2013 (እ.አ.አ)
በእራስ መመካት
ሴፕቴምበር 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ መስከረም 2013 (እ.አ.አ)

እራስን መቻል

ይህን መልእክት አጥኑ እና እንደተገቢነቱ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

እራስን መቻል ለራሳችን እና ለቤተሰቦቻችን መንፈሳዊ እና ጊዜያዊ ደህንነት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፣ ውሳኔ እና ጥረት ነው።1

በቤታችን እና በማህበረሰቦቻችን ውስጥ ራስን ስለመቻል መሰረታዊ ሃሳብ ስናስተምር እና ስንተገብር፣ ድሆችን እና መጽዋቾችን የመንከባከብ እና በመከራ ጊዜ መጽናት ይችሉ ዘንድ ሌሎችንም እራሳቸውን እንዲችሉ ለመርዳት እድሎችን እናገኛለን።

ነጻ ምርጫችንን ተጠቅመን በመንፈሳዊም እና በምድራዊም እራሳችንን የመቻል ልዩ መብት እና ሃላፊነት አለብን። እራስን ስለመቻል እና በሰማዩ አባታችን ላይ ጥገኝነት በመናገር፣ ከአሰራ ሁለቱ ሐዋርያት ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሄልስ እንዳስተማሩት፣ “በጸሎት መንፍስ ሆነን ቅዱስ ቁርባን በመካፈል፣ ለቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ብቁ በመሆን፣ እና ሌሎችን ለማገልገል በመሰዋት ቃልኪዳናችንን ስንኖር የተለወጥን እና በመንፈሳዊ እራሳችንን የቻልን እንሆናለን።2

በጊዜያዊም እራሳችንን የቻልን እንድንሆን ሽማግሌ ሄልስ መክረውናል፣ “ይሄም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በላይ ወይም የሙያ ስልጠና ማግኘት፣ ለመስራት እና ባለን ገቢ መኖርን መማርን ያካትታል። እዳን በማስወገድ እና አሁን ገንዘብ በማጠራቀም፣ ለመጪው አመታት ሙሉ ጊዜ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ተዘጋጅተናል። በጊዜያዊም በመንፈሳዊም እራስን መቻል ዋናው አላማ እራሳችንን ወደ ከፍታ ቦታ በማድረግ እርዳታ የሚሹ ሌሎችን ለማንሳት እንድንችል ነው።”3

ከቅዱሳት መጻህፍት

ማቴዎስ 25፥1–131 ጢማቴዎስ 5፥8አልማ 34፥27–28ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 44፥658፥26–2988፥118

ከታሪካችን

የኋለኛው-ቀን ቅዱሳን በሶልት ሌክ ሸለቆ ከተሰበሰቡ በኋላ፣ ፕሬዘዳንት ብሬጌም ያንግ ለመበልጸግ እና ቋሚ ቤቶችን እንዲያቋቁሙ ፈልገዋቸው ነበር። ይህም ማለት ቅዱሳን በራሳቸው በቂ ለመሆን የሚያስችላቸውን ሙያ ይማሩ ዘንድ አስፈልጓቸው ነበር። በዚህ ጥረት ውስጥ፣ ፕሬዘዳንት ያንግ በሴቶቹ ብቃት፣ ተሰጥኦ፣ እምነት እና ፈቃደኛነት ታላቅ አመኔታ ነበራቸው፣ እና በተወሰኑ ጊዜያዊ ሀላፊነቶች ውስጥ አበረታተዋቸው ነበር። የተወሰኑ የሴቶች መረዳጃ ሀላፊነቶች ባሁን ጊዜ ቢለዩም፣ መሰረታዊ ሃሳቦቹ አንድ ሆነው ቆይተዋል፡

  1. ስራ መውደድን ተማሩ እና ስራ ፈትነትን አስወግዱ።

  2. የግል መስዋዕት መንፈስን አግኙ።

  3. ለመንፈሳዊ ጥንካሬ፣ ጤንነት፣ ትምህርት፣ ስራ፣ ገንዘብ፣ ምግብ፣ እና ህይወትን ለመቀጠል አስፈላጊ ለሆኑ ሌሎችም የግል ሀላፊነትን ተቀበሉ።

  4. ለእምነት እና ፈተናዎችን ለመቋቋም ብርቱነት ጸልዩ።

  5. ሌሎች እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን አጠንክሯቸው።4

ማስታወሻዎች

  1. Handbook 2: Administering the Church (2010)፣ 6.1.1 ተመልከቱ።

  2. ሮበርት ዲ. ሄልስ፣“Coming to Ourselves: The Sacrament, the Temple, and Sacrifice in Service፣” Liahona and Ensign፣ግንቦት 2012 (እ.አ.አ)፣ 34።

  3. ሮበርት ዲ. ሄልስ፣ Coming to Ourselves፣” 36።

  4. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 51 ተመልከቱ።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እንዴት ነው እኔ የምጠብቃቸውን እህቶች በጊዜያዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶቻቸው መፍትሄ እንዲያገኙ የምረዳቸው?

  2. ለቅዱስ ቁርባን በመዘጋጀት እና ለአገልግሎት በመሰዋት መንፈሳዊ ራስ መቻልን እያጎለበትኩ ነውን?

አትም