2015 (እ.አ.አ)
ችቦአችሁን ለኩሱ፡ የ30 ቀን ሙከራ
ኦክተውበር 2015


ወጣቶች

ችቦአችሁን ለኩሱ፡ የ30 ቀን ሙከራ

ስራ ለበዛባቸው በቤተክርሰቲያን ውስጥ ላሉ ወጣቶች፣ በድርጊት ድግግሞሽ ውስጥ ለመያዝ ቀላል ሊሆን ይችላል፣ በተለይም በመንፈሳዊ ነገሮች። ቅዱሳት መጽሐፍቶችን እናነባለን፣ እና በየቀኑ በሚባል ሁኔታ በተመሳሳይ መልኩ እናመልካለን እና ከዛ ለምን በመንፈሳዊ መዋዠቅ ውስጥ የሆንን በመምሰላችን እንገረማለን።

መንፈሳዊ ችቦአችሁን በደምብ እየነደደ ለማቆየት የተሸለው አንዱ መንገድ ትርጉም ያላቸው መንፈሳዊ ተሞክሮዎች እንዲኖራችሁ ማረጋገጥ ነው። ነገር ግን ያ ከድርጊት ይልቅ ለንግግር ይቀላል፣ ስለዚህ ቀጣዮቹ ሀሳቦች በመንፈሳዊ እድገት እንድትቀጥሉ የሚረዷችሁ ናቸው፤ ከዚህ በፊት አድርጋችሁ የማታውቁት (ለማድረግ በጣም የሚከብድ) ከወንጌል ጋር የተያያዘ ድርጊትን ለአንድ ወር በየቀኑ ለማድረግ አስቡ። በትንሹ መጀመር ትችላላችሁ ምክንየቱም ትንሽ ለውጦችን ማለቂያ ወደሌላቸው መቀየር እንደሚቀል ትረዳላችሁ። ከመንፈሳዊ የምቾት ስፍራ ውስጥ የሚያስወጡ ነገሮችን ማድረግ የበለጠ እምነት እና ጥረትን ከእኛ የጠይቃል፣ ነገር ግን ስናደርጋቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር እንዲሆን እየጋበዝን ነው፣ እና ታላቅ እምነት በሰማይ አባታችን ላይ እና ወደ እርሱ ለመቅረብ ፍላጎትን እያሳየን ነው። እንዲያስጀምራችሁ ጥቂት ሀሳቦች እነዚህ ናቸው፤

  • ጠዋት እና ማታ ለመፀለይ እቅድ አውጡ። ጮክ ብሎ ለመፀለይ ሞክሩ።

  • ከትምህርት ቤት በፊት 15 ደቂቃ ቀደም ብላችሁ ተነሱ እና ቅዱስ መፅሐፍታችሁን አንብቡ።

  • ያለፉ የአጠቃላይ ኮንፈራነስ ንግግሮችን አንብቡ።

  • በማህበራዊ ገልፆች ለላይ ጥቅስ ከመጽሐፈ ሞርሞን ለጥፉ።

  • ከመደበኛ ሙዚቃችሁ ይልቅ መዝሙሮችን ወይም የቤተክርስቲያን ሙዚቃዎችን አዳምጡ።