2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ መልካም እረኛ
ፌብሩወሪ 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ የካቲት 2014 (እ.ኤ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ መልካም እረኛ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደwww.reliefsociety.lds.org

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ መልካሙ እርኛ፣ እንዳስተማረው፥

“መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበረሀ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? …

“እላችኋለው … ንሰሀ በሚገባ በአንድ ሀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል”ሉቃስ 15፥4፣ 7

ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም እረኛ እንደሆነ እየተረዳን ስንመጣ፣ የእሱን ምሳሌ ለመከተል እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለማገልገል ፍላጎታችን ይጨምራል። ኢየሱስ አለ፥ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፣ የራሴን በጎች አውቃለሁ፣ የራሴ በጎች ያውቁኛል። ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ” ዮሐንስ 10፥14–15)። በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ማንኛችንም የቤታችንን መንገድ እስከምናጣ ድረስ በጭራሽ አንጠፋም (ሉቃስ 15 ተመልከቱ)።

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዲህ አሉ “የእኛ ኃላፊነት መንጋውን መንከባከብ ነው ። እያንዳንዳችን ለማገልገል ከፍ እንበል።”1

ከቅዱሳት መጻህፍት

ምሳሌ 23ኢሳይያስ 40፥11ሞዛያ 26፥21

ከታሪካችን

የመጀመሪያ የሴቶች የመረዳጃ ስብሰባን የተካፈለችው ኤልሳቤት አን ዊትኒ፣ በ1830 ስለ መለወጧ እንደዚ አለች፥ “ሽማግሌዎቹ ወንጌልን ሲሰብኩት በሰማሁበት ሰአት፣ የመልካሙ እረኛ ድምፅ እነደሆነ አወኩኝ።”2 ኤልሳቤት የመልካሙን እረኛድምፅ ተከተለች አናም ተጠመቀች አናም የቤተክርስትያን ማረጋገጫ ተቀበለች።

አኛም የመልካሙን እረኛ ድምፅ መስማት እና የእርሱን ትምህርት ማካፈል እንችላለን። ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳሉት፣ “እኛ በዚህች ምድር ላይ ልጆቹን የማገልገል እና የማንሳት አደራ ያለን የጌታ እጆች ነን።”3

ልክ እረኛ የጠፋ በግን እንደሚፈልግ፣ ወላጆች የጠፋውን ልጅ ሊፈልጉ ይችላሉ። ፕሬዘደንት ጄምስ ኢ ፋውስት (1920–2007) የቀዳማዊ አመራር ሁለተኛ አማካሪ እንዲህ እንዳሉት፥ “የማይታዘዙ ልጆቻቸውን በማስተማር ጻድቅ፣ ትጉህ፣ እና ጸሎታማ ለሆኑት ልባቸውም ለተሰበረው ወላጆች፣ እንዲህ እንላቸዋለን፣ መልካሙ እረኛ እየተመለከታቸው ነው። እግዚአብሔር የእናንተን ጥልቅ ሃዘን ያውቃል እናም ይረዳል። ተስፋ አለ።”4

ማስታወሻዎች

  1. ቶማሰ ኤስ ሞንሰን “የሰማይ ቤቶች፣ ዘላለማዊ ቤተሰቦች” Liahona፣ ሰኔ 2006፣ 70።

  2. ኤልሳቤት አን ዊትኒ፣ በDaughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 128።

  3. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “What Have I Done for Someone Today?” Liahona፣ ህዳር 2009፣ 86።

  4. ጄምስ ኢ ፋውስት፣ “Dear Are the Sheep That Have Wandered” Liahona, May 2003, 68

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. አዳኝ መልካም እረኛ እንደሆነ ማወቅ በሕይወቶቻችን ውስጥ እንዴት ሰላምን ያመጣልናል?

  2. ከቤተክርሰቲያን እንቅስቃሴዎች “ለጠፉት” ወይም የእኛ እምነት ተከታይ ላልሆኑት በምን አይነት መንገድ ማገልገል እንችላለን?

  3. ልጆቻቸው ወንጌልን ከመኖር የጠፉባቸው ወላጆችን እንዴት ለመርዳት እንችላለን?