2014 (እ.አ.አ)
የእግዚአብሔር አዝመራ
ኦገስት 2014


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2014 (እ.አ.አ)

የእግዚአብሔር አዝመራ

ምስል
ፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ

ክሪስታ የምትባል ሴት በአንድ ወቅት ለአንድ ትንሽ የዘር ድርጅት ሰርታ ነበር። ስራዋን ወዳው ነበር። እሷ የሸጠችው እያንዳንዱ ትንሽ ዘር ተአምር በሆነ ሁኔታ ወደ ካሮት፣ ጎመን፣ ወይም ትልቅ ዛፍነት የመቀየር ብቃት መኖሩ የታላቅ መደነቅ ምንጭ ነበር።

ክሪስታ ኮምፒውተሯ ጋር ተቀምጣ ትእዛዝ መቀበል እና ጥያቄዎችን መመለስ ትወድ ነበር። ነገር ግን አንድ ቀን ግራ ያጋባትን ቅሬታ ተቀበለች።

“ዘሮቹ አይሰሩም፣” አለ ደንበኛው። “ከሁለት ወር በፊት ገዛኋቸው እና አሁንም ምንም ነገር የለም።”

“በጥሩ መሬት ላይ ተክለሀቸዋል እና በቂ ውሀ እና የፀሀይ ብርሀን ሰጥተሀቸዋል?” በማለይ ክሪስታ ጠየቀች።

“አይ፣ ግን የበኩሌን አድርጌአለሁ፣” ብሎ ደንበኛው መለሰ። “ዘሮቹን ገዛኋቸው። ምንም ቢሆን፣ እንደሚያድጉ የተረጋገጡ ናቸው።”

“ግን አልተከልካቸውም?”

“በፍጹም አላደረኩም። ያማ ማለት እጆቼ እንዲቆሽሹ ማድረግ ነው።”

ክሪስታ ስለ እዚህ ጉዳይ አሰበች እና የመትከያ መመሪያዎች መጻፍ እንዳለበት ወሰነች። የመጀመሪያው መመሪያ ምን መሆን እንዳለበት ወሰነች፤ “ዘሮቹ እንዲያድጉ የመትከያ መመሪያዎቹን መከተል አለብህ። መደርደሪያ ላይ አስቀምጠሀቸው እንዲያድጉ መጠበቅ አትችልም።”

ብዙም ሳይቆይ ሌላ ቅሬታ ግራ ያጋባት ጀመር።

“ዘሮቹ እያፈሩ አይደሉም፣” አንድ ደንበኛ አሳወቀ።

“በመልካም መሬት ላይ ተክለሀቸዋል?” ክሪስታ መለሰች። “ተገቢውን የውሃ መጠን እና የፀሀይ ብርሀን ሰጥተሀቸዋል?”

“ኦ፣ አዎ” ደንበኛው አጥብቆ ገለፀ። “በማሸጊያው ላይ ልክ እንደሚለው ሁሉንም አድርጌያለሁ። ነገር ግን አይሰሩም።”

“የተከሰተ ምንም አይነት ነገር ነበርን? አብበው ነበር?”

ደንበኛውም “ምንም ነገር አልተከሰተም፣” አለ። “ልክ እንደ መመሪያው ነበር የተከልኳቸው። ለእራት ቲማቲሞች እንዲኖሩኝ ተስፋ አድርጌ ነበር። “አሁን በጣም ተበሳጭቻለሁ።”

“ቆይ፣” ክሪስታ መለሰች። “ዘሮቹን የተከልኩት ዛሬ ነው እያልክ ነው?”

“አስቂኝ አትሁኚ፣” ደንበኛው መለሰ። “ከሳምንት በፊት ነው የተከልኳቸው። በመጀመሪያው ቀን ቲማቲሞቹን ለማየት አልጠበኩም፤ ታጋሽ ነበርኩ። ልንገርሽ፣ በዚያ እና በአሁን ጊዜ መሀል ብዙ ውሃ ማጠጣት እና መጠበቅ ነው ያለው።”

ክስታ ሌላ መመሪያ መጨመር እንዳለባት አወቀች፤ “እነዚህ ዘሮች ከባይሎጂ ህጎች ጋር ይጣጣማሉ። ዘሮቹን ጠዋት ከተከልካቸው እና በሳምቱ መጨረሻ ላይ ቲማቲሞችን ለመብላት ከጠበቅክ፣ ትበሳጫለህ። ታጋሽ መሆን እና የተፈጥሮ ስራ በፊትክ እንዲገለጥ መጠበቅ አለብህ።”

ክሪስታ ሌላ ቅሬታ እስክትቀበል ድረስ ሁሉም መልካም ነበር።

“በዘሮችሽ በጣም ተበሳጭቻለሁ፣” ደንበኛው መናገር ጀመረ። “ማሸጊያው ልክ እንደሚገልጸው ተከልኳቸው። ውሃ ሰጠኋቸው፣ የጸሀይ ብርሀን ማግኘታቸውን አረጋገጥኩ፣ እና በስተመጨረሻም አዝመራቸውን እስከሚያበቅሉ ድረስ ጠበኩ።”

“ሁሉንም በትከክል ያደረክ ይመስላል፣” አለች ክሪስታ።

“ያ ሁሉ በጣም መልካም ነው፣” ደንበኛው መለሰ። “ግን ያገኘሁት ዝኩኒ ነበር!”

“መዝገቤ ያዘዝካቸው ዘሮች እነዛ እንደነበሩ ያሳያል፣” አለች ክሪስታ።

“ግን እኔ ዝኩኒ አልፈልግም፤ ዱባ ነው የምፈልገው!”

“አልገባኝም።”

“ያለፈው አመት ዱባ ባፈራበት በዱባ ማሳዬ ላይ ነበር ዘሮቹን የተከልኳቸው። ተክሎቹን በየቀኑ አሞገስኳቸው፣ እንዴት የሚያምሩ ዱባዎች እንደሚሆኑ እየነገርኳቸው። ነገር ግን በትልቅ፣ ክብ፣ ብርቱካናማ ዱባ ፈንታ፣ ረጅም፣ አረንጓዴ ዝኩኒ አገኘሁ። ብዙ ናቸው!”

መመሪያዎቹ እንደማይበቁ እና አንድ መርህ መጨመር እንዳለበት ክሪስታ አወቀች፤ “አዝመራውን የምትተክሉት ዘር እና የተከላችሁበት ጊዜ ይወስነዋል።”

የአዝመራው ህግ

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ እግዚአብሔር አዝመራ አስተማረ፤

“አትሳቱ፤ እግዚአበሔር አይዘበትበትም፤ ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደሞ ያጭዳል።

“በገዛ ስጋው የሚዘራ ከስጋ መበስበስን ያጭዳልና፣ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ስራን ለመስራት አንታክት” (ገላትያ 6፥7–9)።

በቅርብ ጊዜያት፣ ጌታ ተጨማሪ ጥበብን እና በዚህ ጽኑ ህግ ምልከታን ሰጥቶናል፤

“ህግ አለ፣ በማይሻር ሁኔታ ከዚህ አለም ምስረታዎች በፊት በመንግስተ ሰማይ ውስጥ የተገለፀ፣ በእርሱም ላይ ሁሉም በረከቶች የተመሰረቱበት

“እና ምንም አይነት በረከት ከእግዚአብሔር ስናገኝ፣ ቅድሚያ በተነገረው ህግ ላይ ታዛዥ በመሆን ነው” (ትናቃ 130፥20–21)።

የዘራነውን፣ እናጭዳለን።

የእግዚአብሔር አዝመራ ከሚገመተው በላይ የከበረ ነው። እርሱን ለሚያከብሩት፣ የተትረፈረፈው በረከቶቹ “በተጨቆነና በተነቀነቀ በተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ ይመጣሉ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሶ ይሰፈርላችኋልና” (ሉቃስ 6፥38)።

ልክ ምድራው ዘሮች ጥረት እና ትግስት እንደሚያስፍጋቸው ሁሉ፣ ብዙ የሰማይ በረከቶችም እንዲሁ። ሀይማኖታችንን በመደርደሪያ ላይ አስቀምጠን የመንፈሳዊ በረከቶችን አዝመራ መጠበቅ አንችልም። ነገር ግን የወንጌል መርሆችን በቤተሰባችን የቀን ተቀን ሕይወት ውስጥ ከተከልንና ከተንከባከብን፣ ልጆቻችን ለራሳቸውና ለወደፊት ትውልዶች ታላቅ ጥቅም ያላቸውን መንሰፋዊ ፍሬዎች ለማፍራት እንዲያድጉ ከፍተኛ እድል አለ።

ለጸሎታችን የእግዚአብሔር መልስ ሁሌ ወዲያውኑ አይመጡም፣ አንዳንዴ ሙሉ ለሙሉ የማይመጡ ሆነው ይገኛሉ፣ ነገርግን እግዚአብሔር ለልጆቹ የተሻለውን ያውቃል። በእርግጥ፣ አንድ ቀን በይበልጥ በጥራት እናያለን፤ እና በዚያን ቀን የሰማይን መልካምነት እና ለጋስነት እናስተውላለን።

እስከዚያ፣ ቃል የተገባው እና ውድ የእግዚአብሔር የበረከት አዝመራ የኛ መሆን እንዲችል ግባችን እና ታላቅ ደስታችን በጌታ እና በአዳኛችን መንገድ መራመድ እና በመልካም እና በፀዳ ሁኔታ መኖር ነው።

የዘራነውን፣ እናጭዳለን።

ያ የሰማይ ህግ ነው።

ያ የእግዚአብሔር የአዝመራ ህግ ነው።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የእግዚአብሔር የአዝመራ ህግ በግንኙነት፣ ንግግር እና ምስክርነት፣ ወይም ስራ እና በትምህርት እቅድ ላይ እንዴት እንደሚተገበር ከምትጎበኟቸው ሰዎች ጋር ተወያዩ። ከዚህ ህግ ጋር የሚዛመዱ ጥቅሶችን ማንበብ እና ማሰብ ትችላላችሁ፣ እንደ መጽሐፈ ምሳሌ 11፥182ኛ ቆሮንጦስ 9፥6፤ እና አልማ 32። የቅድስና ውጤቶችን እንዲያገኙ ያለፉትን ግቦች እንዲከልሱ እና አዲስ ግቦች እንዲያወጡ አበረታቷቸው። ዘላቂ አላማቸው ላይ ለመድረስ በቋሚነት ለመተግበር እቅድን እንዲያዘጋጁ እርዷቸው።

አትም