2014 (እ.አ.አ)
ዋጋ የማይገዛው የተስፋ ውርስ
ግንቦት 2014 (እ.አ.አ)


ዋጋ የማይገዛው የተስፋ ውርስ

ከእግዚአብሔር ጋር ቃል-ኪዳን ለመግባት ወይም ለመጠበቅ ስትመርጡ፣ የናንተን ምሳሌ መከተል ለሚችሉት የተስፋ ውርስን ለመተው ወይም ላለመተው ትመርጣላችሁ።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አንዳንዶቻችሁ ወደዚህ ስብሰባ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሚስዮኖች ተጋባዛችሁ ነበር። እነዛ ሚስዮኖች በመጠመቅ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል-ኪዳን ለመግባት እንድትመርጡ ጋብዘዋችሁ ይሆን ይሆናል።

ሌሎቻችሁ እያዳመጣችሁ ያላችሁት በወላጅ፣ በሚስት፣ ወይም ምናልባት በልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የገባችሁትን ቃል-ኪዳን በሕይወታችሁ መአከላዊ ቦታ ላይ መልሳችሁ እንደምታኖሩ ተስፋ በማድረግ የተዘረጋላችሁን ግብዣን በመቀበላችሁ ምክንያት ይሆናል። እያዳመጣችሁ ያላችሁት አንዳንዶቻችሁ አዳኝን ለመከተል ለመመለስ ምርጫ ያደረጋችሁና የእርሱን የእንኳን ደህና መጣችሁ ደስታ ዛሬ እየተሰማችሁ ያላችሁ ናችሁ።

ማንም ሁኑ እንዲሁን የትም ብትሆኑም፣ አሁን ከምታስቡት በላይ በእጆቻችሁ ውስጥ የብዙ ሰዎች ደስታን ይዛችኋል። በየቀኑና በየሰአቱ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል-ኪዳን ለመግባት ወይም ለመጠበቅ መምረጥ ትችላላችሁ።

የዘላለም ሕይወትን ስጦታ ለመውረስ በሚያስችለው መንገድ ላይ በየትኛውም ቦታ ላይ ብትሆኑም፣ ብዙ ሰዎችን ወደ ታላቅ ደስታ የሚያመራውን መንገድ ለማሳየት እድሉ አላችሁ። ከእግዚአብሔር ጋር ቃል-ኪዳን ለመግባት ወይም ለመጠበቅ ስትመርጡ፣ የናንተን ምሳሌ መከተል ለሚችሉት የተስፋ ውርስን ለመተው ወይም ላለመተው ትመርጣላችሁ።

እናንተና እኔ በዚህ አይነት የውርስ ቃል-ኪዳን ተባርከናል። በሕይወት ውስጥ ብዙ ድስታዎቼን በሟች ሕይወት ውስጥ ፍፅም ላላገኘሁት ሰው አበረክታለው። ከቅድመ-አያቶቼ አንዱ የሆነ ወላጅ አልባ ሕፃን ነበር። ዋጋ የማይገዛው የተስፋ ውርስ ተወልኝ። ያንን ውርስ ለኔ በመፍጠር የተጫወተውን አንዳንድ ክፍሎች ልንገራችሁ።

ስሙ ሔንሪች አይሪንግ ነበር። በታላቅ ሀብት ውስጥ ነበር የተወለደው። አባቱ፣ ኤደዋርድ፣ በኮበርግ አሁን ጀርመን በምትባለው ውስጥ ታላቅ ሀብት ነበረው። እናቱ ባለርስት ቻርሎት ቮን ብሎመበርግ ነበረች። አባቷ የፕረሺያን ንጉስ መሬቶች ጠባቂ ነበር።

ሔንሪች የቻርሎትና የኤድዋርድ የበኩር ልጅ ነበር። ቻርሎት በ31 አመቷ ከሶስተኛ ልጇ መወለድ በኋላ ሞተች። ኤድዋርድ ከዛ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሁሉንም ንብረቶቹንና ሀብቶቹን በመሬት ልማት ውስጥ በማጣት ሞተ። እድሜው 40 አመት ብቻ ነበር። ሶስት ወላጅ አልባ ሕፃናትን ትቶ ሄደ።

ሔነሪች፣ ቅድመ-አያቴ፣ ሁለቱንም ወላጆቹንና ታላቅ አለማዊ ውርስን አጣ። አንድ ሳንቲም እንኳን የለውም ነበር። በታሪኩ ውስጥ የእርሱ ጥሩ እድል ያለው ወደ አሜሪካ በመሄድ ላይ እንደሆነ እንደተሰማው መዘገበ። ምንም እንኳን እዛ ቤተሰብ ወይም ጓደኞች ባይኖሩትም፣ ወደ አሜሪካ የመሄድ የተስፋ ስሜት ነበረው። መጀመሪያ ወደ ኔው ዮርክ ከተማ ሄደ። ከዛ በኋላ ወደ ቅዱስ ሉይስ፣ ሚዙሪ ተጓዘ።

በቅዱስ ሉይስ ውስጥ አንዱ የስራ ባላደረባው የኋለኛው ቀን ቅዱስ ነበር። ከእርሱ በቤተክርስቲያን ሽማግሌ ፓርሊ ፒ ፕራት የተፃፈ የበራሪ ወረቀት ግልባጭ አገኘ። አነበበው፣ ከዛ በኋላ ስለ ኋለኛው ቀን ቅዱሳኖች ማግኘት የቻለውን እያንዳንዷን ቃል አጠና። ለሰዎች የተገለፁት በእርግጥ መልአክቶች መሆናቸውን፣ ሕያው ነብይ እንደነበር እና እውነተኛና የተገለፀ ሐይማኖትን እንዳገኘ ለማወቅ ፀለየ።

ከሁለት ወራት ጥንቃቄ ያለው ጥናትና ፀሎት በኋላ፣ ሔነሪች መጠመቅ እንዳለበት እንደተነገረው ህልም አየ ። ስሙንና ክህነቱን በተቀደሰ ማስታወሻ የማኖረው፣ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ዊሊያም ብራውን ስነ-ስርአቱን እንዲያከናውን ሆነ ። ሔነሪች የዝባብ ውኃ በሞላው ገንዳ ውስጥ ከጠዋቱ 1፥30 ላይ በመጋቢት 11፣ 1855 (እ.አ.አ)ተጠመቀ።

ሔነሪች አይሪንግ በዛ ሰአት ዛሬ የማሰተምረው ነገር እውነት እንደነበር እንደሚያውቅ አምናለው። የዘላለም ሕይወት ደስታ የሚመጣው ለዘላለም በሚቀጥለው የቤተሰብ ትስስሮች አማካኝነት እንደነበር አውቋል። ምንም እንኳን የጌታን የደስታ እቅድ በቅርብ ጊዜ ውሰጥ ሲያገኝ፣ የእርሱ የዘላለም ደስታ ተስፋ በሌሎች የእሱን ምሳሌ የመከተል ነፃ ምርጫዎች ላይ እንደተመረኮዘ አውቋል። የእርሱ የዘላለም ደስታ ተስፋ ገና ባልተወለዱ ህዝቦች ላይ ተመረኮዘ።

እንደ አንድ የቤተሰባችን የተስፋ ውርስ አካል፣ ለዘሮቹ ታሪክን ትቶ አለፈ።

በዛ ታሪክ ውስጥ እርሱን ለምንከተለው ለእኛ ያለው ፍቅር ይሰማኛል። በቃሎቹ ውስጥ ዘሮቹ ወደ ሰማይ ቤታችን በሚመልሰን መንገድ ላይ እርሱን ለመከተል እንዲመርጡ ያለውን ተስፋ ይሰማኛል። ይህንን ለማድረግ አንድ ትልቅ ምርጫ ማድረግ ሳይሆን ነገር ግን ብዙ ትንሽ ምርጫዎችን ማድረግ እንደሆነ አወቀ። ከታሪኩ ውስጥ እጠቅሳለው፥

“ሽማግሌ አንድረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያወራ ከሰማሁበት ጊዜ ጀመሮ---የኋለኛው ቀን ቅዱሳኖችን ስብሰባ ሁልጊዜ ተካፍያለው፣ በተመሳሳይ ሰአት እንደዚህ ማድረግ የኔ ሀላፊነት ሆን ሳለ፣ ወደ ስብሰባው ያልሄድኩባቸው አጋጣሚዎች በእርግጥ በጣም ጥቂት ናቸው።

“ይህንን በታሪኬ ውስጥ ልጆቼ ምሳሌዬን እንዲያስመስሉና ከቅዱሳኖች ጋር መሰብሰብ አስፈላጊ ሀላፊነት መሆኑን በፍፁም እንዳይዘነጉት እሰይመዋለው።”1

ሔነሪች በቅዱስ ቁርባን ውስጥ ኣዳኛችንን ሁልጊዜ እንድናስታውሰውና መንፈሱ ከእኛ ጋር እንዲሆን ቃል-ኪዳናችንን ማደስ እንደምንችል አወቀ።

የጥምቀት ቃል-ኪዳንን ከተቀበለ ከትንሽ ወራቶች በኋላ ብቻ በተጠራበት ሚስዮን ላይ ያ መንፈስ ነበር የደገፈው። እደ ውርሱ በዛ ሰአት የህንድ ድምበሮች ተብሎ በሚጠራው ውስጥ ለሚስዮኑ የስድስት አመታት አማኝ ሆኖ የመቆየት የራሱን ምሳሌነት ትቶ አለፈ። ከሚስዮኑ መልቀቅያን ለመቀበል በግምት 1100 ማይሎች (1770 ኪሎ ሜትሮች) የሚጠጋ ዕርቀትን ከኦክላሆማ ወደ ሶልት ሌክ ከተማ ተጓዘ።

ከዛ በኋላ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በእግዚአብሔር ነብይ ወደ ደቡባማ ዩታ እንዲሄድ ተጠራ። ከዛ በኋላ ወደ ተወለደባት ጀርመን ሚስዮን እንዲያገለግል ሌላ ጥሪ ተቀበለ። ከዛ በኋላ በሰሜናማ ሜክሲኮ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ሰፈራዎችን እንዲገነባ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ግብዣን ተቀበለ። ከዛ በኋላ ወደ ሜክሲኮ ከተማ እንደገና እንደ ሙሉ ጊዜ የሚስዮን አገልጋይ ተጠራ ። እነዛን ጥሪዎች አከበረ። በኮሎኒያ ዧሬዝ፣ ቺኋኋ፣ ሜክሲኮ በትንሽ መቃብር ውስጥ ተቀብሮ ተኝቶ ይገኛል።

እነዚህን እውነታዎች ለእርሱ ወይም ላደረገው ነገር ወይም ለዘሮቹ ታላቅነትን ለመቀበል አላስተጋባም። እነዛን እውነታዎች በልቡ ውስጥ በነበረው ለእምነትና ለተስፋ ምሳሌዎቹ ክብር ለመግለፅ አስተጋባለው።

እነዛን ጥሪዎች ከሞት የተነሳው ክርስቶስ እና የሰማይ አባታችን በኒው ዮርክ ከተማ በጫካ ውስጥ ለየሴፍ ስሚዝ እንደተገለፁለት በነበረው እምነት ምክንያት ተቀበለ። የክህነት ቁልፎች በጌታ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ቤተሰቦችን፤ ቃል-ኪዳናቸውን ለመጠበቅ በቂ እምነት ከነበራቸው ብቻ ለዘላለም የሚያትም ኃይል ተመልሶ እንደተቋቋመ እምነት ስለነበረው ተቀበላቸው።

እንደ ዘሬ ሔንሪች አይሪንግ፣ እናንተ በቤተሰባችሁ ውስጥ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት በሚያመራው በታታሪነትና በእምነት በሚደረጉና በሚጠበቁ የቅዱስ ቃል-ኪዳኖች መንገድ ላይ ፈር ቀዳጅ ልትሆኑ ትችላላችሁ። እያንዳንዱ ቃል-ኪዳን ከራሱ ጋር ሀላፊነቶችንና ቃሎችን ያመጣል። ለሁላችንም፣ ልክ ለሔነሪች እንደነበሩት፣ እነዛ ሀላፊነቶች አንዳንድ ጊዜ ቀላል፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ከባድ ናቸው። ነገር ግን አስታውሱ፣ ሀላፊነቶቹ አንዳንድ ጊዜ ከባድ መሆን አለባቸው ምክንያቱም አላማቸው ከሰማይ አባታትና ከተወደደው ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በቤተሰቦች ውስጥ ለዘላለም እንድንኖር በመንገዱ ላይ እንዲያስኬዱን ነው።

ከአብርሐም መጽሐፍ ላይ ቃሎችን ታስታውሳላችሁ፥

“እንደ አምላክ የሆነ ከመሀላቸው ተነሳ፣ ከእርሱ ጋር ለነበሩት እንዲህም አላቸው፥ ወደታች እንሄዳለን እዛ ቦታ ስላለ፣ እነዚህን ቁሳቁሶች እንወስዳለን፣ እነዚህ የሚያርፉበትን መሬት እንፈጥራለን፤

“ጌታ አምላካቸው የሚያዛቸውን ማናቸውንም ነገሮች ሁሉ እንደሚያደርጉ ለማየት፣ በዚህ እንፈትናቸዋለን፤

“እናም የመጀመሪያ ሁኔታቸውን ለሚጠብቁት ይጨመርላቸዋል፤ የመጀመሪያ ሁኔታቸውን የማይጠብቁት ደግሞ የመጀመሪያ ሁኔታቸውን ከሚጠብቁት ጋር በአንድ አይነት መንግስተ ሰማይ ውስጥ ክብር አይኖራቸውም፤ ሁለተኛ ሁኔታቸውን ለሚጠብቁት ደግሞ ለዘላለም በራሳቸው ላይ ክብር ይጨመርላቸዋል።”2

ሁለተኛ ሁኔታችንን መጠበቅ የሚወሰነው ቃል-ኪዳኖችን ከእግዛብሔር ጋር በመግባታችን ላይና በአማኝነት የሚጠይቁንን ሀላፊነት በመወጣት ላይ ነው። ቅዱስ ቃል-ኪዳኖችን በሕይወት ዘመን ሁሉ ለመጠበቅ እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ በአዳኛችን ላይ ይጠይቃል።

አዳምና ሔዋን በእርግጥ ስለወደቁ፣ ግፊቶች፣ ፈተናዎችና ሞት እንደ አለም አቀፋዊ ውርሳችን አሉን። ይሁን እንጂ፣ የሚወደን የሰማይ አባታችን የተወደደ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን ስጦታ ሰጠን። የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ታላቁ ስጦታና በረከት የአለም አቀፋዊ ውርስን፥ የትንሳኤ ቃል-ኪዳንንና ለተወለዱት ሁሉ የዘላለም ሕይወትን የማግኘት ችሎታን ያመጣል።

ዘላለም ሕይወት፣ ከእግዛብሔር በረከቶች ሁሉ ታላቅ የሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ቤተክርስቶያን ውስጥ በሚሰጠው ስልጣን ባላቸው አገልጋዮቹ አማካኝነት ቃል-ኪዳኖችን ስንገባ ወደእኛ ይመጣል። በውድቀቱ ምክንያት፣ የጥምቀት የማንፃትን ውጤቶችና የመንፈስ ቅዱስ ስጦጣን ለመቀበል የእጅ መጫንን ሁላችንም እንፈልጋለን። እነዚህ ስነ-ስርአቶች ተገቢውን የክህነት ስልጣን ባላቸው ሰዎች መከናወን አለባቸው። ከዛ፣ በክርስቶስ ብርሀንና በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ አማካኝነት፣ ሁሉንም ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባቸውን ቃል-ኪዳኖች በተለይም በቤተ-መቅደሱ ውስጥ የሚሰጡትን መጠበቅ እንችላለን። በዛ መንገድና እርዳታ አማካኝነት ብቻ፣ ማንም ሰው እንደ እግዚአብሔር ልጅ ዘላለማዊ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ የእርሱን ወይም የእርሷን ህጋዊ ውርስ ድርሻ መጠየቅ ይችላል።

ለአንዳንዶች እኔን ማዳመጥ ቢያንስ ተስፋ የለሽ ህልም ሊመስል ይችላል።

አማኝ ወላጆች በተቃወሙ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር የገቢትን ቃል-ኪዳኖች ለመስበር በመረጡ ልጆቻቸው ላይ ሲያዝኑ አይታችኋል። ነገር ግን እነዛ ወላጆች ልብና ተስፋን ከሌሎች ወላጃዊ ልምዶች መውሰድ ይችላሉ።

የአልማ ወንድ ልጅና የንጉስ ሞዛያ ወንድ ልጆች ከቃል-ኪዳኖችና ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት ተቃውሞ ኃያል አመፃ ተመለሱ ። ታናሹ አልማ ልጁን ኮሪያንተንን ከአፀያፊ ሀጢያት ወደ አማኝ አገልግሎት ሲመለስ ተመለከተ። መጽሐፈ ሞርሞን የላማናውያንን ፅድቅ የመጥላት ባህሎችን ወደ ጎን ትተው ሰላምን ለማቆየት ለመሞት ቃል-ኪዳን የገቡበትን ታምራት እንዲሁ ዘገበ።

ወደ ታናሹ አልማና የሞዛያ ወንድ ልጆች መልአክ ተላከ። መልአኩ በአባቶቻቸውና በእግዚአብሔር ህዝቦች እምነትን ፀሎቶች ምክንያት መጣ። ከእነዛ የሀጢያት ክፍያ በሰዎች ልብ ውስጥ የመስራት ኃይል ምሳሌዎች ውስጥ መበረታታትንና መፅናናትን መቀበል ትችላላችሁ።

ጌታ የምንወዳቸውን ሰዎች የዘላለም ውርሳቸውን እንዲቀበሉ ለመርዳት በምንጥርበት ሰአት ሁሉንም የተስፋ ምንጮች ሰጥቶናል። ህዝቦችን ወደ እርሱ መሰብሰባችንን በምንቀጥልበት ሰአት እንዲሁ ለማድረግ የእርሱን ግብዣ በሚቃወሙበትም ሰአት እንኳን ቃል-ኪዳኖችን ገብቶልናል ። ተቃውሟቸው ያስከፋዋል፣ ነገር ግን አያቆምም እኛም ማቆም የለብንም። ቀጣይነት ባለው ፍቅሩ ፍፁም ምሳሌነቱን አስቀመጠለን፥ “እናም በድጋሚ፣ ዶሮ ጫጩትዎችዋን በክንፎችዋ እንደምትሰበስብ ስንት ጊዜ ሰበሰብኳችሁ፤ አዎን አቤቱ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ የጠፋችሁት፤ አዎን፣ አቤቱ የእስራኤል ቤት የሆናችሁ እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፤ እናም እናንተ የጠፋችሁ፤ አዎን ዶሮ ጫጩትዎችዋን እንደምትሰበስብ ሁሉ ስንት ጊዜ ሰበሰብኳችሁ፣ እናም እናንተም ግን አልወደዳችሁም።” 3

በዛ በማያባራው የአዳኙ ሁሉንም የሰማይ አባትን የመንፈስ ልጆች ከእርሱ ጋር ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የማምጣት ምኞት ላይ መወሰን እንችላለን። እያንዳንዱ አማኝ ወላጆች፣ አያቶችና ቅድመ-አያቶች ያንን ምኞት ይካፈላሉ። የሰማይ አባትና አዳኙ ምን ማድረግ ስለምንችለውና ስላለብን ፍፁም ምሳሌዎቻችን ናቸው። ፅድቅን በፍፁም አይገፉም ምክንያቱም ፅድቅ መመረጥ ስላለበት። ፅድቅን ግልፅ ያደርጉልናል፣ እንዲሁም ፍሬዎቹ ጣፋጮች እንደሆኑ እንድናይ ይፈቅዱልናል።

ወደ አለም የተወለደ እያንዳንዱ ሰው ትክክል የሆነውንና ስህተት የሆነውን እንድናይና እንድንሰማ የሚረዳንን የክርስቶስን ብርሀን ይቀበላል። እግዚአብሔር ሟች የሆኑ አገልጋዮችን በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት እንድናደርግ የሚፈልገውንና የሚከለክለውን እንድንገነዘብ እንዲረዱን ልኳቸዋል። እግዚአብሔር የምርጫዎቻችንን ውጤቶች እንዲሰማን በመፍቀድ ትክክለኛውን እንድንመርጥ ምቹ ያደርጋል። ትክክለኛውን ስንመርጥ፣ ደስታን—በሰአቱ እናገኛለን። ክፉን ከመረጥን፣ ሀዘንና ፀፀት—በሰአቱ ይመጣል። እነዛ ውጤቶች እርግጥ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ሆን ተብለው ይዘገያሉ። በረከቶቹ አፋጣኝ ከነበሩ፣ ትክክለኛውን መምረጥ እምነትን አይገነባም። እናም ሀዘን አንዳንድ ጊዜ እንዲሁ ሊቆይ ስለሚችል፣ ለሀጢያት ይቅርታን የማግኘት አስፈላጊነት ከሀዘኔታውና ከአማሚነቱ ውጤቶች በፊት ቶሎ እንዲሰማን እምነትን ይጠይቃል ።

አባት ሌሂ በአንዳንድ ወንድ ልጆቹና በቤተሰቦቻቸው ባደረጉት ምርጫዎች ላይ አዘነ። ታላቅና መልካም ሰው—የእግዚአብሔር ነብይ ነበር። በየጊዜው ሰለ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሰከረላቸው። ጌታ ሁሉንም አለማዊ ድርሻዎቹን ትቶ ቤተሰቦቹን ከጥፋት እንዲያድን ሲጠራው የታዛዥነትና የአገልግሎት ምሳሌ ነበር። በሕይወቱ መጨረሻም ላይ ለልጆቹ አሁንም እየመሰከረ ነበር። ልክ እንደ አዳኝ—እና ልባቸውን የማየት ኃይል እያለውና የሁለቱንም የሀዘንና የአስገራሚ የወደፊት ስሜት እያየ—ሌሂ ቤተሰቦቹን ወደ ደህንነት ሊያመጣ ክንዶቹን መዘርጋቱን ቀጠለ።

ዛሬ የአባት ሌሂ ሚሊዮኖች ዘሮች ለእነርሱ የነበረውን ተስፋ እያስረዱ ነው።

እናንተና እኔ ከሌሂ ምሳሌ የሆነ ነገር ለማውጣት ምን ማድረግ እንችላለን? ከምሳሌው መጽሐፍ ቅዱስን በፀሎታማነት በማጥናትና በመጠበቅ የሆነ ነገር ማውጣት እንችላለን።

የተስፋን ውርስ ለቤተሰባችሁ ለመስጠት በምትሞክሩበት ጊዜ ሁለቱንም አጭሩንና እረጅሙን እይታዎችን እንድትወስዱ ሀሳብ አቀርባለው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጭንቀቶች ይኖራሉ እናም ሴጣን ያጓራል። እንዲሁም ጌታ በራሱ ጊዜና መንገድ እንደሚሰራ በማወቅ በታጋሽነት በእምነት የምንጠብቃቸው ነገሮች አሉ።

የምትወዷቸው ሰዎች በእድሜ ትንሽ ሲሆኑ በቅድሚያ ማደረግ የምትችሉት ነገሮች አሉ። አስታውሱ ልጆች በእድሜ ትንሽ በሚሆኑበት ሰአት የዘወትር የቤተሰብ ፀሎት፣ የቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱሰ ጥናትና በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ ምስክርነታችንን ማካፈል ቀላልና የበለጠ ውጤታማ ናቸው። ትንሸ ልጆች አብዛኛውን ጊዜ ከምንገነዘበው በላይ ለመንፈስ የበለጠ ቅርብ ናቸው።

ትልቅ ሲሆኑም ከእናንተ ጋር የዘመሩትን መዝሙር ያስታውሳሉ። ሙዚቃዎችን ከማስታወስም ባሻገር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎችንና ምስክርነትን ያስታውሰሉ። መንፈስ ቅዱስ ትውስታቸውን ማምጣት ይችላል፣ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱሳት ቃላቶችና መዝሙሮች ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ። እነዛ ትውስታዎች ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ከሚያመራቸው መንገድ ተለይተው ለተወሰነ ጊዜ ምናልባት ለአመታት ሲዳክሩ ወደ መንገዳቸው ሊመልሳቸው የሚችል ስበትን ያወጣሉ።

የምንወዳቸው ሰዎች የአለም ስበት ሲሰማቸውና የመጠራጠር ደመና እምነታቸውን የሚያሸንፍ መስሎ ሲታይ እረጅሙ እይታ ያስፈልገናል። እንዲመራንና እንዲያጠነክራቸው እምነት፣ ተስፋና ልግስና አለን።

እንደ ለሁለት ሕያው የእግዚአብሔር ነብያት አማካሪነት ያንን አይቻለው። የተለየ ማንነቶች ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። ነገር ግን ቋሚ ተስፈኛነትን የሚጋሩ ይመስላሉ። አንድ ሰው በቤተክርስቲያን ውስጥ ሰለ አንድ ነገር የማስጠንቀቂያ ደውል ሲያነሳ፣ የእነርሱ በጣም ተደጋጋሚ ምላሽ “ኦ፣ ነገሮች ይስተካከላሉ” ነው። በአጠቃላይ የማስጠንቀቂያ ደውሉን ከሚያስተጋቡት ሰዎች ይልቅ የበለጠ ስለ ችግሩ ብዙ ያውቃሉ።

የጌታንም መንገድ እንዲሁ ያውቃሉ፣ ስለሆነም ሁልጊዜ ስለ መንግስተ-ሰማዩ ተስፈኞች ናቸው። በአናቱ ላይ እንዳለ ያውቃሉ። ሙሉ ኃያል ነው እንዲሁም ያስባል። የቤተሰባችሁ መሪ እንዲሆን ከፈቀዳችሁለት ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።

አንዳንዶቹ የሔነሪች አይሪንግ ዘሮች የኳተኑ ይመስሉ ነበር። ነገር ግን ብዙዎቹ የቅም ቅም አያት ልጆች አይተዋቸው ለማያውቋቸው ዘሮች ስነ-ስርአቶችን ለመፈፀም ወደ እግዚአብሔር ቤተ-መቅደሶች ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ይሄዳሉ። እርሱ ከተወው የተስፋ ውርስ ውስጥ ወጥተው ሄዱ። በብዙ የራሱ ዘሮች የባለቤትነት ድርሻ እንዳላቸው እየታየ ያለውን ውርስ ተወ።

በእምነት ሁሉንም ካደረግን በኋላ፣ ማሰብ ከምንችለው በላይ ጌታ ተስፋችንን ለቤተሰቦቻችን ታላቅ በረከቶች ያረጋግጣል። እንደ ልጆቹ፣ ለእነርሱና ለእኛ ጥሩውን ይፈልጋል።

ሁላችንም የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ነን። የናዝሬቱ ኢየሱስ የተወደደ ልጁና ከሞት የተነሳው አዳኛችን ነው። ይህች የእርሱ ቤተክርስቲያን ናት ቤተሰቦች ዘላለማዊ መሆን እንዲችሉ በውስጡ የክህነት ቁልፎች አሉ። ይህ ዋጋ የማይገዛው የውርስ ተስፋችን ነው። እውነት እንደሆነ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመሰክራለው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሔነሪ አይሪንግ የድሮ ልምድ ማስታወሻዎችን፣ 1896 (እ.አ.አ)፣ በታይፕ የተፃፈ፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ላይብረሪ፣ 16–21 ተመልከቱ።

  2. አብርሐም 3፥24–26

  3. 3 ኔፊ 10፥5