ልጆች
ችቦአችሁን ብርሀናማ አድርጉ
ከረጅም ጊዜ በፊት በግሪክ፣ የሚያበራ ችቦ የሚይዙ ሯጮች ያሉበት ውድድር ነበር። ችቦው እንደነደደ ሙሉውን ውድድር የሮጠ ሁሉ አሸናፊ ነበር። ህይወት ልክ እንደዛ ነች ይላሉ ፐሬዘዳንት ኡክዶርፍ። የምንይዘው ችቦ የክርስቶስ ብርሃን ነው። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን ስንሞክር፣ ችቦዎቻችንን በደምብ እንዲነዱ እናደርጋለን።
እንደ ኢየሱስ ለመሆን እና ችቦአችሁ ብሩህ እንዲሆን ምን ነገሮችን ማድረግ ትችላላችሁ? ከቀጣዩ ዝርዝር ውስጥ ምረጡ፤
-
ብቸኛ የሚመስልን ሰው ፈገግታ አሳዩ ወይም ሰላም ማለት
-
በአንድ ሰው ላይ ተናዳቹ መቆየት
-
ሰውነታችሁን መንከባከብ
-
በወንድማቹ ወይም በእህታቹ ላይ መቀለድ
-
ነቢይን መታዘዝ
-
ስህተት ስትሰሩ ተስፋ መቁረጥ
-
አንድ ሰው መርዳት