ልጆች
የፍቅር ትስስሮች
አንድ አዋቂ ሰው እያንዳንዳቸው ስፋታቸው 1 ኢንች (2.5 ሴ.ሜ) እና ርዝመታቸው 8 ኢንች (20 ሴ.ሜ) አካባቢ የሆነ 28 ቀጭን ብጥስጣሽ ወረቀት ለመቆራረጥ እንዲረዷችሁ አድርጉ። በዚህ ወር ውስጥ በየቀኑ ፍቅራችሁን ለአንድ ሰው ለማሳየት የአገልግሎት ተግባር ፈጽሙ። ቤታቹን በማጽዳት ወላጆቻችሁን ለመርዳት ወይም ለጎረቤት መልካም ማስታወሻ ለመጻፍ ትችላላችሁ።
በየቀኑ እንዴት እንዳገለገላቹ በአንዱ ብጥስጣሽ ወረቀታቹ ላይ ጻፉ፣ እናም ከዛ ክብ ለመስራት የብጣሽ ወረቀቱን ጫፎች በአንድ ላይ በፕላስተር ወይም በማጣበቂያ አያይዟቸው። የአዲሱን ብጣሽ ወረቀት ጫፎች በአንድ ላይ በፕላስተር ወይም በማጣበቂያ ከማያያዛቹ በፊት የአዲሱን ብጣሽ ወረቀት አንድ ጫፍ ካለፈው ቀን ክቡ ስር በማድረግ ክባችሁን ማገናኘት ትችላላችሁ። የፍቅር ትስስራችሁ ሲያድግ ተመልከቱ! የካቲት ካለፈም በኋላ የአገልግሎት ሰንሰለታችሁ ላይ መጨመራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።