2015 (እ.አ.አ)
በገና ጊዜ ለማገልገል የሚቻልበት መንገዶች
ዲሴምበር 2015


ወጣቶች

በገና ጊዜ ለማገልገል የሚቻልበት መንገዶች

ፕሬዘደንት ሞንሰን፣ በልዩ በገና ጊዜ፣ ሽማግሌዎችን እና በመንከባከቢያ ቦታዎች የሚገኙትን በምጎብኘት ጊዜአቸውን ያሳልፋሉ። ጎብኚዎችን በመቀበላቸው የሚደሰቱ እና ሌሎች ለማይመጡት ጎበኚዎች ተስፋ ብቻ ያላቸው እንዳሉ አመልክተዋል። አንድ ሰውን የሚጠብቁ ሰዎች አሉ፣ ምናልባት በዚህ ገና እናንተም ያ ሰው ለመሆን ትችላላችሁ።

የሚከተሉት በዚህ ገና ማንም ሰው ብቸኛነት እንዳይሰማቸው ለማድረግ የምትችሉበት ጥቂት መንገዶች ናቸው። በህብረተሰባችሁ መካከል ለመርዳት የምትችሉበትን ተጨማሪ መንገዶች ለማሰብ ትችላላችሁ። ጉብኝታችሁን የሚጠብቅ ሰው አለ?

  • በዎርዳችሁ ወይም በቅርንጫፋችሁ ለሚገኙ ሚስዮኖች፣ ላላገቡት፣ እና በእድሜ ለገፉት አባላት የምትልኳቸውን የገና ፖስትካርዶችን አዘጋጁ።

  • በህብረተሰባችሁ ድርጅቶች በፈቃደኛነት በመስራት ተሳተፉ።

  • ለጓደኞቻችሁ እና ለጎረቤቶቻችሁ መጸሐፈ ሞርሞንን እንደ ገና ስጦታ ስጡ።

  • በዎርዳችሁ ወይም በቤተሰባችሁ ውስጥ ያሉትን በእድሜ የገፉ ሰዎች ጎብኙ።

  • ለጎረቤቶቻችሁ ስጦታዎችን ለመስጠት አዘጋጁ።

አትም