የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ነሐሴ 2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ መሲህ
በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለበለጠ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።
ቅዱሳት መጻህፍት “በቅዱሱ መሲሁ መልካም ስብዕና፣ እና ምህረት፣ እና ፀጋ አማካኝነት” በእግዚአብሔር እይታ ውስጥ መኖር እንደምንችል ያስተምራሉ(2ኛ ኔፊ 2፥8) መሲህ “የአራማይክ እና ሂብሩ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ‘የተቀባ’ ማለት ነው። … በአዲስ ኪዳን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ተብሎ ተጠርቷል፣ ይህም ደግሞ መሲህ ለሚለው የግሪክ ቃል አቻ ነው።ይህም የተቀባ ነብይ፣ ቄስ፣ ንጉስ፣ እና አዳኝ ማለት ነው።”1
የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሸንጎ አባል የሆኑት ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ መሰከሩ፤ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእስራኤሉ ቅዱስ፣ እንደ የጌቶች ጌታ እና የነገስታት ንጉስ ሆኖ ለመግዛት ወደ ምድር በመጨረሻ በታላቅ ክብር አንድ ቀን ተመልሶ የሚመጣው መሲህ እንደሆነ አውቃለሁ። ሰው መዳን የሚችልበት ከሰማይ በታች ሌላ አንድም ስም እንዳልተሰጠ አውቃለሁ።”2
ፕሬዘዳንት ዴይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ የአጠቃላይ አመራር ሁለተኛ አማካሪ “ኢየሱስ ክርስቶስ የአለም አዳኝ እና ቤዛ ነው፣” አሉ። “እርሱ ቃል የተገባው መሲህ ነው። ፍጹም የሆነ ህይወት ኖረ እናም ለሀጢያቶቻችን ቤዛ ሆነ። መቼም ቢሆን ከእኛ ጎን ይሆናል። ጦርነቶቻችንን ይዋጋል። ተስፋችን ነው፤ ደህንነታችን ነው፤ እርሱ መንገድ ነው።”3
ተጨማሪ ጥቅሶች
ከቅዱሳት መጻህፍት
የክርስቶስ የሴት ደቀመዛሙርት የእርሱን እንደ መሲህ የነበረውን ሚና ምስክሮች ነበሩ። መቅደላዊት ማሪያም የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ነበረች። ክርስቶስ ትንሳኤን ባደረገበት ጠዋት “ከመቃብሩ የተፈነቀለውን ድንጋይ” ለመጀመሪያ ጊዜ ያየችው እርሷ ነበረች። እርሷ አካሉ በመቃብሩ አለመሆኑን ስትረዳ “እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጪ ቆማ ነበር።”
ከዛም “ወደ ኋላ ዞር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስም እንደነበር አላወቀችም።
“ኢየሱስም፣ አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሏት፣ ጌታ ሆይ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።
“ኢየሱስም፣ ማርያም አላት። እርስዋ ዞር ብላ በእብራይስጥ፣ ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም መምህር ሆይ ማለት ነው።” ማርያምም አትክልተኛው ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ መሲሁ እንደነበር አስተዋለች። (ዮሐንስ 20፥1–17ተመልከቱ።)
በ © 2014 (እ.አ.አ) Intellectual Reserve, Inc. መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፥ 6/14 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፥ 6/14 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, August 2014. Amharic. 10868 506 ትርጉም