2014 (እ.አ.አ)
ጌታን በፍቅር አገልግሉ
ፌብሩወሪ 2014


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ የካቲት 2014 (እ.ኤ.አ)

ጌታን በፍቅር አገልግሉ

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው፣ “ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል” ሉቃስ 9፥24

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዳሉት፣ “አዳኝ ሌሎችን በማገልገል ስራ ውሰጥ እራሳችንን አሳልፈን ካልሰጠን በስተቀር፣ ለሕይወቶቻችን ጥቂት አላማ እንዳለ እየነገረን እንደሆነ አምናለሁ። ሌሎችን በማገልገል ስራ ውስጥ እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ሲያድጉና ሲበለፅጉ — እናም በውጤቱ ህይወታቸውን ሲያድኑ፤ ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ ቀስ በቀስ ይጠወልጋሉ እናም በዘይቤያዊ አነጋገር ህይወታቸውን ያጣሉ።1

በሚከተለው የፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን አገልግሎት ምንባብ ውስጥ፣ የኃለኛው ቀን ቅዱሳኖችን የእግዚአብሄር እጆች እንደሆኑ እና ሌሎችን በታማኝነት ለሚያገለግሉ የዘላለም በረከቶች እንደሚጠብቃቸው እንዲያስታውሱ አድርገዋል።

አገልግሎት በቤተመቅደስ ውስጥ

“ከመጋረጃው ባሻገር ለሄዱት የውክልና ስርአቶችን ስንፈፅምላቸው ታላቅ አገልግሎት ይሰጣል። ብዙውን ጊዜ ስራውን የምንፈጽምላቸውን ሰዎች አናውቃቸውም። ምስጋናዎችን አንጠብቅም፣ እንዲሁም የምናቀርበወን እንደሚቀበሉ ዋስትና የለንም። ይሁን እንጂ፣ እናገለግላለን፣ እናም በዛ ሂደት ውስጥ በሌላ ሙከራ የማይመጣውን እናገኛለን፥ በእርግጥም በፅዮን ተራራ ላይ አዳኞች እንሆናለን። አዳኛችን ህይወቱን ለእኛ የውክልና መስዋዕትነት እንደሰጠ ሁሉ፣ እኛም በተወሰነ መጠን ለእነሱ በእኛ በምድር ላይ ባለነው የሆነ ነገር ካልተደረገላቸው በስተቀር ወደፊት መጓዝ ለማይችሉት በቤተ-መቅደስ ውስጥ የውክልና ስራን ስንፈፅምላቸው ተመሳሳይ ነገር እናደርጋለን።2

እኛ የጌታ እጆች ነን

“ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የቤተሰብ አባል፣ ጓደኞች፣ የምናውቃቸው፣ ወይም እንግዳዎች ቢሆኑም፣ የእኛን ትኩረት፣ ማበረታታት፣ እርዳታ፣ ማፅናናት፣ ደግነት በሚፈልጉ ሰዎች ተከበናል። በዚህ ምድር ላይ እኛ ልጆቹን የማገልገል እና የማንሳት ጭምር አደራ ያለን የጌታ እጆች ነን። በእያንዳንዳችን ላይ ጥገኛ ነው። …

“ሁላችንም የተጠራንበት አገልግሎት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ነው።”3

በአዳኝ ጥላ ስር ማገልገል

“በአዲሷ አለምም፣ ከሞት የተነሳው ጌታ ‘እናም በቤተክርስቲያኔም መስራት ያለባችሁንም ነገሮች ታውቃላችሁና፤ እኔ ስሰራው ያያችሁትን ስራ እናንተም ደግሞ ስሩ፤ ስሰራ ያያችሁትን ስራ እናንተም ያን ታደርጋላችሁ’ [3 ኔፊ 27፥21]።

“እኛም ‘የናዝሬቱን ኢየሱስን … መልካም እያደረገ … በዞረበት’ ጥላ ውስጥ ስናገለግል፣ ሌሎችን እንባርካለን ስራ 10፥38። ልጆቹን በምድር ላይ በማገልገል የሰማይ አባታችንን ስናገለግል እግዚአብሔር ደስታን እንድናገኝ ይባርከን።”4

የማገልገል አስፈላጊነት

“ለማገልገል እድል ሊሰጠን ይገባል። ከእንቅስቃሴ ከተንሸራተቱ ወይም ወደኋላ ለሚቀሩ እና ያለውሳኔ ለሚቆዩ ለእነዚያ አባላት፣ እነሱን ለመርዳት በጸሎት መንገዶችን መፈለግ እንችላለን። እነሱን በተወሰነ አቅም እንዲያገለግሉ መጠየቅ ምናልባት ወደ ሙሉ እንቅስቃሴ ለመመለስ የሚፈልጉት ማበረታቻ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ መርዳት የሚችሉ መሪዎች አንድ አንድ ጊዜ ይህንን ለማድረግ ቸልተኛ ይሆናሉ። ሰዎች መለወጥ እንደሚችሉ በአእምሮአችን ማሰብ ይኖርብናል። መጥፎ ልምዶችን መተው ይችላሉ። ከመተላለፎች ንሰሀ መግባት ይችላሉ። የክህነት ስልጣንን በብቁነት መሸከም ይችላሉ። እናም ጌታን በትጋት ማገልገል ይችላሉ።”5

ማድረግ ያለብንን ሁሉ እያደረግን ነውን?

“አለም የእኛን እርዳታ ፍለጋ ላይ ነች። ማድረግ ያለብንን ሁሉ እያደረግን ነውን? የፕሬዘደንት ጆን ቴይለርን ቃላትም እናስታውሳለን፥ “ጥሪያችሁን ካላጎላችሁ፣ ሀላፊነታችሁን ብታከናውኑ ልታድኑ ለምትችሉት እግዚአብሔር ሀላፊ ያደርጋችኋል።” Teachings of Presidents of the Church: John Taylor (2001)፣ 164። እንዳይወላውሉ የሚደረጉ እግሮች፣ የሚያዙ እጆች፣ የሚበረታቱ አእምሮዎች፣ የሚነሳሱ ልቦች፣ እና የሚድኑ ነፍሶች አሉ። የዘላለም በረከቶች ይጠብቋችኋል። የእናንተ ልዩ እድል ተመልካቾች ሳትሆኑ ነገር ግን በአገልግሎት መድረክ ላይ ተሳታፊዎች እንድትሆኑ ነው።”6

ማስታወሻዎች

  1. “ዛሬ ለአንድ ሰው ምን አደረኩኝ?” Liahona፣ ህዳር 2009፣ 85።

  2. “እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ፣” Liahona፣ ግንቦት 2009፣ 13–14።

  3. “ዛሬ ለአንድ ሰው ምን አደረኩኝ?” 86፣ 87።

  4. “የአዳኝ የአገልግሎት ጥሪ”፣ Liahona፣ ነሐሴ 2012፣ 5”።

  5. “ሌሎችን መሆን አንደሚችሉት እዩዋቸው፣” Liahona፣ህዳር 2012, 68።

  6. “ማገልገል ፍቃደኛ እና ብቁ መሆን፣” Liahona፣ ግንቦት 2012፣ 69።

  7. Teaching, No Greater Call: A Resource Guide for Gospel Teaching (1999)፣ 12።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

“እንደ ክርስቶስ አይነት የሆነ ፍቅር ካላችሁ፣ ወንጌልን ለማስተማር የተሻለ ዝግጁ ትሆናላችሁ። ሌሎች ጌታን እንዲያውቁትና እንዲከተሉት ለመርዳት ትነሳሳላችሁ።”7 ለምትጎበኙዋቸው ሰዎች ተጨማሪ ልግስና እንዲኖራቸው መፀለይን ልብ በሉ። ለእነሱ እንደ ክርስቶስ አይነት የሆነን ፍቅር በምታዳብሩበት ጊዜ፣ ጌታንም ሆነ የምታስተምሯቸውን ሰዎች ትርጉማዊ በሆኑ መንገዶች በተሻለ ሁኔታ ማገልገል ትችላላችሁ።

አትም