2015 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህሪያት፥ ሩህሩህ እና ደግ
ዲሴምበር 2015


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት ታህሳስ 2015 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህሪያት፥ ሩህሩህ እና ደግ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ እሹ። የአዳኝን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ ወደ reliefsociety.lds.org ሂዱ።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት፣ ቤተሰብ፣ እርዳታ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ፣ ርህራሄ ማለት ከሌላ ጋር መሰቃየት ማለት ነው። ይህም የሌላን ስሜት መካፈልን፣ ማዘንን፣ እና ምህረትን ማሳየት ማለት ነው።1

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን ኢየሱስ በርህራሄ የማሰብ ብዙ ምሳሌዎች አሳይቶናል ብለዋል። በቤተ ሳይዳ መጠመቂያ ቦታ የነበረው አካለ ስንኩል፣ ስታመነዝር የተያዘችው ሴት፣ በያቆብ የውሀ ጉድጓድ የነበረችው ሴት፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅ፣ የማሪያም እና የማርታ ወንድም አልዓዛር፣ እያንዳንዱም በኢያሪኮ መንገድ ላይ እንደቆሰለው ሰው አይነት ነበሩ። እያንዳንዱም እርዳታ ያስፈልጋቸው ነበር።

በቤተ ሳይድ ለነበረው አካል ስንኩል ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ተነሳ! መኝታህን ተሸክመህ ሂድ። ለኃጥያተኛዋ ሴትም ይህን ምክር ሰጣት፣ ሂጂ፣ ከእንግዲህ ግን ኃጥያት አትስሪ። ውሀ ለመቅዳት የመጣችውን ለመርዳትም፣ የዘላለም ውሀ ምንጭ የሆነውን የውሀ አቀረበላት። ለሞተችው የኢያኢሮስ ሴት ልጅም ይህን ትእዛዝ ሰጣት፣ አንቺ ልጅ ተነሺ። ለተቀበረውም አልዓዛርም ና ውጣ።

አዳኝም የማያልቅ የርሕራሔ ችሎታውን ሁልጊዜም አሳይቷል። የእውነት ርህራሔ ኗሪ ምሳሌ የሆነው እንዲገባም የልባችንን በር እንክፈት።2

ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍቶች

መዝሙር 145፥8ዘካርያስ 7፥91 ጴጥሮስ 3፥8ሞዛያ 15፥1፣ 93 ኔፊ 17፥5–7

ከቅዱሳት መጻህፍት

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ሁለተኛ አማካሪ ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ ባለቤቴ እና እኔ በ17 አመት ሴት ልጃችን አጠገብ ተንበረከክን እና ለህይወቷ ለመንን አሉ። መልሱ ግን አይሆንም ነበር። ነገር ግን [አዳኝ] በሀዘናችን ርህራሄ እንደሚሰማው ለማወቅ ችለን ነበር።3

ከአዳኝ ህይወት ታሪኮች ውስጥ የምወደው የአልዓዛር ታሪክ ነበር። ቅዱሳት መጻሕፍት ኢየሱስ ማርታን፣ እህቷን [ማሪያም]፣ እና [ወንድማቸውን] አልዓዛር ያፈቅር ነበር።4 አልዓዛር ሲታመም፣ ለኢየሱስ መልእክት ተላከ፣ ነገር ግን በዚያ ሲደርስ አልዓዛር ሞቶ ነበር። ማሪያም ወደ ኢየሱስ ሮጠች፣ በእግሩ ስር ወደቀች፣ እና አለቀሰች። ኢየሱስም ማሪያም ስታለቅስ ሲመለከት በመንፈሱ አዘነ እንባውን አፈሰሰ (ዮሀንስ 11፥33, 35)።

ያም ሀላፊነታችን ነው። ለራሳችን በስሜት መሰማት እና ማየት እና ከዚያም የሰማይ አባት ልጆች በሙሉ እንዲሰማቸው እና እንዲያዩ እናም አዳኛችን ሁሉንም ኃጢያቶቻችንን ብቻ ሳይሆን ደግሞም ህመማችንን እና እንዴት እንደሚያፅናናን ለማወቅ ይችል ዘንድ ስቃዮቻችንን በራሱ ላይ እንደወሰደ እንዲያውቁ ማድረግ ይገባናል።5

ማስታወሻዎች

  1. የቅዱሳት መጻህፍት መምሪያ፣ ርህራሄ

  2. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ የርህራሔ ስጦታ፣ Liahona, መጋቢት 2007 (እ.አ.አ)፣ 4–5, 8።

  3. ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ ጌታ አልረሳችሁም Ensign ወይም Liahona, ህዳር 2012 (እ.አ.አ) 120።

  4. ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ፣ The Lord Has Not Forgotten You፣ 118.

  5. ሊንዳ ኤስ. ሪቭስ፣ The Lord Has Not Forgotten You፣ 120.

ይህን አስቡበት

በርህራሄነታችን ማን ሊባረክ ይችላል?

አትም