2015 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህሪያት፤ በልግስና እና ፍቅር መሞላት
ኦክተውበር 2015


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት ጥቅምት 2015 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህሪያት፤ በልግስና እና ፍቅር መሞላት

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። አዳኝን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ። ለተጨማሪ መረጃ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

የቅዱስ መፅሐፍት መምሪያው ልግስናን እነዲህ ይተረጉመዋል “ታላቁ፣ ድንቁ እና ጠንካራው የፍቅር አይነት” (“ልግስና”) የኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅር ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንማር እና እንደ እርሱ ለመሆን ስንጥር፣ የእርሱ ንፁህ ፍቅር በህይወታችን መሰማት የጀምራል እና እርሱ እንደሚያደርገው ሌሎችን ለማፍቀር እና ለማገልገል እንነሳሳለን። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዳሉት፣ “ልግስና ማለት እኛን ባስቀየመን ሰው ላይ ትግስት ሲኖረን ነው።” “በቀላሉ የመናደድ ስሜትን መቋቋም ነው። ድክመቶችን እና ስህተቶችን መቀበል ነው። ሰዎችን በእውነት እንደሆኑት መቀበል ነው። ከአካላዊ እይታዎች በላይ ወደ በጊዜ የማይደበዝዙ ባህሪያት መመልከት ነው። ሌሎች ላይ የመፍረድ ስሜትን መቋቋም ነው።”1

በመጸሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ታላቅ እውነት እንማራለን “በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮቹ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደ እርሱ ሆነን እንዳለ እናየዋለንና ይህ ተስፋም ይኖረናልና ልክ እርሱ ፍፁም እንደሆነ እኛም ፍፁማን እንሆናለንና” (ሞሮኒ 7፥48)።

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት

ዮሀንስ 13፥34–35፤ 1 ቆሮንቶስ 13፥1–13፤ 1 ኔፊ 11፥21–23፤ ኤተር 12፥33–34

ከታሪካችን

“አንድ በቅርቡ እመበለት የሆነች እህት አብረዋት ለዘኑት እና ላጽናኗት የቤት ለቤት አስተማሪዎች አመስጋኝ ነበረች። እንዲህ ፃፈች፤ የሚያዳምጠኝ፣ ላገኘው የምችል ሰው በጣም አስፈልጎኝ ነበር። እና አዳመጡ። እኔንም አፅናኑኝ። ከእኔም ጋር አለቀሱ። እና አቀፉኝ [እና] በእነዚያ ጥልቅ ተስፋ የመቁረጥ እና ክፉ የብቸኘነት የመጀመሪያ ወራት ውስጥ ረዱኝ።

“ከቤት ለቤት አስተማሪ እውተኛ ልግስናን ያገኘች ሌላ ሴት ስሜቷን አሳጥራ ስትናገር፤ ለመጎብኘት በብትመዘግብበት መፅሐፍት ላይ ከቁጥር በላይ እንደነበርኩ አውቅ ነበር። ስለ እኔ እንደምትጨነቅ አውቅ ነበር።”2

እንደነዚህ እህቶች፣ የዚህ በአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጉባኤ ፕሬዘዳንት የሆኑት፣ የፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ. ታከር [1924 – 2015 (እ.አ.አ)] አርፍተ ነገርን እውነታነት ብዙ በአልም ዙሪያ ያሉ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ያረጋግጣሉ፤ “ቤተሰብ ወደየትም ቢሄድ፣ የቤተክርስቲያን ቤተሰብ እንደሚጠብቀው ማወቅ እንዴት አፅናኝ ነው። ከደረሱበት ቀን አንስቶ፣ እርሱ በክህነት ስልጣን ቡድን ውስጥ ሲካተት እርሷ ደግሞ በሴቶች መረዳጃ ውስጥ ትካተታለች።”3

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን, “Charity Never Faileth,” Liahona, ህዳር 2010, 124.

  2. Daughters in My Kingdom፡ The History and Work of Relief Society 2011፣ 119-120.

  3. Daughters in My Kingdom 87.

ይህን አስቡበት

ክርስቶስ የፍቅር እና ልግስና ፍፁም ምሳሌ የሆነው እንዴት ነው?

አትም