2013 (እ.አ.አ)
ምስክርነታችሁን አካፍሉ
ዲሴምበር 2013


ልጆች

ምስክርነታችሁን አካፍሉ

ለጓደኛ ወይም ለጎረቤት በውስጡ ምስክርነታችሁ የተጻፈበት መፅሐፈ ሞርሞን በመስጠት የወንጌልን ስጦታ በዚህ ገና ለማካፈል ትችላላችሁ። ያንን ዝግጁ ለማድረግ እነዚህን ደረጃዎች ተከተሉ፥

  1. በብጣሽ ወረቀት ላይ፣ ወደ 4½ x 6½ ኢንች (11½ x 16½ ሴ.ሜ) የሚሆን አራት ማዕዘን ያለው ክፍልን ለኩ እና ጎልማሳ ሰው ቆርጦ በማውጣት እንዲረዷችሁ አድርጉ።

  2. በገጹ ከላይ በስእል ወይም በፎቶ የእናንተን ምስል ጨምሩ።

  3. ከምስላቹህ ስር ምስክርነታችሁን ጻፉ።

  4. ጎልማሳ ሰው በውስጠኛው የመጽሐፈ ሞርሞን ሽፋን ላይ ወረቀቱን በመለጠፍ እንዲረዳችሁ አድርጉ።