ወጣቶች
የአገልግሎት በጋ
ደራሲዋ በቨርጂንያ ዩኤስኤ ነው የምትኖረው።
አንድ በጋ ላይ በእንግዳ ሀገር ውስጥ ልዩ ፍላጎቶች ከሚያስፈልጋቸው ልጆች ጋር በመስራት ጊዜ አሳለፍኩኝ። ልጆቹን በመጀመሪያ ሳገኛቸው በጣም ተደናግጬ ነበር። ቋንቋቸውን አልናገርም ነበር፣ ነገር ግን በእኔ ግንኙነቶች ውስጥ መንፈስ እንደሚመራኝ አመንኩኝ። እያንዳንዱን ልጅ እያወኩኝ ስመጣ፣ ቋንቋ ለፍቅር መሰናክል እንዳልሆነ ተገነዘብኩኝ። ተጫወትኩኝ፣ ሳኩኝ እና ከልጆቹ ጋር በእጅ የሚሰሩ ነገሮችን ሰራሁ እናም ለእነሱ የተሟላ ፍቅር ከመሰማት በስተቀር እራሴን መቆጠብ አልቻልኩኝም ነበር። የሰማይ አባት ለልጆቹ ያለውን ፍቅር አየሁ፣ እናም ልቤን የሞላው ደስታ ይህ ነው የማይባል ነበር።
ሌሎችን በማገለግልበት ጊዜ፣ ለእነኛ ለማገለግላቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለሰማይ አባትም ፍቅር ይሰማኛል። “እናንተ ሰዎችን በምታገለግሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን ብቻ እያገለገላችሁ እንደሆነ…” (ሞዛያ 2፥17) የሚለውን በእውነተኛነት እያወኩኝ መጥቻለው። የአገልግሎቴ አላማ፣ በትልቅ የአገልግሎት ፕሮጀክት ውስጥም ሆነ በትንሽ የመልካም ተግባሮች፣ እግዚአብሔርን ለማክበር ነው ( ማቴዎስ 5፥16 ተመልከቱ)። ሌሎችን ሳገለግል፣ ለሰማይ አባት ያለኝን ፍቅር እና በውስጤ የሚቃጠለውን የክርስቶስን ብርሃን ሰዎች እንደሚገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ።