃቸው ከእነሱ ጋር ታተመ። እነቼን በወንጌል ጠንክርው ማየት ያስደንቅ ነበር።

ከዛም ወንድም ቼን በቀጣዩ አመት በመኪና አደጋ ሞተ። ከአደጋውም ተከትሎ፣ የሱ ሞት ሁሌም በአእምሮዬ ያለና በህልሜም የሚያስጨነቀኝ ነበር። በእንባም ነቃሁ እና ደጋግሜ ለምን?” ብዬ ጠየኩ። ለምንድን ነው ጌታ እንዲህ አይነት አደጋ እንዲከሰት የሚፈቅደው? ይሄ ነገር እንዴት እዚህ የሚያምር ቤተሰብ ላይ ይከሰታል? አንድ ቀን፣ በእነዚህ ጥያቄዎች ስታገል፣ የትምህርት መምሪያ አነሳሁ እና እነዚህን የፕሬዘዳንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል ቃላት አነበብኩ፡

“ሟችነትን እንደ ሙሉ መኖሪያ ካየነው፣ ህመም፣ ሀዘን፣ ውድቀት፣እና አጭር ህይወት ጥፋት ይሆናሉ። ህይወትን እንደ አለፈው የቅድመ ሟችነት ጊዜ እና እስከ ወደፊት ሞት በኋላ እንደተዘረጋ ዘላለማዊ ነገር ካየነው ግን፣ ከዛም ሁሉም ክስተቶች በትክክለኛው አኳኋን ይቀመጣሉ። …

ከህመም ትዕግስትን እንማርበት ዘንድ፣በሞትም የማንሞት እና የከበርን እንሆን ዘንድ፣ለፈተና የተጋለጥን አይደለምን?1

በዚያ ወቅት፣ ሀዘኔን ለመተው እና ወደ ቃልኪዳንና ወደሚቻለው ወደፊት ለመመልከት ወሰንኩ። ወንድም ቼን ከቤተሰቡ ጋር በደስታ ዳግም ሲቀላቀል በአእምሮዬ አይን ተመለከትኩ። ያ ምልከታ ሰላምን አመጣልን። መከራዎችን እንጋፈጥ ዘንድ የሰማይ አባት ጥበብ እና ብርታትን ይሰጠናል።

ማስታወሻ

  1. Teachings of Presidents of the Church: ስፔንሰር ደብሊው. ኪምቦል (2006) (እ.አ.አ)፣ 82።