2013 (እ.አ.አ)
የአንድያው ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልእኮ
ዲሴምበር 2013


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ታህሳስ 2013 (እ.ኤ.አ)

የአንድያው ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልእኮ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደreliefsociety.lds.org ሂዱ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርሰቶስ፣ አንድያ ልጅ ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም እርሱ ሟች በሆነች እናት እና ሟች ባልሆነ አባት በምድር ላይ የተወለደ ብቸኛው ሰው ነው። ከአባቱ እግዚአብሔር መለኮታዊ ሀይልን ወርሷል። ከእናቱ፣ ማሪያም፣ ሟችነትን ወርሷል እና ለረሀብ፣ ጥማት፣ ድካም፣ ህመም እና ሞት ተጋላጭ ነበር።1

ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ አንድያ ልጅ ስለሆነ፣ ህይወቱን አሳልፎ ለመስጠት እና መልሶ ለማንሳት ይችል ነበር። ቅዱሳን መጻህፍት እንደሚያስተምሩት “በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት፣” እኛ “ትንሳኤን እናገኛለን” (ያዕቆብ 4፥11)። እኛ “የምናምን ከሆነ” ሁሉም “ሟች ባልሆነ የዘለአለማዊ ህይወት እንደሚነሱ” ተምረናል (ት. እና ቃ. 29፡43)።

በሙሉነት የኢየሱስ የአብ አንድያ ልጅ መሆን ምን ማለት እንደሆነ እየገባን ሲመጣ፣ በክርስቶስ ያለን እምነታችን ይጨምራል። ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን እነዳሉት፣ “በኢየሱስ ክርሰቶስ ማመን (1) የእርሱ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅነት፣ (2) የእርሱ የማያልቀው የኃጢያት ክፍያ፣ እና (3) የእርሱ ትንሳኤ አመኔታ እና ማረጋገጫ ነው።2 የዘመኑ ነቢያት እንደመሰከሩት፥ “[ኢየሱስ ክርስቶስ]…በስጋ አንድያ ልጅ፣ የአለም አዳኝ ነበር።”3

ከቅዱሳት መጻህፍት

ዮሀነስ 3፡16ትምህርት እና ቃልኪዳን 20፥21፣ 24ሙሴ 5፥6፣9

ከታሪካችን

በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በስም ቢጠቀሱ እና ባይጠቀሱም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን የተለማመዱ፣ የተማሩ እና የእርሱን ትምህርት የኖሩ፣ እና ስለ አገልግሎቱ፣ ተአምራቱ እና ድንቅነቱ ስለመሰከሩ ሴቶች እናነባለን። እነዚህ ሴቶች ምሳሌያዊ ደቀመዛሙርት እና በደህንነት ስራ ውስጥ አስፈላጊ ምስክሮች ሆነዋል።

ለምሳሌ፣ ማርታ ለእርሱ እንዲህ በማለት የአዳኙን መለኮታዊነት ጠንካራ ምስክርነት አካፍላለች፣ “ወደ አለም መምጣት የነበረብህ፣ የእግዚያብሄር ልጅ፣ ክርስቶስ እንደሆንክ አምናለሁ” (ዮሀነስ 11፥27)።

ቀደም ካሉት የአዳኝ መለኮታዊነት ምስክሮች እናቱ፣ ማርያም፣ እና የእህቷ (ወንድሟ) ልጅ ኤልሳ ነበሩ። መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ከጎበኛት በኋላ፣ እሷ ኤልሳን ጎበኝች። ኤልሳ የማርያምን ሰላምታ ልክ እንደሰማች፣ እሷ “በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ነበር”(ሉቃስ 1፥41) እና ማርያም ለእግዚያብሔር ልጅ እናት እንደምትሆን መሰከረች።

ማስታወሻዎች

  1. የወንጌል መሰረተ ሀሳቦች (2009)፣ 52 እና 53 ተመልከቱ።

  2. ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “በክርሰቶስ እምነት መገንባት፣” Liahona, መስከረም 2012፣ 13።

  3. “ህያዉ ክርሰቶስ፡ የሀዋርያት ምስክርነት፣” Liahona፣ ሚያዝያ 2000፣2 እና 3።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. የኢየሱስ ክርስቶስን ሚናዎች መረደት ለምን ያስፈልገኛል?

  2. ቃል ኪዳኖቻችንን ስናከብር እምነታችን እንዴት ይጨምራል?