2013 (እ.አ.አ)
ለሁሉም ወቅቶች ቅዱሳን
ሴፕቴምበር 2013


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መስከረም 2013 (እ.አ.አ)

ለሁሉም ወቅት ቅዱሳን

በፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ

ለተቀያያሪው የአመቱ ወቅቶች እንደ ፖስትካርድ ምስል የሚያገለግል የአለም ክፍል የሆነ የልጅነት ጊዜ ትውስታ አለኝ። እያንዳንዱ አላፊ ወር የከበረና ድንቅ ነበር። ፍጹም በሆነ የክረምት ቀን፣ በረዶ ተራራዎችን እና የከተማ መንገዶች ተነጥፎ ነበር። ጸደይ የሚያነጣውን ዝናብ እና አረንጓዴ ለባሹን ህይወት አመጣ። ደካማዎቹ የበጋ ሰማዮች ላሸበረቀው ደማቁ ጸሃይ እንደ አስደሳች ሰማያዊ ሸራ ያገለግሉ ነበር። እና ድንቁም መከር ተፈጥሮን ወደ የሚገርም ብርትኳናማ፣ ቢጫ እና ቀይ ጥላ ቀይሮታል። እንደ ልጅነቴ፣ ሁሉንም ወቅቶች እወድ ነበር፣ እስካሁንም ቀን የእያንዳንዳቸውን መገለጫ እና ልዪነት እወዳለሁ

በህይወታችን ውስጥም ወቅቶች አሉን። አንዳንዶቹ ሞቃት እና አስደሳቾች ናቸው። ሌሎች አይደሉም። የህይወታች ጥቂት ቀናቶች የሚያምር የጊዜ መቁጠሪያ ውስጥ እንዳሉ ምሥሎች ናቸው። እናም ግን ለልብ ድካም ምክንያት የሚሆኑ እና ጥልቅ ተስፋ የመቁረጥ፣ የጸጸት እና መራርነት ስሜት ወደ ህይወታችን ሊያመጡ የሚችሉ ቀናት እና ሁኔታዎች አሉ።

በአንድ ጊዜም ሆነ በሌላ ፍጹም ምስላዊ ወቅቶች በተሞላበት መሬት ላይ መኖሪያ መውሰድ እና በመካከል የማያስፈልጉ ጊዜያት ማስወገድ አስደሳች ይሆናል ብለን አስበን እንደምናውቅ እርግጠኛ ነኝ።

ነገር ግን ይሄ የሚቻል አይደለም። ይህም ተፈላጊም አይደለም።

በራሴ ህይወት ላይ ስመለከት፣ አብዛኛው ታላላቅ እድገቶች ወደ እኔ የመጡት ማእበላማ ወቅቶችን እያለፍኩ እያለሁ መሆኑ ግልጽ ነው።

በሁሉም ብልህ የሆነው የእኛ የሰማይ አባት ልጆቹ እንዲሆኑ ወደታቀደው ስሪታዊ ማንነታቸው እንዲያድጉ፣ በምድራዊ ጉዟቸው የአስቸጋሪ ወቅቶች ተሞክሮ እንደሚያስፈልጋቸው ያውቅ ነበር። የመጽሀፈ ሞርሞን ነቢይ ሌሂ ያለተቃርኖ፣ “ቅድስና ሊመጣ አይችልም” ብሏል(2 ኔፊ 2፥11)። በእርግጥም፣ የህይወት መራራነት ነው ጣፋጭነቱን እንድናስተውል፣እንድናነጻጽር እና እንድንደሰትበት የሚያደርገን (ት. እና ቃ. 29፥39ሙሴ 6፥55 ተመልከቱ)።

ፕሬዘዳንት ብሪገም ያንግ እንዲህ አስቀምጠውታል፣ ክብራቸውን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ለማግኘት፣ የክብር፣የዘላለማዊ ነዋሪነት፣ እና የአለሟችነት ዘውድ የተደፋላቸው አእምሮአዊ ብልጽግና ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ አእምሮአዊ ብልጽግና ላላቸው ፍጥረቶች እንዲያልፉበት በተመደበላቸው እያንዳንዱ ስቃይ ማለፍ አለባቸው። ሟች በሆኑ ፍጥረት ላይ ሊመጣ የሚችለውን እያንዳንዱን ጥፋት የሚያሳልፉት ከጌታ ጋር አብሮነትን ለመደሰት እንዲዘጋጁበት ነው። ያለፋቹሁበት እያንዳዱ መከራ እና ተሞክሮ ለደህንነታቹ አስፈላጊ ነው።”1

ጥያቄው የመከራ ወቅቶችን እንደምናሳልፍ ሳይሆን ማእበሉን እንዴት ነው የምንቋቋመው ነው። በሁሌም ተቀያያሪው የህይወት ወቅቶች ውስጥ የእኛ ታላቁ እድል ታማኙን የእግዚአብሔር ቃል አጥብቆ መያዝ ነው፣ የእርሱ ምክር የተቀረጸው የህይወትን ማእበላት እንድንቋቋም ብቻ ሳይሆን አልፈናቸው እንድንሄድ እንዲመራን ነውና። የሰማዩ አባታችን በአስቸጋሪ ወቅቶች ፈተና ውስጥ ወደ ሊነገር የማይችል ደስታ እና ግሩም የዘላለማዊ ህይወት ብርሀን ይመራን ዘንድ የተቀረጸውን ውድ እውቀት የሆነ ቃሉን በነብያት አማካኝነት ሰጥቷል። በተሞክሮአችን መደርደርም ቢሆን እውነትን እና ቅድስናን አጠንክሮ ለመያዝ፣ ጥንካሬን፣ ብርታትን፣ እና ታማኝነትን ማሳደግ የህይወታችን አስፈላጊው ክፍል ነው።

ወደ ውሃ ጥምቀት የገቡ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን የተቀበሉ እግሮቻቸው በደቀመዝሙርነት መንገድ ላይ አስተካክለው እና የአዳኛችንን ተምሳሌት በአጥኖ እና በታማኝነት እንዲከተሉ ሆነዋል።

አዳኛችን እንዳስተማረው ጸሃይ “በክፉውም በመልካሙም ላይ ይወጣል እና በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባል” (ማቴዎስ 5፥45)። አንዳንዴ ለምን አሰቸጋሪ እናም ልክ ያልሆኑ ነገሮች በህይወት ውስጥ እንደሚከሰቱ አንረዳም። ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ተከታይነታችን፣ “በትጋት ፈልጉ፣ ሁሌም ፀልዩ፣ እና አማኞች ሁኑ በቀጥተኝነት ከተጓዝን፣ ሁሉም ነገሮች ለእኛው መልካም በአንድነት ይሰራሉ” ብለን እንመን (ት. እና ቃ. 90፥24፣ ትኩረት ተጨምሯል)።

እንደ እርሱ ቤተክርስቲያን አባልነታችን፣ እንደ ቅዱሳን፣ በሁሉም የአየር ሁኔታ እና በሁሉም ወቅቶች በደስታ እናገለግላለን። እናም እንደዚህ ስናደርግ፣ ልባችን በታላቅ እምነት፣ የማዳን ተስፋ እና መለኮታዊ ልግስና ልቦቻችን እየተሞሉ ይመጣሉ።

አሁንም ቢሆን፣ አስደሳችም አሳማሚም በሆኑ ወቅቶች ሁሉ ውስጥ ማለፍ ይኖርብናል። በማንኛውም ወቅት ግን፣ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች፣ ወደ እርሱ ብርሃን ስንጓዝ ተስፋችንን በእርሱ ላይ እናሳርፋለን።

በአጭሩ፣ ስለ እርሱ ለመማር፣ እርሱን ለመውደድ እና ባላገራዎቻችንን ለመውደድ የወሰንን የእግዚአብሔር ቅዱሳን ነን። በተባረከው በደቀመዝሙርነት መንገድ ላይ ተሳላሚዎች ነን፣ እና ወደ ሰማያዊው አላማችን በጽናት እንጓዛለን።

ስለዚህ፣ በጸደይ፣ በበጋ፣ በበልግ፣ እና በክረምትም ቅዱሳን እንሁን። በሁሉም ወቅቶች ቅዱሳን እንሁን።

ማስታወሻ

  1. Teachings of Presidents of the Church: Brigham Young (1997)፣ 261–262።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ቀዳማዊ አመራር እንዳስተማሩት፣ “አንዳንድ ታላላቅ ትምህርቶች የተሰበኩት መዝሙር በመዘመር ነው” (Hymns, ix)። ይህን መልእክት ስታካፍሉ፣ ከምታስተምሯቸው ጋር ከእነዚህ አንዱን ወይም ሌላ በመከራ ስለ መጽናት መዝሙር ለመዘመር አስቡ፥ “እንዴት ጽኑ መሰረት ነው”(ቁጥር 10)፤ “The Lord Is My Shepherd”(ቁጥር 108)፤ ወይም “Let Us All Press On” (ቁጥር 243)። የመገፋፋት ስሜት ከተሰማቹህ፣ በህይወት የነበራችሁ ማእበላማ ወቅት እንዴት ወደ በረከትነት እንደተቀየረ አካፍሉ።