2013 (እ.አ.አ)
ቤተሰብ እና ጓደኞች ለዘለአለም
ዲሴምበር 2013


የቀዳሚ አመራ መልእክት፣ ታህሳስ 2013 (እ.ኤ.አ)

ቤተሰብ እና ጓደኞች ለዘለአለም

ምስል
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. አይሪንግ

የትም ብትኖሩ፣ በዳግም የተመለሰውን ወንጌል በመኖራችሁ ያገኛችሁትን ታላቅ ደስታ እየፈለጉ ያሉ ጓደኞች አሏቹህ። ያንን ደስታ በቃላት መግለጽ አይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን በእናንተ ህይወት ሲመለከቱት ያስተውሉታል። በተለይ ልክ እነሱን እንደሚያጋጥማቸው እናንተንም መከራ ሲገጥማቹህ ሲያዩ፣ የዛን ደስታ ምንጭ ለማወቅ ይጓጓሉ።

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ስትጠብቁ ደስታ ተሰምቷችኋል። ያ ቃል የተገባው ወንጌልን የመኖር ፍሬ ነው (ሞዛያ 2፥41 ተመልከቱ)። በሌላ ሰዎች ለመታየት የጌታን ትእዛዛት በእምነት አትጠብቁም፣ ነገር ግን የእናንተን ደስታ የሚመለኩቱ በዳግም የተመለሰውን ወንጌል መልካም ዜና ለመስማት በጌታ እየተዘጋጁ ናቸው።

የተሰጧችሁ በረከቶች ሃላፊነቶች እና አስደናቂ እድሎችን ለእናንተ ፈጥረዋል። እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ የቃልኪዳን ደቀመዝሙር፣ የሚጨምር ደስታ ሌሎች የሚያገኙበትን ዕድል ለሌሎች፣ በተለይም ለጓደኞቻችሁ እና ለቤተሰብ አባላቶቻችሁ፣ ለማካፈል ሃላፊነት አለባችሁ።

የእናንተን እድል ተመልክቶ ጌታ ሃላፊነታችሁን በዚህ ትእዛዝ ገልጿል፥ “የተጠነቀቀው ሰው ባልንጀራውን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው” (ት. እና ቃ. 88፥81)።

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ስትቀበሉና ስትኖሩት በሚከሰቱት ለውጦች አማካኝነት ትእዛዝ ለመጠበቅ የቀለለ እነዲሆን ጌታ ያደርጋል። በውጤቱም፣ ለሌሎች ያላችሁ ፍቅር እናም እናንተ የተደሰታችሁበትን እነርሱም እንዲኖራቸው ያላችሁ ፍላጎት ይጨምራል።

የዚያ ለውጥ አንዱ ምሳሌ በጌታ ሚስኦናዊ ስራ ለመርዳት አጋጣሚን እንዴት እንደምትቀበሉ ነው። የሙሉ ጊዜ ሚስኦኖች የሚያስተምሯቸው ሰዎች እንዲጠቆሙላቸው በሚጠይቁበት ጊዜ በእውነት ከተለወጡት ድምቅ መልስ ለአማግኘት እንደሚችሉ ወዲያው ይማራሉ። የተቀየሩት ለጓደኞች እና ለቤተሰብ አባላት ደስታቸውን ለማካፈል ይጓጓሉ።

የአጥቢያቹህ ሚስኦን መሪ ወይም ሚስኦኖች ለማስተማር የሰው ስም ሲጠይቁ፣ ይህ ለእናንተ ታላቅ ሙጋሴ ነው። ጓደኞች የእናንተን ደስታ ማየታቸውን እና፣ ስለዚህ፣ እነዚያ ጓደኞች ወንጌልን ለመስማት እና ለመቀበል ለመምረጥ እንደተዘጋጁ ያውቃሉ። ወደ መንግስቱ ሲመጡ የሚያስፈልጓቸው ጓደኞች እንደምትሆኑ መተማመን አላቸው።

ሚስኦኖች ከእነርሱ ጋር እንዲገናኙ በመጋበዛችሁ ጓደኞቻችሁን እናጣለን ብላችሁ አትፍሩ። ሚስኦኖችን ባይቀበሉም፣ ለእኔ ውድ መሆኑን የሚያውቁትን ነገር በማካፈሌ ለብዙ አመታት ያመስገኑኝ ጓደኞች አሉኝ። ደስታን እንዳመጣላችው የሚመለከቱትን ወንጌል በማካፈል ጓደኞች ለዘለአለም ማፍራት ትችላላችሁ። ጓደኛ እና በተለይም የቤተሰብ አባል የደስታ ዕቅድን ለመከተል እንዲመርጡ ለመጋበዝ አጋጣሚው በፍጹም አይለፋቹህ።

በቤተክርሰቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ እንዳለው ለዚያ ግብዣ ሌላ ታላቅ አጋጣሚ የለም። በእዚያ በህይወት ሊቀበሉ ላልቻሉት ለጥንት ዘመዶቻችን ጌታ የደህንነትን ስነስርአትን ሊያበረክት ይችላል። በፍቅር እና ተስፋ ወደታች ወደ እናንተ ይመለከታሉ። ወደ እሱ መንግስት ውስጥ ለመምጣት እድሉ እንደሚኖራቸው ጌታ ቃል ገብቷል (ት. እና ቃ. 137፥7 ተመልከቱ)፣ እና በልባቹህ ውስጥ ለእነርሱ ፍቅር 2.እንዲኖራችሁ ተክሏል።

ልክ ለሚስኦናዊ አገልጋዮች የሰዎች ስም ስትሰጡ እንደምታደርጉት ሁሉ፣ አብዛኞቻችሁ ለሌሎች የቤተመቅደስን ስነስርአት በማካፈል ደስታ ተሰምቷችኋል፣ ። ለጥንት ዘመዶቻችሁ ስነስረአቶችን ስትፈጽሙ እንዲያውም ታላቅ ደስታ ተሰምቷችኋል። በምትክ በሚሰራ የቤተመቅደስ ስነስረአቶቸ ለጥንት ዘመዶቻችን የበረከቱን መንገድ በማካፈል ብቻ የዘላለማዊ ደስታችን የሚቻል እንደሆነ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ተገልጾለት ነበር (ት. እና ቃ. 128፥18 ተመልከቱ)።

የገና ወቅት ልባችንን ወደ አዳኝ እና የእርሱ ወንጌል ወዳመጣልን ደስታ ያዞረዋል። ያንን ደስታ ለሌሎች ስናካፍል በይበልጥ አመስጋኝ መሆናችንን ለእርሱ እናሳያለን። ለሚስኦኖች ስሞችን ስንሰጥ እና የጥንት ዘመዶቻችንን ስም ወደ ቤተመቅደስ ስንወስድ ምስጋና ወደ ደስታ ይቀየራል። የምስጋናችን ማሳያውም ለዘላለም የሚጸኑ ጓደኞች እና ቤተሰቦችን ሊያፈራ ይችላል።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ፕሬዘዳንት አይሪንግ ለሌሎች ወንጌልን በማካፈል ለጌታ ምስጋናችንን ማሳየት እንደምንችል ያብራራሉ። ከምታስተምሯቸው ጋር የወንጌል ስጦታ እንዴት ህይወታቸውን እንደባረከው መወያት ትችላላቹህ። የወንጌል ስጦታን ለማካፈል የሚፈልጉትን ሰው በጸሎት መንፈስ እንዲመርጡ እና እንዴት ማደረግ እንደሚችሉ ለመጋበዝ አስቡበት።

አትም