2013 (እ.አ.አ)
መጽሐፈ ሞርሞን ማካፈል እችላለሁን?
ዲሴምበር 2013


ወጣቶች

መጽሐፈ ሞርሞን ማካፈል እችላለሁን?

ደራሲው በዋሽንግተን፣ ዩ.ኤስ.ኤ ይኖራል።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ አመቴ ወቅት፣ የሴሚናሪ አስተማሪዬ አባል ላልሆኑ ጓደኞች መጽሐፈ ሞርሞን እንድንሰጥ የእኔን ክፍል ጋበዘ። በአስገራሚ ሁኔታ ፈሪ ብሆንም፣ ግብዣውን ተቀበልኩ።

ብርታትን ለመገንባት ጥቂት ቀናት ፈጀብኝ፣ ነገር ግን በስተኋላ ለጓደኛዬ ብሪትኒ በምሳ ሰአት መጽሐፉን ሰጠሁና አጭር ምስክርነት አካፈልኩ። ብሪትኒ ለመጽሐፉ አመሰገነችኝ።

በዚያ የትምህርት አመት መጨረሻ ላይ፣ ብሪትኒ ቤት ቀይራ ሄደች፣ ግን መገናኘታችንን አላቆምንም። ስለ አዲሱ ትምህርት ቤቷ እና እንዴት በአብዛኛው ጓደኞቿ የቤተክርስቲያኗ አባል እንደነበሩ ነገረችኝ፣ ግን ከእኔ ጋር ምንም መንፈሳዊ ነገር አላወራችም ነበር።

ለሚስኦናዊ አገልግሎት ከመሄዴ በፊት ያ ተቀየረ። ለእኔ ትልቅ ዜና አለኝ የሚል መልእክት ከብሪትኒ ደረሰኝ፥ ልትጠመቅ ነበር፣ እናም ጓደኛዋ በመሆኔ እና ጥሩ ምሳሌ ስላሳየሁ ልታመሰግነኝ ፈልጋ ነበር።

እግዚአብሔር ሚስኦናዊነት ልምድ ያልነበረው አንድ አይን አፋር የሆነ የ15 አመት ወንድ ልጅ ወሰደ እና እንደምትቀበል ወዳወቃት አንድ ሰው ወንጌል እንዲያካፍል መራው። መንፈስ ቀዱስን በመስማት፣ በዳግም ስለተመለሰው ወንጌል ለመማር የሚጠብቁ በአከባቢያችን ያሉ ሰዎችን ሁላችንም ማግኘት እንደምንችል አውቃለሁ። አንድ ሰው እንኳን ወደ ጌታ በማምጣት ከረዳን፣ “በ(እኛ) አባት መንግስት ውስጥ ከእሱ (እሷ) ጋር ደስታችን እንዴት ታላቅ [እንደሚሆን]!” አውቃለሁ። ት. እና ቃ. 18፥15